የትውልዱን የባህር ማዶ ሙዚቃ መላመድ በጥበባዊ አይኖቹ አሻግሮ የተመለከተው ወጣት አሰልቺ እና ድግግሞሽ የሚስተዋልበትን "ቺግቺጋ" የተሰኘውን የአገሩን የሙዚቃ ሥልት እንደ ሞገደኛ ምሁር ፈነቃቅሎ ሳያፈራርሰው በዘዴ እና በጥበብ ከ ባህርማዶዎቹ "ሬጌ"፣ "ሮክ ኤን ሮል" እና "ፖፕ" ሙዚቃ ስልቶች ጋራ ተጣጥሞ የሚሄድበትን መንገድ እንደ አንዳንዶቹ ተስፈኞች ባሕር ማዶ መሻገር ሳያስፈልገው ደጁን ቆልፎ በመለማመድ እና ተፈጥሮ ያደለችውን የሙዚቃ ምትሃት እንደዛር በላዩ ላይ እና በተከታዮቹ ላይ በማውረድ ላለፉት ሃያ ዓመት በመደነቅ ስሜት ውስጥ የሰማናቸውን ጊዜ አይሽሬ ሙዚቃዎች አበርክቶልናል።