የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ወልድ ዋህድ ሰንበት ት/ቤት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


ይህ የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተ-ክርስቲያን ወልድ ዋህድ ሰንበት ት/ቤት የበጎ አድራጎት የጉዞ ክፍል እና የሽያጭ ክፍል ቻናል ነው
በዚህ ቻናል ላይ
1️⃣ የበጎ አድራጎት ስራዎች ይኖራሉ
2️⃣ የንግስ ጉዞ / የሂወት ጉዞ

3️⃣ የሂወት ጉዞ
4️⃣ የሂወት ጉዞ ይኖራል
4️⃣ ንዋያተ ቅድሳት ሽያጭ
5️⃣ በተጨማሪ ጥያቄና መልስ ይኖራል

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций




+ ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር +

እመቤታችን ጌታን ጸንሳ ከወለደችው በኋላ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ እንደ ልጅነቱ እያገለገላት ፣ እንደ አምላክነቱ እያገለገለችው አብራው በአንድ ቤት ውስጥ ኖራለች፡፡

ሌላውን እንተወውና ይኼ ነገር ብቻ ለማሰብ ያስጨንቃል! ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ አንድ ቤት ውስጥ መኖር እንዴት ያለ ነገር ነው? ልብ በሉ ድንግል ማርያም ጠዋት ከእንቅልፍዋ ስትነቃ "እንዴት አደርህ?" የምትለው ፈጣሪዋን ነበር:: ማታ ስትተኛ "ደህና እደሪ" የሚላትም አምላክዋ ነበር:: የማይተኛው ትጉሕ እረኛ በተኛች ጊዜ ሕፃን ሆኖ ከአጠገብዋ ያደረ ከእመቤታችን በቀር ማን አለ?

ኪሩቤልና ሱራፌል ቅዱስ ቅዱስ የሚሉትን አምላክ እንደ እናት "እሹሩሩ" ብላ ያስተኛች እርስዋ ነበረች:: ምድርን  በአበባ ልብስ የሚያስጌጠውን ጌታ በተኛበት ያለበሰችውም እርስዋ ነበረች:: ዓለምን በእጆቹ የያዘውን ጌታ ክንዶችዋን ያንተራሰችው እርስዋ ነበረች:: እነዚያን ሌሊቶች ድንግል ማርያም እንዴት አሳልፋ ይሆን? በሕልምም በእውንም ከፈጣሪ ጋር ማሳለፍ እንዴት ያለ ጸጋ ነው?

ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው፡፡ እመቤታችን ከልጅዋ ጋር ለሠላሳ ዓመታት አብራ በአንድ ቤት ስትኖር የነበራቸው ንግግር ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደመሆኑ ጸሎትም ጭምር ነበር፡፡

የጠዋትና ማታ ጸሎትሽ ከልጅሽ ጋር ማውራት የሆነልሽ : ልጅሽ የሚሠጥሽ መልስ የፈጣሪ መልስ የሆነልሽ እመቤቴ ሆይ ስላንቺ ክብር ማሰብ ምንኛ ያስጨንቃል?

እስቲ ረጋ ብላችሁ አስቡት! እመቤታችን እና ጌታችን በእነዚያ ሁሉ ዓመታት ምን ሊነጋገሩ ይችሉ ነበር? ከእርስዋ በቀር ማን ይነግረናል? ድንግል ሆይ አንቺ ካልነገርሽን ማን ይነግረናል? ለማዕድ ስትቀመጡ ምን ብሎ ጸልዮ ይሆን? እንደ ሐዋርያቱ ቆርሶ ሠጥቶሽ ይሆን? ውኃን እንዲጠጣ ሞልተሽ ስትሠጪው ውቅያኖስን እንዴት በውኃ እንደሞላ ነግሮሽ ይሆን?

