🇺🇸🇸🇸 ዩናይትድ ስቴትስ በደቡብ ሱዳን እየተባባሰ የመጣውን የፀጥታ ሁኔታ ተከትሎ ከአስቸኳይ ጊዜ ሠራተኞች ውጪ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች
🗣 “በተለያዩ የፖለቲካ እና የጎሳ ቡድኖች መካከል የሚካሄደው ግጭት ቀጥሏል። ሕዝቡ በቀላሉ የጦር መሳሪያዎችን እያገኘ ነው። በተጨማሪም በመላ ሀገሪቱ የተንሰራፋው የከብት ዝርፊያ ወደ ግጭት ሲያምራ ይታያል" ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ "እንደ የመኪና ዝርፊያ፣ ግድያ፣ የደፈጣ ጥቃት፣ አካላዊ ጥቃት፣ ዝርፊያ እና እገታን የመሳሰሉ ከባድ ወንጀሎች ጁባን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን እየተስፋፋ ነው" ሲል የገለጸ ሲሆን፤ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች በሚያጋጥማቸው ትንኮሳ እና ጥቃት ምክንያት ስራቸው "በጣም አደገኛ" ሆኗል ብሏል።
🇺🇳 ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፤ መሪዎች በሀገሪቱ ሌላ አስከፊ ቀውስ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና በግጭቱ አፈታት ዙርያ የፈረሙትን የሰላም ስምምነት እንዲያከብሩ ጠይቋል።
🗣 "ደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነቱን በመተግበር፣ ተቋማትን በማጠናከር እና የዴሞክራሲ መሠረት በመገንባት ወደፊት መጓዝ ይኖርባታል፡፡ አሁን በመታዘብ ላይ ያለነው ከዓመታት በፊት የነበረውንና ሀገሪቷን ለውድመት የዳረገውን ግድየለሽ የስልጣን ሽኩቻ ነው" ሲሉ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ያስሚን ሶካ በመግለጫቸው ተናግረዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia