“ እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል ። ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል ።
ከሰማሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም ። ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ ።
ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበው ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።
እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው' ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ ።
እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል ። እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል ። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ። የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ። "
" ጠበኛ እውነቶች " ከተሰኘው የሜሪ ፈለቀ መጽሐፍ የተቀነጨበ ::
@wegoch
@wegoch
@paappii