በእርግጥ በእነዚያ ዓመታት ክርስቶስ ለእናቱ ምን ምን ሲነግራትስ ኖሮ ይሆን? ስለየትኛውስ ምሥጢር ሲገልጥላት ነበር? ገና የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለ በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያነጋገሩት የአይሁድ መምህራን ‹በማስተዋሉና በመልሱ ሲገረሙ ነበር› እመቤታችን ከሕጻንነቱ ጀምሮ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ አብራው ስትኖር በስንቱ ነገር ስትደነቅ ኖራ ይሆን? /ሉቃ. ፪፥፵፯/

እንደ መንፈሳዊት እናት ድንግል ማርያም ለልጅዋ የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እየነገረች አሳድጋው ይሆን?  ሙሴ ስላያት ዕፀ ጳጦስ ታሪክ አልነገረችው ይሆን? ታሪኩን ሰምቶ "ያቺ ዕፅ አንቺ ነሽ እሳቱ ደግሞ እኔ ነኝ"ብሏት ይሆን? ውኃ ስለፈለቀበትና እስራኤል ስለጠጡበት ዓለት ነግራው ይሆን? እርሱስ "ያ ዓለት እኮ እኔ ነበርሁ" ብሎአት ይሆን?

ብሉይን ስታነብ ሐዲስን እየተረጎመ እንደ ኤማሁስ መንገደኞች ልብዋን አቃጥሎት ይሆን? ሉቃ. ፳፬፥፴፪/ ጠቢበ ጠቢባን ሊቀ ሊቃውንት ኢየሱስ ክርስቶስ በቤትሽ ጉባኤ የዘረጋብሽና ያስተማረሽ ድንግል ሆይ አንቺ እንደሆንሽ በልብሽ ከመጠበቅ ውጪ ብዙ አትናገሪም:: ሆኖም ልጅሽ ምን ምሥጢር ነግሮሽ ይሆን?

ኤልሳቤጥ እንኳን ዮሐንስን ጸንሳ ስለጽንሱ የምትለው ብዙ ነገር ነበራት:: ፈጣሪ በአንቺ ዘንድ ያደረ ድንግል ሆይ አንቺስ ምን ትነግሪን ይሆን? "የመለኮት እሳት በሆድሽ ባደረ ጊዜ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት ነው:: እንደምን አላቃጠለሽም? የኪሩቤል ዙፋን በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘረጋ? በግራ ነው ወይንስ በቀኝ? ታናሽ አካል ስትሆኚ ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን ይችላል?" እያልን ከአባ ሕርያቆስ ጋር እንጠይቅሻለን::

እንዳንቺ ፈጣሪውን የሚያውቅ ፍጡር የለምና የዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት : የነገረ መለኮት ምሁራን : የወንጌሉ ተንታኞች ሁሉ ከአንቺ እግር ወድቀው እንደ አዲስ ስለ ክርስቶስ ሊማሩ ይገባቸዋል:: ልህቅተ ሊቃውንት እመቤታችን ሆይ ሊቃውንት ሁሉ ያንቺ ተማሪዎች ናቸው:: ባለ ቅኔዎች ሁሉ ባንቺ ፊት ገና ፊደል አልቆጠሩም:: ሰውና መላእክት አንድ ላይ ተሰልፈው "ብርቱ የሚሆን በአንቺ ያደረገውን ታላቅ ነገር" ሊሰሙ ይጠባበቃሉ:: ወዳጄ ጥቅስ ፍለጋህን ትተህ እግዚአብሔርን በእቅፍዋ ከያዘችው ቃሉን በሹክሹክታ በጆሮዋ ከሰማችው ድንግል እግር ሥር እንደ እኔ ብትደፋ ይሻልሃል:: የእግዚአብሔርን እጆች ይዛ የመጀመሪያዎቹን የሕፃንነት እርምጃዎቹን እንዲራመድ የመራችውን ድንግል መቆም ያቃተንን ደካሞች እንድትመራን አብረን ደጅ ብንጠናት ይሻላል::

እነ ጴጥሮስ በቅዱሱ የታቦር ተራራ ከጌታ ጋር ነበሩ ፊቱ ሲያበራ አይተው በዚህ ካልኖርን ብለው ተመኝተው : ኤልያስና ሙሴን አግኝተው ነበር:: ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር የኖርሽው እመቤታችን ሆይ የልጅሽ ልብሱ ስንት ቀን አብርቶ ይሆን? ከነቢያትስ እነማንን አምጥቶ አሳይቶሽ ይሆን? እንደ ጴጥሮስ "ሦስት ዳስ እንሥራ" የማትይዋ የእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ሆይ ቤትሽ ደብረ ታቦር ሆኖልሻልና ልጅሽ ምን አሳይቶሽ ይሆን? ከእግዚአብሔር አብ "ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሚው" የሚል ድምፅ መስማት የማያስፈልግሽ "ለእኔም ልጄ ነው" ማለት የምትችይዋ እናት ሆይ እንደ እግዚአብሔር አብ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" ለማለት ሥልጣን የተሠጠሽ ሆይ ሠላሳ ዓመት ከጌታ ጋር መኖርሽን ባሰብሁ ጊዜ ጠባብዋ ሕሊናዬ ኃጢአት ያደቀቃት ሰውነቴ እጅግ ተጨነቀች::

