አልጣሽ
ገፃቸው በመታከት ዳምኗል።አይኖቻቸውን ቡዝዝዝዝ አድርገው ፊትለፊታቸው የሚነታረኩትን የልጅ ልጆቻቸውን በአርምሞ ሲያዩ ከቆዩ በኋላ "አይ አለመታደሌ!" ብለው በረጅሙ ተነፈሱና እያዘገሙ ወደ ኩሽናው ዘለቁ። ተንበርክከው የምጅጃውን እሳት በእፍታ የሚታገሉትን ባለቤታቸውን በጨረፍታ ቃኝተው አለፉና መደቡ ላይ በቁማቸው ወደቁበት።
አያ ቢምር እና እመይቴ አልጣሽ በስተርጅና የልጅ ልጆቻቸው ሞግዚት ሆነው የአፍታ እረፍት የሰማይ ያህል እንደራቃቸው ውለው ሌላ የድካም ቀን እስኪመጣ ያሸልባሉ።የመጀመሪያ ልጃቸው ሁለቱን የእራት አመት መንታ ልጆቿን፣ሁለተኛው ልጃቸው ደግሞ እህል በአፏ ከሌለ አርፋ የማትቀመጠዋን የሁለት አመት ልጁን ጥለውባቸው ወደ አጨዳ ያቀናሉ።
"እመይ...አበይ...ደኅና አድራችኋል?ንሱ ልጆይን ፍቀዷቸው...ህደናል" ይሏቸዋል።
ዛሬም እንደወትሯቸው ሶስቱ ህፃናት የወላጆቻቸው ዳና ከመጥፋቱ እየተፈራረቁ ጎጆይቱን በአንድ እግሯ ያቆሟት ጀመር።መንትዮቹ ፍቅሩ እና ሰውነት ከውልደታቸው አንስቶ ተስማምተው አያውቁም።እንደውም የቆዬው የልምድ አዋላጅ "አይ ሰውነት!ያኔም የእናታቸው ምጥ ሲመጣ...ወይ እሱ አይወጣ...ወይ ወንድሙን አያስወጣ...አናቱን በእግርና በእግሩ መሃል ደፍጥጦ ይዞ ብርሌ አስመስሎት ቀረ...ይኸው አድጎም አልተወው"ይላሉ መንትዮቹ ሲጣሉ ባዩ ቁጥር።ረፋዱ ላይ እመይቴ አልጣሽ ያቀጠኑትን ሊጥ ተሸክመው ወደ ምጣዳቸው አቀኑ።ሊጡን በኩባያ እየጠለቁ እንደ ረሀብተኛ ልዥ ሆድ መሃሏ የጎደጎደው ምጣዳቸው ላይ ያፈሱትና በክብ ቅርፅ በተሰራችው የጣውላ ማለስለሻቸው ዙሪያዋን ያለብሷታል።እንደ ሽማግሌ ጥርስ ዙሪያው የተፈረካከሰ ሙግዳቸውን አንስተው ምጣዳቸውን ከመክደናቸው ሰውነት ሲከንፍ መጥቶ ሊጡ ላይ አንድ ጆግ ውሃ ይሞጅርበትና እያሽካካ ይሮጣል።የ 80 አመት ጉልበታቸው አሯሩጦ መያዝን ባይፈቅድላቸው
"ሃይ!...ሃይ!...ሃይ!...ምነ ምነ አንዳች ያልታሰበ ቢያጥለቀልቅህ!"ረግመውት ወደ ሊጡ ይዞሩና
"አይ አለመታደሌ!"ብለው ከጎን ያለው ምድጃ ላይ አብሲት ሊጥዱ ገለባ መማስ ይጀምራሉ።ከእሳት ጋር ሲታገሉ አልፈዋቸው ከመደቡ የወደቁትን ባለቤታቸውን እየቃኙ
"ይኸ ተንከሲስ... ሊጡን አቅጥኖ አፈር አልብሶኝ አያ ቢምር!...አብሲት እስክጥል ማታ ከድኘ ያኖርኳት ሞሳ ባጨላ አለች በሳህኔይቱ...ይህዱ ጓዳ እሷን እየቀመሱ ይቆዩኝማ" ብለው አባብለው አሰወጧቸው።አያ ቢምር በጋሬጣና በእንቅፋት ጥፍሮቻቸው የወለቁ እግሮቻቸውን እየጎተቱ ወደ ጓዳ አቀኑ።መሃል ወለል ላይ ትንሿ የልጅ ልጃቸው በሁለቱም ጉንጮቿ ሞልታ የምታኝከው ባቄላ መፈናፈኛ አሳጥቷት በጭንቅ ስትቃትት አገኟት።ከ60 አመት በላይ ሞፈር የታዘዘለት እጃቸውን ወደ ማጅራቷ ሰደው መሬትን በአፍንጫ አስልሰው ካቃኗት በኋላ
"ኧረ አፈሩን ብይው!ይችን የመጋዣ ልጅ መጋዣ! "ሲሉ ተራግመው እመይቴ አልጣሽ የጠቆሟቸውን ሳህን ሲያማትሩ ከአጠገቧ እርቃኑን ተቀምጦ አዩት።እጆቻቸውን ወደላይ ሰቅለው
