የማይቆጨኝ 2ኛ እድል
( ሱመያ ሱልጣን)
ለተከፋሁበት ሰው 2ኛ እድል ከማይሰጡት ነኝ። ልከፋ የምችለው እጅግ በቀረብኩት ሰው ስለሆነ ላጣው አካባቢ ላለማጣት የምከፍለውን ያህል ለ 2ኛ እድል እጄ አይዘረጋም።
የምወዳት ጓደኛ ነበረችኝ። ሃይስኩል ነበርን። ገና ሁሉ ነገር ብርቅ የሆነብን ሰዓት። እና የሆነ ቀን ላይ ይሄ ለወጣትነት አዲስ መሆን አለያየን። የመከፋቴን ጥግ አልረሳውም ክፍሌ ውስጥ እንዳልታይ አንዱ ክፍል ላይ ጥግ ሄጄ እስከማልቀስ ነበር። የ "አይጎዳ" መጸዳጃ ቤቶች እንባዬ እስኪያጥባቸው። ከዛ ከልቤ ለረጅም ጊዜ አስወጣኋት። አንድ ቀን የ እድሜያችን ግርግር ሲያበቃ ድጋሚ ተፈላለግን እና "ይቅርታ" ም ባልነበረው እርቅ አብረን ቀጠልን። አሁን ላይ ዱንያ ላይ ካሉኝ ኒዕማዎች ውስጥ "እሷ" አንድ ብዬ ከምቆጥራት ናት። አለ አይደል የሆነ ቦታ ስትሄዱ ብቻውን የማይዘንጥ ሰው ፣ ይሄ የሰርጋችሁ ወይም የናንተ ፕሮግራም ላይ ራሱን የማያደምቅ እና ከናንተ በላይ የሚጨነቅ ሰው፣ ልክ ቤተሰቦቻችሁ እነሱን ሲያዩ ልባቸው የሚያርፍባቸው ሰዎች። እንደዛ ናት ለኔ።
እና ከሰሞኑ ለ 2 እና 3ወር አካባቢ በሆነ ድብርት ውስጥ ገብቼ ተደበቅኳት። መውደቄ ስለሚሰብራት አፍራታለሁ። ዛሬ ምንም እንኳን ከድብርቴ ባልወጣም የናፍቆቴን ጻፍኩላትና "ህይወት ላይ ስወድቅ እኮ ስለማፍርሽ ነው" ብዬ አልኳት።
"አብረን መውደቅ እንችላለን እኮ። ካልሞትኩ በስተቀር እኮ ሁሌም ላንቺ አለሁ እኮ ምንም ቢፈጠር" አለችኝ።
ወላሂ 3 ጊዜ ህይወት ላይ አሸነፍኩ። አንድ ስተዋውቃት፣ 2ኛ ድጋሚ እድል ሥሰጣት እና 3ኛው በምንም ሁኔታ ውስጥ እንዳለችኝ ምዬ መናገር ስለምችል።
@sumeyasu
@sumeyaabot