ዮሐንስ በፍጥሞ ደሴት ብዙ ራእይ አይቶ "በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርኩ" ብሎ ጻፈ:: ሠላሳ ዓመታት የጌታ ቀን የሆነላት በመንፈስ የነበረች ድንግልስ ስንት ራእይ አይታ ይሆን?
መላ የሰውነታችን አካል ሁሉ አፍ ቢሆን የእርስዋን ክብርና ምስጋና ተናግረን መፈጸም አንችልም::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሰኔ 21 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ
(ወተዘከርኒ ለኃጥእ ገብርኪ ተክለ ማርያም)

ንዑ ንወድሳ ለማርያም ድንግል
(ኑ ድንግል ማርያምን እናወድሳት!)


መንፈሳዊ የኪነ ጥበብ ምሽት
🗓እሁድ መጋቢት 21 2017 ዓ.ም
🕰12:00-2:00
📍በወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት


ኢየሱስ አምላክ መሆኑን የሚገልጹ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 👇

1. “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”
  — ዮሐንስ 1፥1

2. “ቶማስም፦ ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።”
  — ዮሐንስ 20፥28

3. “በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤”
  — ቆላስይስ 2፥9

4. “የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤”
  — ቲቶ 2፥12-13

5. “ስለ ልጁ ግን፦ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።”
  — ዕብራውያን 1፥8

ክርስቶስ ፈጣሪ መሆኑን የሚገልጡ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች 👇

1. “ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።”
  — ዮሐንስ 1፥3

2. “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤”
  — ቆላስይስ 1፥15-16

3. “ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤”
  — ዕብራውያን 1፥2

4. “ደግሞ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤”
  — ዕብራውያን 1፥10

ክርስቶስ ስለራሱ አምላክነት የመሰከረበት 👇

1. “ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው።”
  — ዮሐንስ 8፥58

2. “እኔና አብ አንድ ነን።”
  — ዮሐንስ 10፥30

3. “ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳየን ትላለህ?”
  — ዮሐንስ 14፥9

4. “አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።”
  — ዮሐንስ 17፥5

5. ማርቆስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶¹ .. ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና፦ የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው።
⁶² ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ።

ዳንኤል 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።
¹⁴ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።


ክርስቶስ ከሰዎች አምልኮ (latria) ሲቀበል 👇

1. “እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና፦ ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።”
  — ማቴዎስ 28፥9

2. “ቶማስም፦ ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።”
  — ዮሐንስ 20፥28

3. ራእይ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥
¹⁸ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።

“የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።”
  — ኢሳይያስ 44፥6

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled0

ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled9


👉🏾 እግዚአብሔር #ቅዱስ #ሚካኤልን በልዓም ወደ ተባለ ሰው ላከው"

👉የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ወዳጆች ወገኖች የመካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ወልድ ዋህድ ሰንበት ት/ቤት ድህረ ገጽ የሚተላለፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በያላችሁበት የምትከታተሉ በእግዚአብሔር ሰላምታ ሰላም እንላችኋለን፣ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን እያልን ዛሬ በርዕሱ እንደተጠቀሰው "እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን በልዓም ወደ ተባለ ሰው ላከው" በሚል ርዕስ ነው የምንነጋገረው፣ አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን፦

