ላለፉት 14 ክፍለ ዘመናት የኖሩ ዑለሞቻችን ለሰይድ ዑመር የ20 ረከዐ ተራዊህ ይህን ያህል ክብደት የሰጡትና ከርሱ መጨመርን ወይም መቀነስን በግልጽ ባይከለክሉም በጥርጣሬ ዓይን እንዲያዩ ያደረጋቸዉ ስለኹለፋኡ ራሽዲን ባጠቃላይና ስለሰይድ ዑመር በተለይ የተነገሩ የሀዲስ ዘገባዎች፣ሀሳባቸዉ ከአላህ ፍላጎት ጋር አብዝቶ መግጠሙ፣እንዲሁም የሶሀቦች ስምምነት በሸሪዐዉ ያለዉ ክብደት እንደሆነ ዕሙን ነዉ፡፡ ይኸዉም፡-
1. የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በአንድ ሀዲሳቸዉ የሚከተለዉን ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡-
فَعَليْكُمْ بسُنَّتِي وسُنَّةِ الخُلَفاءِ الرَّاشِدِينَ المَهْدِيِيِّنَ عَضُّوا عَلَيْهَا بالنَّواجِذِ
‹‹አደራችሁን፣የኔንና ቅኑን ጎዳና የተከተሉትን ቅን ኸሊፋዎች (ኹለፋኡ ራሽዲን) ሱናዎች ተከተሉ፤አጥብቃችሁም ያዟቸዉ፤››[i]
ኹለፋኡ ራሽዲን የሚባሉት በዋነኛነት አቡበክር፣ዑመር፣ዑስማንና ዐሊ መሆናቸዉ ይታወቃል፡፡[ii] ይህ ሀዲስ ሶሂህ ነዉ፤ ስለትርጉሙ ከተሰጡ ማብራሪያዎች፡-
إن سنة الخلفاء والطريقة المسلوكة عنهم أيضاً سنة وليس ببدعة ، وقيل : إن سنة الخلفاء في الواقع سنة النبي - صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - وإنما ظهرت على أيديهم
‹‹የኹለፋኡ ራሽዲን ሱናና የአስተሳሰብ /የትግበራ/ መንገድም እንደዚሁ ሱና እንጅ ቢድዐ አይደለም፤‹በነርሱ እጅ ይፋ ስለሆነ እንጅ የነብዩ የራሳቸዉሱና ነዉ› ተብሏልም፤››[iii]
በሙሀመዳዊዉ ድንቅ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ከታላቁ መምህር ﷺ ሥር ለዓመታት ተኮትኩተዉ ለፍሬ ከበቁት አራቱ ኸሊፋዎች በላይ የሸሪዐዉን ይዘትና መንፈስ ሊረዳ ሚችል ሌላ ሰዉ እንደሌለ ዕሙን ነዉ፡፡ ከላይ የሰፈሩ የወለላዉ ነቢ ﷺ ምስክርነት ይህንኑ ያረጋግጣል፡፡ ለሀዲሱ የተሰጠዉ ማብራሪያ ደግሞ የኹለፋኡራሽዲን ሱና በእርግጠኝነት በነርሱ እጅ የተገለጸ ወይም በአንደበታቸዉ የተነገረ የነብዩ ﷺ ሱና መሆኑን ያስረግጣል፡፡ ነብዩ ‹ሱናቸዉን ተከተሉ› ሲሉ ‹ቃላቸዉ ቃሌ፣ተግባራቸዉ ተግባሬ ነዉ› በማለት በነርሱ ላይ ያላቸዉን መተማመን እየገለጹ ነዉ፡፡ ስለዚህ የሰይድ ዑመርን ትዕዛዝ መተግበር የነብዩን ﷺ ትዕዛዝ ከመተግበር አይተናነስም። በዚህ ትንታኔ አግባብ የተራዊህ 20 ረከዐ በሰይድ ዑመር የተገለጸ የነብዩ ﷺ ሱና ነዉ ማለት ይቻላል፡፡ የሶሀቦች ሙሉ ስምምነት (ኢጅማዕ) ይህን ፍሬ ነገር ከመረዳት የመነጨ ይመስላል፡፡ የተራዊህ 20 ረከዐ አሀዝ በዑለሞች እንዲህ ክብደት ተችሮት አራቱም መዝሀቦች የጸናዉም ለዚሁ ነዉ፡፡ የያዝነዉን ርዕሰ ጉዳይ በስምምነት ለመዝጋት ይህ ሀዲስ ብቻ በቂ ቢሆንም ሌሎች ተጨማሪ ዘገባዎችን አነሆ፤
