በቀደም ለት ማታ ቡና ከምጠጣበት ቦታ ወደ ቤቴ እየተጣደፍኩ እየሄድኩ እያለው አንድ እድሜው 10 እስከ 12 የሚገመት ጎዳና ቤቱ የሆነ ልጅ እግሬ ላይ ጥምጥም ብሎ ሳንቲም ይለምነኝ ጀመር ፡፡ ይሄ አይነቱ ልመና በምኖርባት ከተማ በጣም የተለመደ በመሆኑ በመሰልቸትም ጥድፊያ ላይ ስለነበርኩም (እንደ ምንክንያት)ለልመናው ቦታ አልሰጠሁትም ነበር ብቻ የሆነው ሆኖ ሳንቲም ሳልሰጠው ከእግሬ ላይ አስነስቼው ወደ መንገዴ ...ጥቂትም ሳልራመድ አባት አባት አለኝ ዞርኩ ኮሮና ቫይረስ ስለገባ ምግብ ቤቶች የተራረፈ ምግብ (ቡሌ) ስለማይሰጡን እኮ ነው አለኝ ፡፡ ያማል ፡፡ያለኝን ሰጠውት ወደ ቤቴ እየሄድኩ መንግስት ምን እያሰበ ነው ብዬ እንጠይቅ ውስጤ አስገደደኝ እነዚህ ልጆች ጎዳና ላይ ውለው ጎዳና ላይ እንደሚያድሩ የሚጠፋው ያለ አይመስለኝም እንደ በሽታው አካሄድ ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ልጆቹ እንደ ዜጋ ለጊዜውም ቢሆን ተመርምረው አንድ ቦታ የሚቀመጡበት መንገድ አይታሰብም ወይ እነዚህ ልጆች ከባለሀብቱ እስከ ወጣቱ የማይነኩት ሰው አለ ወይ የማይሄዱበት የማይንቀሳቀሱበት ስፍራ አለ ወይ በሽታውን ለማሰራጨት ከፍተኛ እድል እንዳላቸው ሳይታሰብ ቀርቶ ነው ወይ ? እነሱስ ቢሆን ልብሳቸው ቢያድፍ ሰውነታቸው ቢቆሽሽ ሰው አደሉ ወይ ዜጋ አደሉ ወይ ?ጥያቄ ይሆንብኛል ፡፡ነገሮች እንዴት እየሄዱ እንዳሉ ያሳስበኛል ሀገሬን እወዳለው ደሜ አጥንቴ ገለመሌ ቅብርጥሴ ሲል የነበረ ሁሉ ማንነቱን ክዶ ቃሉን በልቶ ለገንዘብ ሲያደገድግ ሳይ ያሰጋኛል ገንዘቡን ሀይማኖት አድርጎ ሲያጎበድድ ሲያይ ያመኛል ፡፡ይገርማል እንዴት ሰው ነኝ በዛ ላይ ሀገሬን ወዳለው ከሚል ሰው እንደዚ አይነት ተግባር ይፈፅማል ይሉኝታ እሴቴ ነው መገለጫዬ ከአባቴ ቃል ውልፊት ..ለኔ ያለው የትም አይሄድም.. የኔ እድል ከኔ ውጪ የት ገብታ ..ሲል የነበረው ሁሉ ለገንዘብ ሲያጎበድድ ማየት ይቀፋል ፡፡በምን ሂሳብ በምን ህግ አንድ እቃ 80 እና 90 በመቶ ይጨምራል በምን አይነት ልኬት እራሱን ቢለካ ፊት ለፊት አስቀምጦ የለም ጨርሻለው ለማለት የበቃው ?ያስደነግጣል ፡፡ሲደመር መንግስት እያደረገው ያለውን ጥንቃቄ ባልጠላም ቡዙ የታሰበበት አይመስለኝም ፡፡እንዴት ?ቫይረሱን ለመከላከል ታስበው እጃችንን እንታጠብበት ዘንድ የተቀመጡት ሮቶዎች የተቀመጡበት አከባቢ ያለው ጭንቅንቅ ለታክሲዎቹ የወጡት አዎጆች ከመሀል ከተማ እንደተንቀሳቀሱ አለመስራታቸው ሁሉ ያሳስባል ፡፡ከህግ ውጪ የምግብ ሸቀጦች ላይ ሁሉ የተጨመሩት የዋጋ ጭማሪዎች ያሳስባሉ ፡፡ያሰጋል ፡፡ስለዚህ አስብ ታክሲ ስትሳፈር የምትይዘውን ብረት የገንዘብ ልውውጦችህ ካፌ ቁጭ ስትል ብና የምታማስልበት ማንኪያ የበርህ እጀታ የስልክህ የላይኛው ክፍል የተቀመጥክበት ወንበር ብቻ ተወው ነገሮችህ በሙሉ ለኮሮና ቫይረስ መስፈሪያ የሆኑ ናቸው ፡፡ያገባቸዋል የሚባሉና የሆነ ለውጥ ሊፈጥሩ የሚችሉ ሰዎች በአብዛኛው ጆሮ ዳባ ልበስ ስላሉ እራስህን /ሽን/ጠብቅ ጠብቂ "አትጨባበጡ" ባለባጃጆች እና ባለ ታክሲዎች ከገንዘብ ውጪ አስቡ "ተራርቃቹ ተቀመጡ"ባለ ሀብቶች ብትችሉ ምናችሁም አደለም እና ሰርቪሶቻችሁን ለህዝቡ በማሰማራት ተባበሩ ከወሬ ያለፈ ነገር ለመስራት ተንጠራሩ መንግስት መደረግ ያለበትን ሁሉ ለማድረግ ይሞክር አስገዳጅ መመሪያዎችን ያውጣ ግን ባንተ በኩል የሚጠበቅብህን አድርግ ቢያንስ እራስህን ከጠረጠርክ ተመርመር ከሰው ጋር ላለመገናኘት ሞክር በተረፈ ሳኒታይዘር (ውድ ነው ላታገኝም ትችላለህ )ጓንት ተጠቀም እጅህን ታጠብ (ውሀ ከየት አምጥቼ እንዳትለኝ)ለማንኛውም ሞክር ከዛ ፀሎት እና ዱአ አድርግ ወደ ፈጣሪህ ጩህ
እግዜር ይጠብቀን
አላህ ይጋርደን
አሜን !!
✍ንጉስ ደረሰ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
እግዜር ይጠብቀን
አላህ ይጋርደን
አሜን !!
✍ንጉስ ደረሰ
@wegoch
@wegoch
@wegoch