የዚህን ልጅ የቲክቶክ መልዕክቶችን ለሰከንድ ችሎ ማድመጥ ይከብዳል። አሳዳጊ የበደለው ባለጌ ነው። በዚህ ልክ ጋጠወጥ ለመሆን የተለየ ችሎታ ይጠይቃል።
አንዳንድ ድኩማኖች ሌላ የሚታወቁበት ዕውቀትም ሆነ መልካም ምግባር ሳይኖራቸው ሲቀር በብልግናም ቢሆን ለመታወቅ ራሳቸውን በእጅጉ ያዋርዳሉ። ከሶስት አስርት ዓመታት በፊት ሰልማን ሩሽዲ የተባለ እንግሊዛዊ satanic verses የተሰኘ በነብያችን ﷺ እና በቤተሰቦቻቸው ዙሪያ የሚያጠነጥን ልብ ወለድ ጽፎ ነበር። መጽሀፉ እዚህ ግባ የማይባል ቢሆንም ነብዬን ﷺ ስላንቋሸሸ ብቻ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ተጎናጽፏል። የተለያዩ አካላትም ሽልማት ሰጥተውታል። በተቃራኒው ከብሪታንያ የቀኝና የግራ ክንፍ ፖለቲከኞች ድርጊቱን በማውገዝ ከሰውየው ነውር ራሳቸውን ያራቁ ነበሩ። ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍም በለንደን አድርገዋል። ከኛም ዘንድ በግለሰብ ደረጃ የዚህን ባለጌ ነውር የተቃወሙ እንዳሉ አይተናል። በተቋም ደረጃ ግን የተለየ ነገር እስካሁን አላየሁም።
አሜሪካ ውስጥም በአባላት ድርቅ የተመታች አንዲት ቤተክርስቲያን ሀላፊ ቁርአንን በሜዲያ ፊት በማቃጠል አንድ ሰሞን ዝነኛ ሆኖ ነበር። በዚህ ብልግናው ያገኘውን ዝነኝነት ቤተክርስትያኑን ለማስተዋወቅ ተጠቅሞበታል።
እንዲህ ዓይነት እብዶች በሚያገጥሙን ሰአት የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ ያስፈልጋል፦
1- ብልግናን በብልግና አለመመለስ፣
2- ግለሰቡን ብቻ ነጥሎ መተቸች፤ ከሀይማኖት ወይም ብሄር ጅምላ ፍረጃ መጠንቀቅ፣
3- ጉዳዩን ወደህግ መውሰድ፣ ሂደቱን ሳይሰለቹ በመከታተልና ለውጤት በማብቃት ለሌሎች አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንዲያገኝ መስራት፤
3- ብልግና የሚረጭባቸውን ሜዲያዎች ተረባርቦ በማዘጋት በጋጠወጥነት ሊሸምተው የፈለገውን ዝናና ገንዘብ ማሳጣት፤
4- የተነሱ ብዥታዎች ካሉ በዕውቀት ብርሀን ማምከን፣
5- የዕምነት ወገኖቹ ይህን ብልግና በግልጽ በማውገዝና ባለጌ ልጃቸውን ከራሳቸው በመነጠል ከነውሩ ራሳቸውን ማጽዳት ይጠበቅባቸዋል።
ከዚህ ውጭ ሙስሊሞችን በማበሳጨት ዝነኛ መሆን ለሚሹ አካላት ፍላጎት ማሳኪያ ግብአት ላለመሆን መጠንቀቅ ያሻል።
በመጨረሻም ዕውነትን በሀሰትና በስድብ መሸፈን አይቻልም። ከአሁን በፊት እነአቡጀህል ሞክረው ከስረውበታል። ብዙዎች ተፍጨርጭረው ወድቀውበታል። የጸሀይን ብርሀን በሰፌድ ለመካተር መሞከር ከንቱ ድካም ነው። ወደላይ የተፋ አክታው ተመልሶ የሚያቆሽሸው ራሱን ነው። 'ኢነሻኒአከ ሁወል አብተር!!!'
ለተጨማሪ መልዕክት የቴሌግራም ቻነሌን ይከታተሉ።
https://t.me/hassentaju