ከሌሊቱ 10:30 ላይ "የኔ ፍቅር ከመስሪያ ቤት ትዕዛዝ ስለመጣልኝ(ብኝ) በጠዋት ወደ ክፍለ ሀገር ልሄድ ነው" የሚል በኔ እሳቤ ነገ ጠዋት ውብ አይኖቿ ሲገለጡ የሚነበብ መልዕክት ላኩላት።"የተረገመ መስሪያ ቤት!!የት? ስንት ሰዓት? ለስንት ቀን? ከማ ጋ?" የሚል የጥያቄ አገልግል አስታቀፈችኝ፣ሰዓቴን አየሁት 10:31 ይህቼ ሴት አትተኛም እንዴ እያልኩ በመገረም ውስጥ "የነዚህን ጥያቄዎች መልስ" ብዬ ከመፃፌ ስልኬ እጄ ላይ ተንቀጠቀጠች፣እጅግ የምወደው ስም በስልኬ መስታወት ላይ ብቅ አለ "አለሜ" አነሳሁት፣ ሙሉ አካላትን በሚቀሰቅስ ለሆሳስ "የኔ ፍቅር፣ ብላ ከላይ በፅሁፍ የላከቻቸውን ጥያቄዎች አዥጎደጎደች፣ ሳቄ አመለጠኝ፣ለምን እንደሳቅኩ ገብቷታል፣ "ምኗ እብድ ነኝ በናትህ! ተደናብሬ ሰላምታውንም ረሳሁትኮ፣እንደምን ነህልኝ የኔ ንጉስ" አለችኝ "ደህና ነኝ አለሜ አሁን ይሄን የምናወራበት ግዜ አይደለም፣አሁን ተኚ ጠዋት ከመውጣቴ በፊት ደውዬልሽ ሁሉንም እናወራለን" አልኳት "ልብሶችህ ንፁ ናቸው? ገንዘብስ እጅህ ላይ አለ?" "አለሜ" አልኳት አንድ አይነት ጥሪ እንኳን ሆኖ የፍቅር፣የቁጣ፣የደስታ፣የሀዘን፣የናፍቆት፣የመከፋት ሲሆን ለይታ ታውቀዋለች። ከዚህች "አለሜ" ከምትል ቃላት ውስጥ" አንቺ አርፈሽ ተኚ ጠዋት እናወራለን" የሚል ወርቅ አወጣች፣"ደህና እደርልኝ እንደነቃህ ደውል" ብላኝ ስልኩ ተዘጋ።አዓምሮዬ እሷን እያሰበ፣መላ ሰውነቴ እሷን እየናፈቀ፣አልጋዬ ጎን ከቆመው ሳጥን መሳብያ ውስጥ ግራ እጄ አንድ ነገር አቀበለኝ፣ትናንት ቤቴ ውስጥ ረስታ የሄደችው ሻርፕ!!ሁሌ በቦርሳዋ ትርፍ ሻርፕ ስለምትይዝ ቤቴ የመጣች ቀን አድርጋ የመጣችውን ማስቀረት ልማዴ ነው። መጀመሪያ አከባቢ ትቃወመኝ ነበር ታድያ አንድ ቀን ልትቀበለኝ ስትታገለኝ አንገቷ ስር ገብቼ "አለሜ ተጠናቀሽማ አትሄጂም ባይሆን ጠረንሽን እዚህ ተይልኝ" አልኳት ፈቀደች ፣ወደ አፍንጫዬ አስጠጋሁት ኡፍ ብዬ በረጅሙ ተነፈስኩ፣የሷን ጠረን ከአንገቷ ስር የማግኩ ያህል ተሳምኝ!!
