ለውብ ቀን!
💚
#ፍቅል
(መንግስቱ መርሃጽዮን)
ስጋ እወዳለሁ! ስጋ የሌለበት ምግብ ቅጠል ፣ ቅጠል ነው የሚለኝ! ግን ምን ያደርጋል የእኔ
ስጋ ወዳድነትና የስጋ ዋጋ አልገናኝ ብለው የስጋ አምሮቴን የማስታግሰው በወር ወይም
በሁለት ወር አንዴ ቢበዛ ሁለቴ ነው! በአሁኑ ግዜ ባለው የስጋ ዋጋ መናር የተነሳ ቁርጥ
አምሮኝ ልቆርጥ ቢለዋ አንስቼ ስገዘግዝ ለስጋው የከፈልኩት ዋጋ ስጋውን ሳይሆን ቢላው
ስጋዬን የሚቆርጠኝ ያህል እየተሰማኝ ነው። ሆኖም ግን ስጋ መብላት አላቆምኩም።
ደሞዝተኛ ነኝ! የግብርም፣ የግድብም፣ የበላሁት ብድርም ተቀናንሶለት የቤት ኪራይ ከፍዬ ፣
የታክሲ መድቤ፣ ለእናቴ ጡረታ ቆርጬ ለቀለቤና ለድራፍት የምትሆን ትንሽ ገንዘብ ነች
የምትተርፈኝ። ከእርሷ ላይ ደሞ ለስጋ ከተነሳላት .........።
ቅዳሜ ግማሽ ቀን ሰራለሁ። ዛሬ ግን ስብሰባ ስለነበር "በድፍን ቅል አይጥ ገባች" አይነት
ጉንጭ አልፋ ውይይት አይሉት ሙግት ስዳረቅ አርፍጄ ከቢሮ እንደወጣሁ ገና እኩለ ቀን
ሳይሆን የፀሀይዋ ግለት መሀል አናቴን እየፈጀኝ ቁጭ ብዬ ጫማዬን አስጠረግኩ።
ጫማ እድለኛ ነው! አርጅቶም፣ እንደኔ ባለ እግረኛ እግር ተረግጦም፣ በባለግዜዎች
ረግጦም ባጠቃላይ ረግጦም ሆነ ተረግጦ፣ አልያም ረጋግጦ ተወልውሎ ሲቀባባ ይወዛል።
ድህነትና ተስፋ ማጣት ያጎሳቆለው ፊት ግን ምን ቢቀባቡት አይወዛም። ችግሩ ጥልቅ ነዋ!
ህመሙ ከቆዳ ይጠልቃል! ጉዳቱ የነብስ ነው።
ከኮሌጅ ከተመረቅኩ ስንት ዓመት ሆነኝ? እሯ........! ሚስት ሳላገባ ፀጉሬ ገባ፣ አይኖቼን
ባይኔ ሳላይ በመነፅር ታገዘ፣ ። ምነው ግን ይህ ብሶት ቢቀርብኝ??
ከገባሁበት ሆቴል በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ በመታጠብ ያረጠብኴቸውን እጆቼን እያራገፍኩ
ክትፎ አዘዝኩ።
"ኖርማል፣ ስፔሻል?" አስተናጋጇ ጠየቀቺኝ
"ኖርማል፣ ኖርማል" አልኩ አስረግጬ
"ጥሬ፣ ለብለብ፣......" አላስጨረስኳትም
"ጥሬ!"