"አይ አለመታደሌ!" ካሉ በኋላ እንደ አመጣጣቸው እያገዘሙ ወደ ባለቤታቸው ተመልሰው መደቧ ላይ ተጠቅልለው ተኙ።
እንጀራና ወጡ ተዘጋጅቶ የምሳ ወጉ ከደረሳቸው በኋላ አያ ቢምር ከልብ ወዳጃቸው ጋር ሊያወጉ ወደ መንደር ዘለቁ።እመይቴይቱ ግን ፣ ቁሞ በመዋል የተብረከረኩ ጉልበቶቻቸውን ታቅፈው፣እሳት ያሟሸሻቸውን አይኖቻቸውን ከመክደናቸው እዛው ኩሽናው ወለል ላይ እንደተጋደሙ የልጅ እንቅልፍ ወሰዳቸው።ለአፍታ ካሸለቡ በኋላ ከአለት የከበደ አንዳች ነገር ጆሯቸውን ሲጫናቸው እየጮኹ ተነሱ።ዙሪያቸውን እየተፈራረቁ ከሚስቁት ሶስት ህፃናት ጋር እላያቸው ተበግራ የቆመችዋን ጥጉቧን አህያቸውን እያባረሩ የተረገጠ ጆሯቸውን በሻሻቸው ጥፍንግ አድርገው አስረው እዬዬአቸውን ያወርዱት ጀመር።ፍቅሩ ፈገግታው ከገፁ ሳይጠፋ እየተጠጋቸው
"እመይ...ሰውነት'ኮ ነው የኩሽናውን በር ከፍተን አህያይትን እናስገባትና ምጣዱን ትስበረው ያለኝ"አለ ወንድሙን በስርቆሽ እያየ።
"ይሄይ?ይኸ?ይኸማ ቢሆንለት በተኛሁበት ቢያነደኝ ነበር ደስታው...ምነ አንተ ዝም ያልከው እንግዲያ?"
" 'አፍርጨ ነው የምጥልህ' እ...እያለኝ"
"ፈ...ርጠህ ቅር በለ...ው እንደ እ...ንቧይ"ከማለታቸው በተረገጠው ጆሯቸው በኩል አንዳች ነገር 'ጭውውውውውውው' ሲልባቸው ታወቃቸው።
አመሻሽ ላይ ተረኛው እረኛ ታሪክ
"እመይቴ አልጣሽ....ከብቶይን አምጥቻቸዋለሁ አስገቧቸው" ብሎ ጮኸና ምላሻቸውንም ሳይሰማ ወደሌሎች ባለከብቶች አቀና።
አያ ቢምር ከዋሉበት ወግ ሲመለሱ መንትዮቹ እንደወትሯቸው እየተነታረኩ፣ትሁንም ከምሳ አትርፈው የከደኑት መሶብ ላይ ለብቻዋ ሰፍራ እየታገለች፣ከብቶቻቸውም የጎረቤታቸው ማሳ ላይ ሲምነሸነሹ አገኟቸው።ከብቶቹን ከበረታቸው ጨምረው ባለቤታቸውን ጥሪ ገቡ።
"አልጣሽ!...ኧረ አልጣሽ!ኧረ 'ምኑ ገባሽ?"እያሉ ዋናውን ቤት ቆጡ ሳይቀራቸው አሰሱት።እየተጎተቱ ወደ ኩሽናው ሲዘልቁ እመይቴ አልጣሽ እጥፍጥፍ ብለው ተኝተዋል።
"ኧግ የደረባኑ መልአክ!ምነ አልጣሽ ምነ?አስርና ክያ እነጀራ አወጣሁ ብለሽ እስካሁን መኝታ?ኧረግ የኔይቱ ወይዘሮ!"ብለው እላያቸው ላይ ጣል ያረጉትን ኩታ ሲገልጡት አፀድ የመሰለው ሻሻቸው በደም ርሶ፣የጆሮ ግንዳቸውና የአንገታቸው ስር የደም ድልህ ተጋግሮበት አገኙት።ያዩትን ስለተጠራጠሩ ኩታውን ወደነበረበት መልሱና አይኖቻቸውን ማሻሸት ገቡ።ፍቅሩ ሲበር መጣና
"አበይ...ይኸ ሰውነት እመይን በተኛይበት ጥጉቢትን አህያ አስረገጣት።ጥሩ ውሃ ስጭኝ ብየ ብጠራት ብጠራት አኩርፋ ነው መሰል ዝም አለችኝ።ናማ አንተ ስጠኝ"
የእመይቴ አልጣሽ ቀብር ላይ አንድ ወዳጃቸው እንዲህ ሲሉ ሙሾ አወረዱላቸው።
"አንች የኔ ጉልበታም እንዲህ ነበርሽ ወይ
ክያ እንጀራ አውጥተሽ ማረፍሽ ነወይ
አንች ተደከመሽ እኔ እጋግራለሁ
ጠጅሽን ያሉ እንደሁ እንዴት አደርጋለሁ
ቀና በይ አልጣሽ ቅጅልኝ ከጠጁ
የጠላሽ አይጠፋም ሞልቷል የልጅ ልጁ"
ዘማርቆስ
(@wogegnit)
@wegoch