2. በሊቃዉንት የሀሰን ደረጃ የተሰጠዉ ተከታዩ ሀዲስም የላይኛዉን ሀሳብ ያጸናል፡-
اقتدوا باللذين من بعدي أبي بكر وعمر
‹‹እኔን የሚተኩትን አቡበክርንና ዑመርን ተከተሉ፤››[iv]
ይህ ሀዲስ ከኹለፋኡ ራሺዲን መካከል የሰይድ አቡበክርንና የሰይድ ዑመርን ፈለግ በተለየ ሁኔታ መከተልን ያሰምርበታል፡፡ 20 ረከዐ ተራዊህ በሰይድ ዑመር አማካይነት የተገለጸ ሱና መሆኑ በዚህ ሀዲስ ብርሀን የበለጠ ክብደት እንድንቸረዉ ያደርገናል፡፡
3. ሰይድ ዑመር ‹‹አልፋሩቅ›› በሚል ቅጽል ስም ይታወቃሉ- ዕዉነትን ከሀሰት የሚለዩ ማለት ነዉ፡፡ በእስልምና ወሳኝ የታሪክ እርከን ላይ አላህ እርሳቸዉን በማስለም ዕዉነትን ከሀሰት ለይቷል፡፡ ሲሰልሙ አርባኛ ሙስሊም ነበሩ፡፡ በስድስተኛዉ ዓመተ ‹ሪሳላ› መሆኑ ነዉ፡፡ ከርሳቸዉ መስለም በፊት ሙስሊሞች ጥቃት እንዳይበረታባቸዉ ለመጠንቀቅ ሲባል ሀይማኖታቸዉን በድብቅ ለማከናወን ተገደዉ ነበር፡፡ ሰይድ ዑመር ሲሰልሙ ግን ይህ ሁኔታ በቅጽበት ተቀየረ፡፡ ሙስሊሞች ከፍተኛ ጉልበት አገኙ፡፡ ይፋ ለመዉጣትም ተደፋፈሩ፡፡ የአላህ መልዕክተኛም ﷺ በሶሂህ ሀዲስ ስለሰይድ ዑመር እንዲህ መስክረዋል፡-
إِنَّ الله تَعَالَى جَعَلَ الْحَقَّ عَلَى لِسَانِ عُمَرَ وَقَلْبِهُ
‹‹አላህ በዑመር አንደበትና ልቦና ላይ ዕዉነትን አኑሯለወ፤››[v]
ከባድ ምስክርነት ነዉ፤ሰይዱል በሸር ﷺ በኒህ ተማሪያቸዉ ቃልና ተግባር ብቻ ሳይሆን በቀልባቸዉ በሚያስቡት ነገር ሳይቀር ምን ያህል ይተማመኑ እንደነበር ያሳያል፡፡ ‹ዑመር የሚናገሩትና የሚያስቡት ሁሉ ሀቅ ስለሆነ ተቀበሉት›› ማለት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ስለዚህ የተራዊህ ረከዐዎች ቁጥር 20 መሆኑ ዕዉነት እንጅ ሌላ ከማይናገር አንደበት፣ዕዉነት እንጅ ሌላ ከማይቋጥር ልቦና የመነጨ ስለሆነ ዕዉነትነቱ ከጥያቄ ዉስጥ የሚገባ አይደለም።
4. ሰይድ ዑመር ‹‹ሙልሀም›› /አላህ ፍላጎቱን ከልቦናቸዉ ዉስጥ ከሚያሳድርላቸዉ ሰዎች መካከል አንዱ/ መሆናቸዉ በዓለማት ዕዝነት ﷺ አንደበት ተመስክሮላቸዋልበ፡-