መጋቢት  12

✍በዚህች እለት  እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን ወደ በልዓም ወደ ተባለ ሰው ላከው፣ ይህም "ሀብተ መርገምና፣ ሀብተ ቡራኬ የተሰጠው ነቢይ ነው" እስራኤል ከግብፅ ከወጣ በኋላ 40 ዘመን በበረሐ ተጉዘው ሞአብ ሲደርሱ "ንጉሡ ባላቅ ወልደ ሶፎር" ግብፅን በዘጠኝ መቅሰፍት በአሥረኛ ሞት በኩር፣ በአሥራ አንድ  ስጥመተ ባሕር ያጠፋ ጦር የማይመልሰው ጠላት ተነስቷል መጥተህ እርገምልኝ" ብሎ እጅ መንሻ አስይዞ ላከበት፡፡

ነቢዩ በልዓም መልክተኞችን ዋሉ፣ እደሩ ብሎ ሌሊት ወደ እግዚአብሔር
ጸለየ፣ በጸሎቱም ምላሽ ፈጣሪ ወደዚያች ከተማ እንዳይሄድ አመለከተው፣ "መልእክተኞችንም አልሆነም እናንተም ሂዱ አላቸውና ሄዱ" ንጉሥ ባላቅም እጅ መንሻ ቢያንስበት ነው ብሎ ከፊተኞች የበዙና፣ የከበሩ ሰዎችን ላከ፣ ባላቅም "ለነቢይ በልዓም ክብርህን ከፍ አደርጋለሁ ቤትህን በወርቅ እሞላለሁና  እርገምልኝ አለው" ነቢይ በልዓም ወርቅ ብርም ቢሰጡኝ በትልቁም ይሁን፣ በትንሹ ከአምላኬ ፈቃድ አልወጣም፣ ነገር ግን ፈጣሪ የሚለኝን ልወቅ አላቸውና ፈጣሪውን በጸሎት ለመነ፣ ፈጣሪውም "ነቢይ በልዓም ተነስ ከእነሱ ጋር ሂድ ነገር ግን የምነግርህን ትናገራለህ" አለው፡፡

አህያይቱን ጭኖ ከሄድኩማ እንዴት አልረግምም? እያለ ሲጓዝ በመንገድ
ቅዱስ ሚካኤል ሰይፋን መዞ ለአህያይቱ ታያት፣ ፈርታ ቆመችና ወደ እርሻ ውስጥ ገባች" በልዓምም ለመመለስ መታት፣ በዚያን ሰዓት እንደገና ቅዱስ ሚካኤል ከግንብ መካከል ቆመ፣ አህያይቱ ወደ ቅጥሩ ተጠግታ እግሩን ረገጠችው፣ አሮጌ ነቢይ አደረገሽኝ? ወይኔ ጦር በያዝኩ በወጋሁሽ ነበር አለ፣
ያን ጊዜ በሰው አንደበት "ከታናሽነትህ ጀምረህ ተራራውን ውጪ፣ ሜዳውን
ሩጪ ብለህ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁም ለምን ሦስት ጊዜ መታኸኝ? ምን አድርጌ ነው? አለችው"

ያን ጊዜ ዓይኑ ተከፍቶ " መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተገለፀለትከእህያው ወርዶ
ሰገደለት
" አህያህን ለምን ሦስትጊዜ መታህ? ከፊቴ ባትሸሽ ኖሮ አንተን በገደልኩ ነበር አለው፣ " ነቢይ በልዓምም በድያለሁ ፈቃድህ ካልሆነ ልመለስ "አለው፣ ሂድና የምነግርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው፡፡

ንጉሥ ባላቅም ነቢይ በልዓም መምጣቱን ሰምቶ በደስታ "ወደ አርኖን ዳርቻ መጣና ስለ መጣሁ ደስ አይበልህ እግዚአብሔር የገለፀልኝን ብቻ እናገራለሁ አለው" ንጉሥ ባላቅም መሥዋዕት ሰውቶ የሕዝቡን ዳርቻ አሳየና እርገምልኝ አለው፣ ነቢይ በልዓምም እግዚአብሔር ያልረገመን እንዴት እኔ እረግማለሁ? እግዚአብሔርስ ያልነቀፈውን እንዴት እነቅፋለሁ አለ? ንጉሡም እርገምልኝ ብልህ ትመርቃቸዋለህ? አለው፣  የገለፀልኝን ብቻ እናገራለሁ ብዬሃለሁ አለው፣ ለሦስት ጊዜ መስዋዕትን እየሰዋ እርገምልኝ አለው፣ ነቢይ "በልዓምም ያዕቆብ ከተማህ ምን ያምር? እስራኤል ቤቶችህ ምን ያምሩ? ብሎ አድንቆ አሞገሰ" ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል እያለ ምስጢረ ሥጋዌ ተገልጾለት ተናገረ፣ እርገምልኝ ብልህ ትመርቃለህ? አለው፣ እግዚአብሔር የገለፀልኝን ብቻ ነገርኩ አለው፣ ነቢይ በልዓምም " እረግሜ ባላጠፋልህም መክሬ አጠፋልሃለሁ፣ ደናግናኑ ለጣዖት ይሰግዳሉ፣ ያን ጊዜ ፈጣሪ ተቆጥቶ ያጠፋቸዋል" አለው፣ ያቺ ቀን "መጋቢት 12 ቀን" ነች፡፡

