....ሐሜት አይገድለውም!
--------------------
የሰው መንገዱ መች ይታወቃል፡
ጀመርኩት ያለው ድንገት ያበቃል፡
ህይወት እንድህ ነው ብቻ ይደንቃል፡
አመለጠኝ ሲል ይገባል በእጁ፡
ሀዘን ያጠላው ይደምቃል ደጁ፡
ጠልፎት ይቆማል ታማኝ ወዳጁ፡
...አይ ህይወት.......
አጠፋኝ ያለው ህይወት ይዘራል፡
ማር የተባለው ከሬት ይመራል፡
ብቻ ስንቱ ግፍ ምኑ ይወራል፡
የሰው ልጅ ሆዱ አይታወቅም፡
የሳቀ ሁሉ ደስታን አያውቅም፡
አታነጋግሩኝ የለውም ጥቅም፡
ዛሬን ብታጣ በመከራ ዶፍ ብትወገርም፡
ነገ ተስፋ አለህ ወድቀህ አትቀርም፡
መጥፎ ጠባሳ በቃል አትፈርም፡
የያዝከው ቢበን ያለምከው ጠፍቶ፡
ሁሉ ባይመች ችግሩ ከፍቶ፡
ሆድህ ባይሞላ ከአለም ሰፍቶ፡
የማያልፍ የለም አይዞህ ከቶ፡
የሰው መንገዱ መች ይታወቃል፡
የጌታ ሚስጥር በጣም ይደንቃል፡
አሏህ ሲፈቅድ ቃሉ ይበቃል፡
የሰው ልጅ ፕላን አይታወቅም፡
ነገ ይነሳል ዛሬ ቢወድቅም፡
ይህንን እውነት አትጠይቅም!?
.....ለማንኛውም....!!
እንኳን ውስን ጠላት አለም ቢሰባሰብ፡
ያልሆንኩት ቢወራ ክፋትን በማሰብ፡
ቢያጥላሉኝ ቢያገሉኝ ከማህበረሰብ፡
የሌለኝ ማንነት ስም ሆኖ ቢለጠፍ፡
እኔን ለማነወር ማንም ቢተጣጠፍ፡
ውሸት ቢሸመጠጥ ነገር ቢቀረጠፍ፡
ምንም ለጠላቴ ይህ ባይዋጠውም፡
ስኬት ላይ እስክደርስ መጓዜን አይተውም፡
ሰውን በሽታ እንጅ ሐሜት አይገድለውም፡
https://t.me/tdarenatbebawikalatoch/7223
--------------------
የሰው መንገዱ መች ይታወቃል፡
ጀመርኩት ያለው ድንገት ያበቃል፡
ህይወት እንድህ ነው ብቻ ይደንቃል፡
አመለጠኝ ሲል ይገባል በእጁ፡
ሀዘን ያጠላው ይደምቃል ደጁ፡
ጠልፎት ይቆማል ታማኝ ወዳጁ፡
...አይ ህይወት.......
አጠፋኝ ያለው ህይወት ይዘራል፡
ማር የተባለው ከሬት ይመራል፡
ብቻ ስንቱ ግፍ ምኑ ይወራል፡
የሰው ልጅ ሆዱ አይታወቅም፡
የሳቀ ሁሉ ደስታን አያውቅም፡
አታነጋግሩኝ የለውም ጥቅም፡
ዛሬን ብታጣ በመከራ ዶፍ ብትወገርም፡
ነገ ተስፋ አለህ ወድቀህ አትቀርም፡
መጥፎ ጠባሳ በቃል አትፈርም፡
የያዝከው ቢበን ያለምከው ጠፍቶ፡
ሁሉ ባይመች ችግሩ ከፍቶ፡
ሆድህ ባይሞላ ከአለም ሰፍቶ፡
የማያልፍ የለም አይዞህ ከቶ፡
የሰው መንገዱ መች ይታወቃል፡
የጌታ ሚስጥር በጣም ይደንቃል፡
አሏህ ሲፈቅድ ቃሉ ይበቃል፡
የሰው ልጅ ፕላን አይታወቅም፡
ነገ ይነሳል ዛሬ ቢወድቅም፡
ይህንን እውነት አትጠይቅም!?
.....ለማንኛውም....!!
እንኳን ውስን ጠላት አለም ቢሰባሰብ፡
ያልሆንኩት ቢወራ ክፋትን በማሰብ፡
ቢያጥላሉኝ ቢያገሉኝ ከማህበረሰብ፡
የሌለኝ ማንነት ስም ሆኖ ቢለጠፍ፡
እኔን ለማነወር ማንም ቢተጣጠፍ፡
ውሸት ቢሸመጠጥ ነገር ቢቀረጠፍ፡
ምንም ለጠላቴ ይህ ባይዋጠውም፡
ስኬት ላይ እስክደርስ መጓዜን አይተውም፡
ሰውን በሽታ እንጅ ሐሜት አይገድለውም፡
https://t.me/tdarenatbebawikalatoch/7223