لَقَدْ كَانَ فِيمَنْ قَبْلَكُمْ مِنَ الأُمَمِ مُحَدَّثُونَ – أَيْ مُلْهَمُونَ – فَإِنْ يَكُنْ فِي أُمَّتِي أَحَدٌ فَإِنَّهُ عُمَرُ
‹‹ከናንተ በፊት ከነበሩ ሕዝቦች ዉስጥ ‹ሙልሀም› ስብእናዎች ነበሩ፤በኔ ኡመት ዉስጥ ‹ሙልሀም› ስብዕና ካለ ያ ስብዕና ሊሆን የሚችለዉ ዑመር ነዉ፤››[vi]
5. ሰይድ ዑመር እንዲህ ዓይነት የታደሉ ስብዕና ስለነበሩ ቁርአን ለበርካታ ጊዜ የርሳቸዉን ሀሳብ ደግፎ ወርዷል፡፡ አል-ፋሩቅ ራሳቸዉ የተወሰኑ አጋጣሚዎችን እንዲህ ተርከዉልናል፡-
وافقتُ ربِّي في ثلاث: في مقام إبراهيم، وفي الحجاب، وفي أَساري بدر، قلت: يارسول الله، لو اتخذنا من مقام إبراهيم مصلَّى؟ فنزلت: "وَاتَّخِذُوا مِنْ مَقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلَّى". وقلت: يارسول الله، إن نساءك يدخل عليهنَّ البرُّ والفاجرُ، فلو أَمرتَهُنَّ أَن يَحَتَجِبْن؟ فنزلت الآية الحجاب: "وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَاعاً فَاسْأَلُوهُنَّ مِنْ وَرَاءِ حِجَاب". واجتمع نساء النبي r عليه في الغَيْرة، فقلت: " عسى ربُّه إن طلقكنَّ أَن يبدله أَزواجاً خيراً منكن" فنزلت كذلك
‹‹በሶስት ጉዳዮች ሀሳቦቼ ከጌታየ ፍላጎቶች ጋር ተገጣጥመዋል፤በመቃመ ኢብራሂም፣በሂጃብና በበድር ምርኮኞች ጉዳይ፡፡ ‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ፣መቃመ ኢብራሂምን የመስገጃ ቦታ አድርገዉ ለምን አይዙም?› በማለት ጠየቅኳቸዉ፤ ወዲያዉኑ ‹መቃመ ኢብራሂምን የመስገጃ ቦታ አድርጋችሁ ያዙ› የሚል የቁርአን አንቀጽ ወረደ፡፡[vii] ‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ፣ደግም ክፉም ሰዎች ባለቤቶችዎ ወዳሉባቸዉ ጓዳዎች ስለሚገቡ መከለያ ግርዶ (ሂጃብ) እንዲያደርጉ ቢያዟቸዉስ?› በማለት ጠየቅኩ፤ወዲያዉኑ ‹‹አንዳች ነገር ስትጠይቁ ከመጋረጃ ጀርባ ጠይቋቸዉ› የምትለዉ ሂጃብን ግድ የምታደርገዉ የቁርአን አንቀጽ ወረደች፡፡[viii] ባለቤቶቻቸዉ ባደሙባቸዉ ጊዜ ‹እርሳቸዉ ከፈቷችሁ አምላካቸዉ ከናንተ የተሸሉ ሚስቶችን ይተካላቸዋል› በማለት ገሰጽኳቸዉ፡፡ እንደዚሁ የምትል የቁርአን አንቀጽ[ix] ወረደች፡፡››[x]
ቲርሚዚ ‹ሀሰን› በሆነ ሰነድ እንደዘገቡት ዐብደላህ እብን ዑመር እንዲህ ብለዋል፡-