በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራዎች የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉና ችግር ፈቺ ሊሆኑ እንደሚገባ ተጠቆመ፡። (ታህሳስ 26/04/2017 ዓ.ም) ከ47 ዩኒቨርስቲዎች ለተውጣጡ የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተሮች ስልጠና ተሰጥቷል። በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተወካይ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሃንዲሶ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት የማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ፣ ሙያዊ ፣ ሳይንሳዊና ችግሮችንም በአግባቡ የሚፈቱ ሊሆን ይገባል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአካባቢያቸው ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫና የንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን በማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች የተቆጠረ ተከታታይነትና ወጥነት ያለው ውጤት እንዲመዘገብ በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ዶ/ር ሠራዊት ተናግረዋል፡፡
የማህበረሰብ ጉድኝት እና አገር በቀል እዉቀት ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ ሰላም አለሙ በበኩላቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚከናወኑ ቁልፍ ተልዕኮዎች መካከል የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራ አንደኛው መሆኑን አመልክተው ተቋማቱ የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ችግሮች እንዲቀረፉ በትጋት መስራትና የማህበራዊ ሀላፊነታውን መወጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል። የስልጠናው ዓላማም አሳሳቢ እየሆኑ በመጡና ተለይተው በተቀመጡ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም የአእምሮ ጤናና አደንዛዥ እጽ፣ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት፣ ህገወጥ ስደትና የሰዎች ዝውውር ላይ የምርምርና ግብዛቤ ፈጠራ ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል መሆኑን አመልክተዋል።። ተቋማቱ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ በአካባቢያቸው ያሉ ትምህርት ቤቶችን እንዲደግፉ ፣ የማህበረሰቡ ዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ግንዛቤ እንዲያሳዳድጉ እና እንዲያግዙ ማስቻልም ሌላኛው አላማ መሆኑን ጠቅሰዋል። በስልጠናው ላይ ሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተሮች የተሳተፉ ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከጤና ሚኒስቴር ፣ከመንገድ ደህንትና መድህን ፈንድ ፣ ከስደተኖች ጉዳይ አስተዳደር እና ከጅማ ዩኒቨርስቲ በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።