ያዘዝኩት እስኪቀርብ ወጪ ወራጁን እያየሁ ድምቅ ብላ የተወለወሉ መጫሚያዎቼን
ያጠለቁ ረዣዥም እግሮቼን አነባብሬ በሃሳብ ስዛብር አንዲት ብርማ ቆንጆ የቤት መኪና
ወደ ሰፊው ግቢ ገብታ ጥላ ተሻምተው ከቆሙ ሌሎች ሁለት መኪኖች ጎን ስትቆም
ከመስተዋቷ ላይ አርፎ የሚንፀባረቀው የፀሀይ ጨረር ዓይኖቼን ስለወጋኝ በስተግራዬ ካለው
ወንበር ላይ ቦታ ቀይሬ ቁጭ አልኩ። ያዘዝኩትም ምግብ ስለቆየ ከዚህችው መኪና ውስጥ
ወዳሉት ጥንዶች ሳልፈልገው አይኖቼም ቀልቤም አርፎ ነበርና ሁኔታቸው ገርሞኝ ነበር።
ሁለቱም ደጋግማው ወደ እኔ እያዩ የሆነ ነገር ያወራሉ። ትንሽ ዘግየት ብዬ ስመለከትም
አይኖቻቸው እኔ ላይ ደሞ መልሰው እርስ በእርሳቸው ይሆናል። የቀረበልኝን ምግብ
ለመጀመር እንደወተት ከነጣው እንጀራ ጥግ ላይ ሚጥሚጣ በትኜ በለምለሙ እንጀራ
የናፈቀኝን ክትፎ ጠቀም አድርጌ ጠቅልዬ አንዴ እንደጎረስኩ በዚህችው መኪና ውስጥ
ከሚያሽከረክረው ጎን ተቀምጣ የነበረችው ወጣት ልጅ ከመኪናው ወርዳ እኔ ወዳለሁበት
ስትመጣ ውበቷን እያየሁ የሰርቅ ዳንዔል "ቆንጆዎቹ" የሚለው ከረዥም አመታት በፊት
ያነበብኩት መፅሀፍ ትዝ እያለኝ ነበር።
እረ ይሄ ብቻ አይደለም! "The beautiful ones are not yet born" የሚል አንድ ልብ
ወልድም ማንበበቤ ትዝ አለኝ። ይቺን አይነት ቆንጆ ልጆች መወለዳቸውን ቢያይ ኖሮ ያ
ጋናዊ ደራሴ ቆንጆዎቹ መወለዳቸውን የሚገልፅ ሌላ መፅሀፍ ባስነበበን ነበር።
ከመስተዋቱ ላይ ተብረቅርቆ ወንበር ካስቀየረኝ የፀሀይ ነፀብራቅ ይልቅ በደመቀ ፈገግታ
ወደ እኔ የምትራመደውን ሳይሆን የምትሰፈውን ወጣት ሴት ላይ አይኖቼን ተክዬ ሶስተኛ
ጉርሻዬን እንደጎረስኩ ለካ ወደኔው ኖሮ የምትመጣው የበረንዳውን ደረጃ እየወጣች
"ጋሼ!?" አለቺኝ ። ግራ ተጋብቼ ግራና ቀኜን ተገላመጥኩ። ከጠረጴዛዬ ላይ ከተቀመጠው
ክትፎ የያዘ ትሪ እና ከውሃ በብርጭቆ በቀር ማንም የለም።
ፍልቅልቅ ብላ እየሳቀች ከፊት ለፊቴ ቆማ
"ጋሼ እንዴት ነህ? አላወቅከኝም አይደል?" ተጠምጥማ ሳመቺኝ ። ግራ በመጋባት ቆሜ
ተሳምኩላት።
"ይ.....ይቅርታ ተሳስተሽ እንዳይሆን። አላወቅኩሽም! "
"እኔ አውቄሀለሁ! ይባስ ብላ አቅፋኝ አንገቴ ስር ገብታ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ግራ ገባኝ።
ካንገቴ ተላቃ
አይኖቿ ላይ አርጋው የነበረውን ቡናማ የፀሀይ መነፅር አውልቃ እንባ ባረጠባቸው ሌጣ
አይኖቿ እያየቺኝ
" አሁንስ? አወቅከኝ?" ፈገግ እንደማለት ብላ ጠየቀቺኝ።
"አምላ..............ኬ! ፍ........ቅር!?" አልኳት ሰውነቴን እንደመንዘር እያለው። አሁን እኔ ነኝ
ያቀፍኳት ። ሳላውቀው እንባዬ ወረደ ።
"ፍቅር!? " ድንጋጤ ወሮኝ ቀጠልኩ 'በህልሜ አይደለም አይደል? " አልኳት።
"ኖ! አይደለም ጋሼ!? እውን ነው! " መኪናውን ያሽከረክር የነበረው መልክ መልካም ወጣት
ምን ግዜ ካጠገባችን መጥቶ እንደቆመ ሳላውቅ ጥቅልል ናፕኪን ሲሰጣት ከውስጡ መዛ
መጃመሪያ ለእኔ ሰጥታኝ ስታበቃ ለርሷም ወስዳ አፍንጫዋንና አይኖቿን አባበሰችበት።
"ተዋወቀው ጋሼ? ሄኖክ ይባላል! እጮኛዬ ነው" በአክብሮት እጅ ነስቶኝ ተዋወቅን።
"አምላኬ! እንዴት አወቅሺኝ ግን? ስንት ዓመት ሆነው? ሃያ አይጠጋውም" ጠየኳት።
እንደልጅነቷ ተሽኮርምማ ሳቀችና አሁን ሃያ ሁለት ዓመት ሆነኝ። ያኔ ስታውቀኝ ስድስት
አመት አልሞላኝም ነበር" ብላኝ አትኩራ አየቺኝና አይኖቿ እንባ ሞልተው መልሳ እቅፍ አርጋ
ሳመቺኝ። ከትላልቅ ዓይኖቿ ወፋፍራም የእንባ ዘለላዋች እርግፍ፣ እርግፍ ሲሉ ፊቷን አባብሳ
"ጠረንህ እንዳለ ነው! ያኔ መጀመሪያ ቀን አቅፈህ ይዘኽኝ ሄደህ " ምን ልግዛልሽ?" ስትለኝ
"አቡ ወለድ" ስልህ ምን እያልኩ እንደሆነ መለየት አቅቶህ ግራ ስትጋባ። ልክ የዛን ለት
አቅፈህ ደባብሰህ ስትስመኝ የነበረው ደስ የሚል ጠረንህ ዛሬም እንዳለ ነው። እየበላህ?!
