Фильтр публикаций




"ጠንካራ የስፖርት ምክር ቤት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና!" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ 15ኛ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂደናል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የከተማችንን የስፖርት እድገት ለማረጋገጥ እንዲሁም በአካል እና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለመገንባት በርካታ ስራዎች የሰራን ሲሆን፣ በከተማችን 1,314 የህፃናት እና ወጣቶች የመጫዎቻ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት አብቅተናል።

ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት በ11ዱም ክፍለ ከተሞቻችን 128 የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና መርሃ-ግብሮችን ከፍተን በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን፣ ማህበረሰባችን የስፖርትን ጥቅም ተረድቶ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
@subitime


ዛሬ ማለዳ በልደታ ክፍለከተማ በመሰረትነው የበጎነት መንደር ውስጥ በመገንባት ላይ ያሉ ተጨማሪ ሁለት ባለ 9 ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተመልክተናል።
በበጎነት የመኖሪያ መንደር እስካሁን ሰባት የመኖሪያ ህንጻዎች ተጠናቅቀው ለልማት ተነሺዎች እና የኑሮ ጫና ላለባቸው የከተማችን ነዋሪዎች የተላለፉ ሲሆን፣ በመኖሪያ መንደሩ ለሚገኙ ነዋሪዎቻችን የእንጀራ ፋብሪካን ጨምሮ ልዩ ልዩ የስራ እድል ፈጥረንላቸዋል።

በከተማ አስተዳደሩ እና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ትብብር እየተገነቡ የሚገኙትን ሁለት ባለ 9 ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች የምናስተላልፍ ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
@
subitime


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ለከተማዋ ልማት ጉልህ ፋይዳ ያላቸው አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

የጸደቁ አጀንዳዎች:-

1ኛ. የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጤና፣ ፅዳት እና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ መሆኑን በማረጋገጥ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

2ኛ. በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፣ አፈፃፀም ቁጥጥር እና ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በመወያየት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

3ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ መርምሮ በጥልቅ በመወያየት በመንግስት እና የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ እና በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ

4ኛ. በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ

5ኛ. ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
@subitime


"እኛ ኢትዮጲያዊያን እንድንበታተን ሳይሆን አብረን እንድንኖር የተፈረደብን ህዝቦች ነን::"
"ኢትዮጲያን ካለ ብሔረሰቦቿ ብሔረሰቦቿን ያለ ኢትዮጲያ ማሰብ አይቻልም ::"
ዩሱፍ ያሲን (ሀሰን ኡመር አብደላ)
ኢትዮጲያዊነት አሰባሳቢ ማንነት በአንድ ሀገር ልጅነት
ህዳር 2009

መነበብ ያለበት ድንቅ መፅሀፍ
@subitime


ዛሬ በኢትዮዽያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ቼይ ሃይ እና ከሲጂሲኦሲ ግሩፕ (CGCOC group) በተገኙበት የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን በፍጥነት ማስጀመር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ጋር ተወያይተናል::

የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት በ2008 ዓ.ም ከኤግዚም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ይገነባል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም ብድሩ እስከ ዛሬ ባለመለቀቁ ምክንያት ሳይጀመር በመዘግየቱ ከተማው አስተዳደር በራሱ በጀት ለመገንባት ወስኗል ።

በከተማዋ ያለውን የውሃ ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም የከተማ አስተዳደሩ በራሱ በጀት ለመገንባት ዛሬ ከቻይና ኤምባሲ እና ከ‍ኮንትራክተሩ ሲጂሲኦሲ ግሩፕ ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል::

የከተማችንን የውሃ አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ ከፍተኛ በጀት
መድበን በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን የገርቢ መጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታም ሲጠናቀቅ ይህንን ጥረታችንን ይበልጥ ውጤታማ እንደ ሚያደርግ እና ያለብንን የውሃ ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ይበልጥ እንደሚፈታ እናምናለን::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
@subitime


ዛሬ የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደርን መርቀን ከካዛንቺስ በልማት ለተነሱ ነዋሪዎቻችን አስረክበናል።

የኢትዮጵያ መልክ የሆነችው አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ በገባነው ቃል መሰረት፣ መሰረተ ልማት ከማሟላት በተጨማሪ የሰው አኗኗርን ማሻሻል እና የነዋሪዎቻችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ትኩረት ሰጥተን በመስራት ላይ እንገኛለን።

ነዋሪዎቻችንን ካረጀ እና ለመኖር ምቹ ካልሆነ የካዛንቺስ አካባቢ እንዲወጡ አድርገን ለኑሮ ምቹ የሆነ ቤት እና አካባቢ እንዲገቡ ያደረግን ሲሆን በዚህም የሰው ህይወትን የመቀየር ስራን ሰርተናል።
ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት በፈቃደኝነት የተነሳችሁ እና ከጎናችን የቆማችሁ ነዋሪዎችን ስለ ትዕግስታችሁ እና ድጋፋችሁ እያመሰገንኩ፣ ይህ ስራ እንዲሳካ ህግ እና አሰራሩን በመቀበል ቦታውን በፈቃደኝነት ለልማት የለቀቃችሁ የአካባቢው አርሶ አደሮችንም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

ይህን ታላቅ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብታችሁ ያጠናቀቃችሁ ኮንትራክተሮችን፣ አማካሪ ድርጅቶችን፣ ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላትን፣ ያስተባበራችሁ አመራሮችን እንዲሁም የክፍለከተማው አመራሮችን በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
@subitime


በትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ድርጊት በፈጸሙ የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ::

በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ድርጊት በፈጸሙ የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በሰጡት መግለጫ፥ የፔንሲዮን ቤቶችን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ድርጊት በፈጸሙ 879 የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል።

በዚህም አዋኪ ድርጊት በፈፈሙ በ184 ጫትና ሺሻ ቤቶች፣ 112 አረቄ ቤቶች፣ ግሮሰሪ መጠጥ ቤቶች 48፣ 12 ፔንሲዮን ቤቶች፣ 120 ፑል ቤቶች፣ የድምፅ ብክለት ያለባቸው ሙዚቃ ቤቶችና ቪዲዮ ቤቶች 122 እንዲሁም 171 ሌሎች የንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ነው የተገለፀው።

እርምጃ የተወሰደው በሁሉም ትምህርት ቤቶች ያለውን የመማር ማስተማር ሂደት ሰላማዊ ለማድረግ እንደሆነምየአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል ።

እርምጃ የተወሰደው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከትምህርት ቢሮ፣ ንግድ ቢሮ፣ ፓሊስና ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር የጋራ ግብረ ሃይል በማቋቋም በጥናትን ላይ መሠረት በማድረግ የተወሰደ እርምጃ እንደሆነም ተገልፃል።
@subitime


ዛሬ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካንዚም አዳራሽ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ባማረና በደመቀ ሁኔታ አክብረናል።

በበዓሉ ላይ የተከበሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና የሁሉም ክልሎች አፈ ጉባኤዎች የተገኙ ሲሆን፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ቤት፣ የኢትዮጵያውያን ሁሉ መናገሻ፣ የአፍሪካ ህብረት መዲና እና ሶስተኛዋ የዓለም ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባችን የህብረብሄራዊ አንድነታችን ተምሳሌት መሆኗን በሚመጥን ልክ ተከብሯል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
@subitime



Показано 10 последних публикаций.