በሬ ተንኳኳ በድንጋጤ ከእንቅልፌ ባንኜ(ለካ እሷን እያሰብኩ እንቅልፍ ወስዶኝ ነበር) ሰዓቴን ተመለከትኩ 12:01 ይላል፣ ድንጋጤዬ በእጥፍ ጨመረ ሊነጋ አከባቢ ቤቴ ሲንኳካም ሆነ ስልኬ ሲጠራ ይረብሸኛል፣የሆነ በጣም የምወደው ሰው ሞቶ ሊያረዱኝ የመጡ ይመስለኛል!! ድጋሚ ተንኳኳ "አምላኬ ሆይ ቸር ወሬ አድርገው" እያልኩ ተነስቼ ከፈትኩት፣ ልክ ከፍቼ ውጭ ላይ ያለውን ሰው ስመለከት መላ አካላቴ በድንጋጤ ራዱ፣የልብ ምቴ ጨመረ፣እጆቼ ተንቀጠቀጡ አለሜ ነች! (ቤቷ ከቤቴ በፈጣን እርምጃ 40 ደቂቃ እኮ ነው)"በሰላም ነው አለሜ?" በኔ አፍ ሌላ ሰው የጠየቀበት ነው የመሰለኝ፣ዘላ እቅፍ አደረገችኝ እና "በርዶኛል እንገባ" ብላ የሆነ በትልቅ ቦርሳ ያንጠለጠለችውን ነገር ተሸክማ ገባች፣ተከትያት ገባሁ "አንተ ጉዞ አለብኝ እያልክ ትተኛለህ እንዴ" አለችኝ ያን ሁሉ ነገሬ የሆነውን ፈገግታ እያሳየችኝ፣ቦርሳዋን ከፈተችው የታሰረ ብር(አምስት ሺህ ይመስለኛል)፣የታጠበ ሱፍ(መቼ ይታጠብ ብዬ ከሰጠሁበት እንዳወጣችው!)፣የተቋጠረ ምግብ(የምወደውን ፍርፍር) ተገረምኩኝ "እኔ የምልሽ አለሜ አለቃ እኔ ጋ መልዕክት ከመላኩ በፊት ላንቺ ደውሎልሽ ነበር እንዴ?" ደነገጠች "ማለት?" አለችኝ "ማለቴማ ቀድሞ ካልነገረሽ እንዴት በአንድ ሰዓት ውስጥ ያውም በጠራራ ሌሊት ይሄን ሁሉ ማድረግ ይቻላል?" ሂድ ወረኛ! በል አሁን ተነስ እና ተጣጠብ"
1:30 በሬ ላይ ሹፌሩ የመኪናውን ጥሩንባ አጮኸው፣ ያጩኻ! እኔ አንደሆንኩ በአለሜ ውብ ጣቶች ቁርሴን በልቼ፣ጥቁር ሱፍ ለብሼ፣ገንዘብ በኪሴ ከትቼ ተጠናቅቄያለሁ!!
"ደሞ የት ሂዱ አለ" አልኩት ሾፌሩን
"መቀለ" አለኝ ሰላም ግባ የኔ ንጉስ ብላ ከንፈሬን ሳመችኝ፣ሾፌሩ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ዞረ።
መኪናው አቅጣጫውን ወደ ሰሜን አዙሮ መጋለብ ጀመረ።
ሰው እንዴት እንዲህ ሁሉ ነገር ተሟልቶ ይፈጠራል? እንዴት ምንም አይጎለውም? እንዴት ምንም ያልጎደለውን እንደኔ ካለው ምንም ከሌለው ያቆራኛል? ይህች ሴት የእናቴ ፀሎቶች ድምር ውጤት ነች እንዴ? "እሺ አለቃ አዲስ አበባ መውጫ ላይ ደርሰናል የምገዛልህ ነገር አለ?" ሀሳቤን አቋረጠብኝ " አይ ምንም አልፈልግም፣ እንካ የምትገዛው ነገር ካለ ግዛ ብዬ 100 ብር ሰጠሁት።
ስልኬን አነሳሁና "አለሜ አንቺ ለኔ የመኖሬ ምክኒያት ነሽ አፈቅርሻለሁ!" ብየ ላኩላት!!!!
ተሞነጫጨረ: አልኑር
@wegoch