አለቺኝ። ምግቡን ትቼ ከእነኛ ልዩ አይኖቿ ውስጥ የኔን የወጣትነት ዘመን፣ የእርሷን
የጮርቃነት ግዜ እንደ ፊልም ወደ ኋላ አጠንጥኜ እያየሁ ።
*
*
*
ፍቅርን የማውቃት ትኩስ የኮሌጅ ተመራቂ ሆኜ ግቢውን እንደለቀቅኩ ስራ እስካገኝ ድረስ
ከተጠጋሁባቸው የእናቴ ዘመዶች ቤት በከረምኩበት ግዜ ነበር። ከዚሁ ዘመዶቼ ቤት ፊት
ለፊት ካለ የቆርቆሮ አጥር ከነበረ ግቢ ውስጥ የግቢውን በር ገርበብ አርጋ የምትቆም
በግምት አራት ወይም አምስት ዓመት የሚሆናት ቅላቷ ወደ ቢጫነት የሚያደላ፣ ስስና ሉጫ
ፀጉር የነበራት ፣ ሌባ ጣቷን ትናንሽ ከናፍሯን ፈልቅቃ በማፈር ስሜት አፉዋ ውስጥ
የምትከት ልጅ ነበረች። ስገባና ስወጣ በትንሹ በተከፈተው በር በኩል ብዙ ግዜ ቆማ
ስለማያት በአይን ተላምደን
"ሚሚዬ ደና ነሽ?" እላታለሁ። አትመልስልኝም። ይልቅ ትሽኮረመምና ዝም ብላ እስክርቅ
ታየኛለች። ትንሽ ሰነባብቶም ድንገት ያላየኋት ከሆነ
"ጋሼ?!" ስትል ትጠራኝና እንደገና ደግሞ አፍራ ትሽኮረመማለች። አዘውትራ በር ላይ
የመቆሙዋ ሚስጥር ግራ ሲገባኝ አንድ ቀን ለታ ቆም አልኩና
"ሚሚዬ ነይ እስኪ?" አልኳት ። አመነታች። ተሽኮረመመች፣ ግቢ ውስጥ ወደ ኋላዋ አየች
ትንሽ ቆይታ መጣች። እቅፍ አርጌ ስሚያት
"ማነው ስምሽ?" ስል ጠየኳት። ጠቋሚ ጣቷን አፏ ውስጥ ጨምራ ለራሷ ብቻ በሚሰማ
ድምፅ አቀርቅራ
"ፍቅል" አለቺኝ
"ማን?" ለማጣራት ጠየኳት።
"ፍቅል" ደገመችው
"ኦውውውው! ፍቅር ነው ስምሽ?" አሁንም እፍረትና መሽኮርመም እንደያዛት አቀርቅራ
"ሃዎ" አለቺኝ። ቁጢጥ ካልኩበት ሆኜ እንዳለሁ
"ለምንድነው ሁሌ እዚህ ቆመሽ የማይሽ?" ቀና ብላ አይታኝ
"አባዬን እየጠበኩ" አለቺኝ ተኮላትፋ በሚጣፍጥ አን