📍በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።
📍መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል። ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። በአጋጣሚ ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።
📍ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።
💎ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም።
ሁሉንም ክብርና ምስጋና የፈጠረን ይውሰድ።
📖አርምሞ
ወብ አዳር ❤️
@telemondo