ምንጭ፦ "ድርሳነ ሚካኤል ዘወርሐ መጋቢት"

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled0

ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled9


🚌  ጉዞ ወልድ ዋህድ  🚎

ልዩ ሳምታዊ ጉዞ

⛪️ ወደ ስውሯ ማርያም ገዳም

     መጋቢት 28 ደርሶ መልስ
መነሻ ሰዓት 12:00

የጉዞ ዋጋ 700 ብር
መስተንግዶን ጨምሮ

👉  ትኬቱን  በሰንበት ት/ቤቱ
       መዝሙር ቤት ያገኙታል

ለበለጠ መረጃ 📱 09 85 46 75 66
                           09 96 48 12 33
                           09 83 03 21 99
                                   ይደውሉ።

  👉በዚህ ጉዞ ላይ በመሳተፍ በረከት ያገኙ ዘንድ ፈጥነው ይመዝገቡ👈
              ‼️ ማሳሰቢያ:-  ቦታ ሳይሞላ ትኬቱን ገዝተው በእጆ ይያዙ ‼️


ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled0

ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled9


ተጠቃሚ ያጡ መድኃኒቶች

1️⃣/ ቃለ እግዚአብሔር
               ጠዋት አንድ
               ማታ አንድ

2️⃣/ ንስሐ
         በየሳምንቱ አንድ አንድ

3️⃣/ ስጋወ ደሙ
        ቢያንስ በ40 ቀን አንዴ

4️⃣/ ጸበል
      ከምግብ በፊት በየቀኑ አንዴ

5️⃣/ እምነት
    ዘወትር በየሰከንዱ ያለማቋረጥ

6⃣/ ፍቅር
       ዘወትር ያለማቋረጥ ለሁሉም

7⃣/ ሰላም
  ለተከታታይ ሰዓታት እስከ ዘላለም

8⃣/ጸሎት
 በቀን ሰባት ግዜ ያለማቋረጥ

9⃣/ ፆም
   ከምግብ በፊት

1⃣0⃣/ ምፅዋት
በየቀኑ ከምታገኘው ጥቂቱን

1⃣1⃣/ ስግደት
ጠዋት 21
ማታ 20

☞☞ማሳሰቢያ፡- ሁሉም መድኃኒቶች ተስፋ በተባለ ውሃ ማወራረጃነት መዋጥ ይኖርባቸዋል፡፡

☞☞ማሳሰቢያ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ  ለ 15 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ።

1 ሰው ለ15 ምዕመን ይላክ

እነዚህ 100% መድኃኒት ናቸው ግን ተጠቃሚ አጥተዋል። ( አነስተኛ ነው )

