"እንጋባ" ሲል ጠየቃት አሳምነው። አልተቀበለችውም አስማሩ። "ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው። ተስማሙ።
ቤቷ እየመጣ ይጠይቃታል። ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፣ ካላት ታቀርባለች ይበላሉ። አወግተው ይለያያሉ። የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም።
አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ መጣ። እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ። ስለ ሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ።
አስማሩ አሳምነው ረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት። ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም። ጃኬቱን አውልቆ ሄደ። አስማሩ እሱንም አጥባ አኖረችው። ሱሪውን ደርቦ መጣ "ወበቀኝ!" አወለቀው።
አስማሩ አጥባ አኖረችው፣ ካፖርቱን ጥሎ ሄደ፣ አጥባ አኖረችው። አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ፣ አስማሩ "ምነው?'' አለችው። "በጠራራ ፀሀይ ብርድ ሆዴ ገባ'' አላት።
"ምች ይሆናል" አለችው። የምች መድኃኒት ብታሽለት ተሻለው። ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም ጥሎት ሄደ። አስማሩ አጥባ አኖረችው፡፡
ትንሽ ቆይቶ፣ ፍራሹን ተሸክሞ መጣ።
"ምነው?" አለችው።
"ላሳድሰው መሄዴ ነው። አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው'' አላት። አመነችው።
ጨዋታው ደራ፣ ፍራሹን ረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ሌሊት ቢመጣ አስማሩ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ፍራሿ ላይ ደርባው ደረሰ። ያኔ "ተነሽ" ከማለት "ጠጋ በይ'' ማለት ቀልሎ ተገኘ። ጠጋ አለች::
By Alemayew Gelagay
@wegoch
@wegoch
@paappii