«ጓደኝነት»
እጂግ ረቂቅ ነውና፤
የሰወች የኛ ፍጥረት፡
ጣዕሙ ጓደኝነት ነው፤
ለስኬትም ሆነ ለጥረት፡
እውነተኛ ወዳጅነት፤
ሁሌም የለውም ክስረት፡
መከራ በመጣ ቁጥር፤
ይበልጥ ይፀናል ከብረት፡
በተውሒድ ላይ ተገንብቶ፤
ሱና ላይ ሲመሰረት፡
ጓደኝነት
ችግሩ ነገረኛ አለ፤
ከወዳ ወድህ አዋቃሽ፡
ምቀኛና በሽተኛ፤
የአዞወችን እንባ አልቃሽ፡
ያለ የሌለን የሚቀባጥር፤
ጥላቻና ቂምን ቀስቃሽ፡
በአይን ያየኸውን እመን፤
ከአይን በላይ ጆሮ አትጠቀም፡
ጓደኝነታችን ይፈርሳል፤
ከማንም ነገር አትልቀም፡
እስካሁን አብረን ስንኖር፤
ሲፈራረቁ ዘመናቶች፡
ጥምረታችን የሚያበሽቃቸው፤
ብዙ ናቸው በርካቶች፡
በነዚያ ሁሉ ዘመናት፤
በጧትም ሆነ በማታም፡
እኛን ለማጠራጠር፤
ሲለፉ አይተናል ቅናታም፡
ንግግር ሲበዛ ቢመርም፤
ይሰለቻል ሁሌ ዝምታም፡
.....በጣም ዝም አትበል.....!!
ባሳለፍናቸው ጊዜወች፤
ለአንተ ቦታ ሲኖረኝ፡
ውደታህን አንተ ሳቶን፤
ሰው ነበር ሰምቶ እሚነግረኝ፡
ምን ያህል እንደም'ጠላኝ፤
ምን ያህል እንደም'ቶደኝ ፡
ሰው ነው እየነገረ ፤
የሚያስደስት የሚያናድደኝ፡
ይህ ነው የኛ በሽታ፤
በጓደኝነታችን መካከል፡
ጓደኝነቱን ከፈለከው ፤
ይህ ተግባራችን ይስተካከል፡
ጓደኛዬ ካልከኝ በኋላ፤
በሰው አታስመርምረኝ፡
ጥፋት ስትመለከት፤
ቀጥታ መጥተህ አናግረኝ፡
በዚህች ጊዜያዊ ጎጆ፤
ዱንያ በምትባል ሀገር፡
ወዳና ወድህ የሚለው፤
ይገርመኛል የሰው ነገር፡
ለሁለት አለም ተብሎ፤
ሲወ'ጠን በእውነተኝነት፡
በማንም ወሬ አይፈርስም፤
ውጥኑም አይደፈርስም ረቂቅ ነው ጓደኝነት፡
https://t.me/tdarenatbebawikalatoch/7267
እጂግ ረቂቅ ነውና፤
የሰወች የኛ ፍጥረት፡
ጣዕሙ ጓደኝነት ነው፤
ለስኬትም ሆነ ለጥረት፡
እውነተኛ ወዳጅነት፤
ሁሌም የለውም ክስረት፡
መከራ በመጣ ቁጥር፤
ይበልጥ ይፀናል ከብረት፡
በተውሒድ ላይ ተገንብቶ፤
ሱና ላይ ሲመሰረት፡
ጓደኝነት
ችግሩ ነገረኛ አለ፤
ከወዳ ወድህ አዋቃሽ፡
ምቀኛና በሽተኛ፤
የአዞወችን እንባ አልቃሽ፡
ያለ የሌለን የሚቀባጥር፤
ጥላቻና ቂምን ቀስቃሽ፡
በአይን ያየኸውን እመን፤
ከአይን በላይ ጆሮ አትጠቀም፡
ጓደኝነታችን ይፈርሳል፤
ከማንም ነገር አትልቀም፡
እስካሁን አብረን ስንኖር፤
ሲፈራረቁ ዘመናቶች፡
ጥምረታችን የሚያበሽቃቸው፤
ብዙ ናቸው በርካቶች፡
በነዚያ ሁሉ ዘመናት፤
በጧትም ሆነ በማታም፡
እኛን ለማጠራጠር፤
ሲለፉ አይተናል ቅናታም፡
ንግግር ሲበዛ ቢመርም፤
ይሰለቻል ሁሌ ዝምታም፡
.....በጣም ዝም አትበል.....!!
ባሳለፍናቸው ጊዜወች፤
ለአንተ ቦታ ሲኖረኝ፡
ውደታህን አንተ ሳቶን፤
ሰው ነበር ሰምቶ እሚነግረኝ፡
ምን ያህል እንደም'ጠላኝ፤
ምን ያህል እንደም'ቶደኝ ፡
ሰው ነው እየነገረ ፤
የሚያስደስት የሚያናድደኝ፡
ይህ ነው የኛ በሽታ፤
በጓደኝነታችን መካከል፡
ጓደኝነቱን ከፈለከው ፤
ይህ ተግባራችን ይስተካከል፡
ጓደኛዬ ካልከኝ በኋላ፤
በሰው አታስመርምረኝ፡
ጥፋት ስትመለከት፤
ቀጥታ መጥተህ አናግረኝ፡
በዚህች ጊዜያዊ ጎጆ፤
ዱንያ በምትባል ሀገር፡
ወዳና ወድህ የሚለው፤
ይገርመኛል የሰው ነገር፡
ለሁለት አለም ተብሎ፤
ሲወ'ጠን በእውነተኝነት፡
በማንም ወሬ አይፈርስም፤
ውጥኑም አይደፈርስም ረቂቅ ነው ጓደኝነት፡
https://t.me/tdarenatbebawikalatoch/7267