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled0

ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled9


የሰንበት ት/ቤት ታሪካዊ አመጣጥ

+++++++++++++++++++++++
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በመሥራቿ በእግዚአብሔር ከተመሠረተች ጀምሮ ልጆቿን በተለያየ መንገድ ሰብስባ ከማስተማሯም በላይ ልጆቿ ያስተማረቻቸውን በተግባር እንዲፈጽሙ ስታደርግ ቆይታለች። ስታስተምርም ከመሥራቿ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሕይወትን መሠረት በማድረግ ነው። ቀድሞ በዘመነ ኦሪት፣ ከዚያም በዘመነ ነቢያትና ነገሥት በኋላም በዘመነ ሐዲስ ልጆቿ እግዚአብሔርን እንዲያውቁና ርሱን በማክበር እየታዘዙ እንዲኖሩ አድርጋለች።
ቤተክርስቲያን ኵላዊትና ዓለም ዐቀፋዊት እንደመኾኗ መጠን አንዲት ናትና በየትኛውም ዓለም ያሉ የሰው ልጆች ኹሉ በየሚግባቡበት ቋንቋ እግዚአብሔርን ዐውቀው እንዲያመልኩት ሳታስተምር የኖረችበት ጊዜ የለም፤ ይኹን እንጂ ዓለሙ የርሷን ድምጽ አልሰማ ብሎ ከእግዚአብሔር ይልቅ በዲያብሎስ ክፉ ምኞት እየተመራ አእምሮውን አጥቶ እያበደ ይገኛል፤ የቤተክርስቲያንን ድምጽ የሰሙ ግን በእግዚአብሔር መዳፍ ተደግፈው በኅሊና ዕረፍት በደስታ ይኖራሉ፤ እየኖሩም ነው። ታዲያ ለዚኽ ኹሉ ጉዞዋ ልጆቿ ተባብረው በፈጣሪዋ በእግዚአብሔር ረድኤት ዛሬ ላይ ደርሳለች፤ ቤተክርስቲያን ዓለም ዐቀፋዊት እንደመኾኗ ስለ ዓለም ዐቀፍ እንቅስቃሴ መጻፍም ኾነ መናገር የጊዜ ጉዳይ ኾኖ ስለሚገድበን ስለ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ትንሽ እንጠቁምዎ!
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን፥ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብለው ከሚያምኑ ከሕንድ፣ አርመን፣ ሶርያና ግብጽ አኀት ተብለው ከሚጠሩት አንዷ ናት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታዲያ በመግቢያችን እንደገለጽነው ልጆቿን ሰብስባ እያስተማረች ወደ መንግሥተ እግዚአብሔርም እንዲገቡ በተግባር እንዲፈጽሙ ማለትም በሥጋ ወደሙ እየታተሙ በጎ እገዛንም ለፍጥረት ኹሉ እንዲያደርጉ እያስደረገች ሲኾን በኢትዮጵያ በኹሉም ክልሎችና አካባቢዎች ልዩ ልዩ መዋቅሮችን በመዘርጋት አገልግሎቷን ለኹሉም ተደራሽ እያደረገች ነው፡፡

የሰንበት ት/ቤት ትርጕም

ሰንበት የሚለው ቃል በእብራይስጡ “ማቆም፤ ሰርቶ ማረፍ” የሚል ትርጉም አለው፡፡ እግዚአብሔር ስድስት ቀን ሠርቶ በሰባተኛው ቀን እንዳረፈ (ዘፍ2*2) እለተ ሰንበት በሥጋ አርፈን በመንፈስ የምንበረታበት (የዮሐ.ራዕይ 1*3) የእግዚአብሔርን ውለታ የምናስታውስበት (ዘጸ 20*10) መልካም በማድረግ የምንጠመድበት ዕለት ነው፡፡ (ማቴ 12*2)።
በዚኽ ዕለት የእግዚአብሔር ቃል የሚነገርበትና ውለታው የሚወሳበት ሥፍራ ሰንበት ት/ቤት ይባላል፡፡ በእረፍት ቀናቸው /በሰንበት/ መንፈሳዊ ትምህርት የሚማሩ በእግዚአብሔር ቤት እያደጉ ለዓለም ብርሃን የሚኾኑ የክርስቲያን ልጆች ደግሞ ሰንበት ተማሪዎች ይባላሉ፡፡

የሰንበት ት/ቤት ዓላማ

ሕፃናትን በምግባር ማሳደግ፤ ወጣቶችን በሃይማኖት ማጎልመስ እና የአባቶችን አደራ ተረክቦና ጠብቆ የሚያስረክብ ባለ ራዕይ ትውልድ መፍጠር ነው፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤት ጥቅም

