~ዝሆን ሁለት ጥርሶቹ ጎልተው ስለሚታዩ ሌሎች ጥርሶች የሉትም ማለት አይደለም። እነዚህ ጎልተው የሚታዩት ጥርሶች ውበቱ ወይም ግርማ ሞገሱ ናቸው። በዛውም ልክ የጥቃት ሰለባ ያደርጉታል። ፈገግታችንን ብቻ ስለሚያዩ የማይከፋን ለሚመስላቸው፣ ስለማንጨናነቅ ቁም ነገር የማናውቅ ለሚመስላቸው፣ መልካም ብለው ባሉት ቦታ ስለማያገኙን እርባና ቢስ ለምንመስላቸው ሰዎች አቅል ይስጥልን። ሁለት ጥርስ ብቻ ሁሌ አትመልከቱ ሌሎች ከ20 በላይ ጥርሶች አሉ። ሳቆቻችን የሚሸሽጉትንን ለመመልከት ሰፋ በሉ። ከምናሳያችሁ የበለጠ የምናሳይበትን ምክንያት ተረዱ።