Day 7
ሰዎች የቤት፣ የተሽከርካሪ፣ የሕይወት፣ ወዘተ. . . ዋስትና በመግዛት ለሚደርስባቸው አደጋ ተመጣጣኝ ካሳ ለማግኘት ይሞክራሉ። በተለይ የሕይወት ዋስትና የገዙ ሰዎች አደጋ አጋጥሟቸው ሕይወታቸው ሲያልፍ፥ ይህ የገዙት ዋስትና ከሞት በኋላ ሊያግዛቸው ስለማይችል፥ ካሳው ለቤተሰባቸው ይከፈላል። ከዚህ የተሻለ የሕይወት ዋስትና እንዳለ ያውቁ ኖሯል? ከሞት ስለሚሻገረውና ለዘላለም ዘላቂ ስለሆነው ዋስትና ሰምተዋል? ይህንን ዋስትና የያዘ ሰው ለዘላለም ከአምላኩ ጋር በደስታ መኖር ይችላል። ይህ የሕይወት ዋስትና በከብቶች በረት የተወለደው፣ ፍጹም ሰው፡ ፍጹም አምላክ የኾነው፣ ስለ ሰው ልጆች ኹሉ ኃጢአት በመስቀል ላይ የሞተው፥ በሦስተኛውም ቀን ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው፣ ወደ ሰማይ ያረገው፣ ዳግመኛም ተመልሶ የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዘላለማዊ የሕይወት ዋስትና የሚገኘው ርሱን በማመን ብቻ ነው። ሌሎች ዋስትናዎች በሙሉ እስከሞት ድረስ ተጎጂውን ለማገዝ ይጥራሉ። ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኘው ዘላለማዊ ዋስትና ግን አሁንም ከሞት በኋላም ለዘላለም አስተማማኝ ነው። ዛሬውኑ ፈጥነው ይህንን ዋስትና ይያዙ። ልናማክሮ እና ልንረዳዎ ዝግጁ ነን!
#ኑ_ወደ_ኢየሱስ
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ
Follow Meskerem Getu on:
Facebook | Instagram | TikTok | Threads
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest

“እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማና በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እርሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ስለ ሆነ አይፈረድበትም።” (የዮሐንስ ወንጌል 5:24)