፩. ሰንበት ትምህርት ቤት ሃይማኖቱን ጠንቅቆ ያወቀ መልስ ያለው ትውልድ ይፈጥራል፡፡
፪. ለቤተ-ክርስቲያንና ለሃገር የውስጥ ጉልበት፤ የውጭ ውበት የሚኾኑ ምርጥ ዜጎችን ያሥገኛል፡፡
3. ለቤተ-ክርስቲያን ተልዕኮዋን የሚያሳኩ እጆች፤ ጠላቷን የሚረቱ ኃይሎች የሚኾኑ ባለ ራዕይ ወጣቶችን ይቀርጻል፡፡
ሰንበት ትምህርት ቤት ክርስትናን በማስፋፋት ምንፍቅናን በመከላከል ዓለማ›ቀፋዊ እውቅና አለው፡፡ በሰንበት ት/ቤት ያደጉ ልጆች በሚሰማሩበት ሥፍራ የተሳካላቸውና በማኅበራዊ ሕይወት የተዋጣላቸው መሆናቸው ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ መሆኗን ያረጋግጣል፡፡ ሰንበት ት/ቤት ሥራ አስለምዳና ጸባይ አርማ ወደ ስኬት ተራራ የምታወጣን ደግ እናትን ትመስላለች፡፡ አበው እንደሚሉት እሳት ያልነካው ሸክላና በሰንበት ት/ቤት ያልተማረ ወጣት አንድ ናቸው፡፡

የሰንበት ት/ቤት አመሠራረት

በብሉይ ኪዳን “ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም እረፉ” (ዘጸ 20*10) በተባለው አምላካዊ ቃል መሠረት የአይሁድ ልጆች የእግዚአብሔርን ቃል በመስማትና ውለታውን በማሰብ ያከብሩት ነበር፡፡ በዓመትም ሦስት ጊዜ ልጆች ወደ አምልኮ ሥፍራ ይወሰዱ እንደነበር አሪት ዘጸአት 23*17 ያስረዳል፡፡ የነቢዩ ሳሙኤልን ታሪክ ስናስታውስ ደግሞ ልጆች በእግዚአብሔር ፊት በመቅደሱ ያድጉ እንደነበር እንረዳለን፡፡ (1 ሳሙ.3*1)
በሐዲስ ኪዳን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰማቸውና ሲጠይቃቸው በመቅደሱ መገኘቱ የሃይማኖት ልጆቹ በእግዚአብሔር ፊት ማደግ እንዳለብን አብነት ነው፡፡ ሉቃ 2*46 በሚያስተምርበት ጊዜም ሕፃናትን ማቅረቡ (ሉቃ 18*16) ልጆቻችሁ በፊቴ ይመላለሳሉ፤ ከቤቴ በረከትን ጠግበው ተንኮል በሌለበት ቃሌ ይደጉ ማለቱ እንደኾነ እንረዳለን፡፡
የመጀመርያዎቹን ክርስቲያኖች ሕይወት ስንመለከት ልጆቻቸው አብረው ተጉዘው የክርስትናንም የፍቅር ማዕድ ተካፍለው የአባቶቻቸውንም ሃይማኖት ወርሰዋል፡፡ ክርስትናው እየሠፋ ሲሄድ መከራም እየበዛ ሲመጣ ልጆችን በክርስቲያናዊ ዓላማና በሰማያዊ ራዕይ ማሳደግ ስላስፈለገ በ 200 ዓ.ም ገደማ በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤት ተመሠረተ፡፡
ዓለም አቀፋዊና ክርስቲያናዊ ከኾኑት የአንጾኪያና የእስክንድርያ ት/ቤቶች የሚወጡ ደቀ መዛሙርት ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማጠናከር ተጠቃሾች እንደኾኑ ታሪክ ይናገራል፡፡
ሀቢብ ጊዮርጊስን የመሰሉ ግብፃዊያን ዲያቆናት ወጣቶችን በሰንበት ትምህርት ቤት በማሰልጠን የእስክንድርያን ቤተ-ክርስቲያን ከመናፍቃን አድነዋል÷ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የቤተ-ክርስቲያን የውስጥ ጉልበት፤ የውጭ ውበት በመኾን ዓላማዋን ያሳካሉና፡፡

ሰንበት ት/ቤት በኢትዮጵያ

ትውልዱ ወደ ዘመናዊ ትምህርት በማዘንበል ሃይማኖቱን ችላ እንዳይል በማሰብ አባቶቻችን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን በማወቅ የሚያድግ፤ መልስ ያለው ትውልድ ለመፍጠር ከ 1935-1940 ዓ/ም ባለው ጊዜ ሰንበት ት/ቤትን በአዲስ አበባ መሠረቱ፡፡ በጊዜውም “ተምሮ ማስተማር” በሚል መጠሪያ ይታወቅ ነበር፡፡ ቀጥሎም በ 1953 ዓ.ም መመሪያ ወጥቶለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ትእዛዝ በየአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያኑ ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም የተደረገ ሲኾን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን በቃለ ዓዋዲው የሰንበት ት/ቤት አወቃቀር መመሪያ ተካተተ፡፡

ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled0

ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled9




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🚌  ጉዞ ወልድ ዋህድ  🚎

⛪️ ወደ ምድረ ከብድ
  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም


በዛውም በመንገዳችን ላይ
        አዳዲ ማርያምን እንጎበኛለን

 የጉዞ ዋጋ 800 ብር

     መነሻ ቀን    መጋቢት 4
     መመለሻ ቀን    መጋቢት 5
     መነሻ ሰአት      12 ሰአት

👉  ትኬቱን  በሰንበት ት/ቤቱ
       መዝሙር ቤት ያገኙታል

ለበለጠ መረጃ 📱 09 85 46 75 66
                           09 96 48 12 33
                           09 83 03 21 99
                                   ይደውሉ።

  👉በዚህ ጉዞ ላይ በመሳተፍ በረከት ያገኙ ዘንድ ፈጥነው ይመዝገቡ👈
              ‼️ ማሳሰቢያ:-  ቦታ ሳይሞላ ትኬቱን ገዝተው በእጆ ይያዙ ‼️


ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled0

ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled9






አዳዲስ እና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled0

እዲሁም
ቻናላችን ይቀላቀሉ

👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled9


🚌  ጉዞ ወልድ ዋህድ  🚎

⛪️ ወደ ምድረ ከብድ
  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም


በዛውም በመንገዳችን ላይ
        አዳዲ ማርያምን እንጎበኛለን

 የጉዞ ዋጋ 800 ብር

     መነሻ ቀን    መጋቢት 4
     መመለሻ ቀን    መጋቢት 5
     መነሻ ሰአት      12 ሰአት

👉  ትኬቱን  በሰንበት ት/ቤቱ
       መዝሙር ቤት ያገኙታል

ለበለጠ መረጃ 📱 09 85 46 75 66
                           09 96 48 12 33
                           09 83 03 21 99
                                   ይደውሉ።

  👉በዚህ ጉዞ ላይ በመሳተፍ በረከት ያገኙ ዘንድ ፈጥነው ይመዝገቡ👈
              ‼️ ማሳሰቢያ:-  ቦታ ሳይሞላ ትኬቱን ገዝተው በእጆ ይያዙ ‼️


ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled0

ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled9


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🚌  ጉዞ ወልድ ዋህድ  🚎

⛪️ ወደ ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት

 የጉዞ ዋጋ 600 ብር
ደርሶ መልስ
          16/06/2017 ዓ.ም 
👉  ትኬቱን  በሰንበት ት/ቤቱ
       መዝሙር ቤት ያገኙታል

ለበለጠ መረጃ 📱 09 85 46 75 66
                           09 96 48 12 33
                                   ይደውሉ።

  👉በዚህ ጉዞ ላይ በመሳተፍ በረከት ያገኙ ዘንድ
              ‼️ ፈጥነው ይመዝገቡ  ‼️

ግሩባችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇

https://t.me/weled0


🚌  ጉዞ ወልድ ዋህድ  🚎

⛪️ ወደ ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት

 የጉዞ ዋጋ 600 ብር
ደርሶ መልስ
          16/06/2017 ዓ.ም 
👉  ትኬቱን  በሰንበት ት/ቤቱ
       መዝሙር ቤት ያገኙታል

ለበለጠ መረጃ 📱 09 85 46 75 66
                           09 96 48 12 33
                                   ይደውሉ።

  👉በዚህ ጉዞ ላይ በመሳተፍ በረከት ያገኙ ዘንድ
              ‼️ ፈጥነው ይመዝገቡ  ‼️






💅ሰአሊ, Merry

የምትፈልጉትን የምታገኙበት group
ነው ጆይን በሉ ታተርፉላቹ
👇👇👇👇👇👇👇
@mezenagagroup1
@mezenagagroup1
👆👆👆👆👆👆👆👆
@Tsegayelove



Показано 20 последних публикаций.