Репост из: የሕይወት እምሻው ወጎች/ Hiwot Emishaw
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
‹‹ስለ እራቁት ነው እንዴ ?››
------
መቼ’ለታ እንደነገርኳችሁ አዳዲሶቹ መፅሐፎቼን ለመሸጥና ከአንባቢዎቼ ጋር ለመገናኘት ዛሬ ከሰአት በኋላ ሚሊኒየም አዳራሽ ተቀምጫለሁ፡፡
ብዙ ዓይነት ሰው አገኘሁ፤ ብዙ መፅሐፍት ሸጥኩ፤ ብዙ ሳቅኩ፡፡
ከሁሉ የገረሙኝን ምልልሶች መርጬ ላጋራችሁ፡፡
ለማስታወስ ያህል የቡና ቁርስ እና ለእርቃን ሩብ ጉዳይ የተባሉትን ሁለት መፅሐፎቼን ጠረጴዛ ላይ ደርድሬ ከአላፊ አግዳሚው ወደ እኔ የሚመጣውን ሰው ሰላም እያልኩ እያስተናገድኩ ነው፡፡
ሁለት ጠና ያሉ ዘናጭ ሴቶች ተጠጉኝ፡፡
አንደኛዋ ተገዳ የቆመች በሚመስል አኳኋን ከልቧ ሳትሆን ዙሪያ ገባውን ስታማትር ሌላኛዋ ለእርቃን ሩብ ጉዳይን አነሳችና፣
‹‹ሰላም›› አለችኝ፡፡
‹‹ሰላም›› መለስኩ፡፡
‹‹የራስሽ ታሪክ ነው ይሄ?››
‹‹አይደለም››
‹‹አናቃቂ ትምህርት ነው?››
‹‹ አይ አይደለም››
‹‹ታዲያ ምንድነው?››
‹‹አጫጭር ታሪኮች ናቸው፡፡ ልቦለድ››
‹‹ማለት?››
‹‹የፈጠራ ጽሁፍ››
‹‹ስንት ነው ዋጋው?››
‹‹ሶስት መቶ›››
‹‹አይቀንስም?››
‹‹ውይ እናትዬ አይቀንስም››
‹‹በይ እሺ በርቺ››
‹‹አመሰግናለሁ››
ሄዱ፡፡
አንዲት ወጣትና ቀጭን ልጅ ደግሞ ከሩቅ ስትበር መጣችና ልክ ጠጋ ብላ ስታየኝ
‹‹ውይ…ሜሪ ፈለቀን መስሽኝ ነበር››
‹‹አ…አይደለሁም››
‹‹አንቺ ማነው ስምሽ?››
‹‹ሕይወት››
‹‹እንደ ሜሪ ፈለቀ አይነት ነው የምትጽፊው …?››
‹‹እ….››
‹‹ሜሪ ፈለቀ የለችም እዚህ?››
‹‹እኔንጃ…አላየኋትም…እዚያ ጋር አዘጋጆቹ አሉ እነሱን ጠይቂያቸው››
በመጣችበት ፍጥነት ጥላኝ ሄደች፡፡
አራት ምርጥ ሽቷቸው ከእነሱ ቀድሞ የደረሰ ሂጃብ ያደረጉ ቆነጃጅት ተጠጉኝ፡፡
‹‹ለእርቃን ሩብ ጉዳይ…ስለ እራቁት ምናምን ነው እንዴ?›› አንደኛዋ ጠየቀችኝ፡፡
‹‹እ….›› አልኩ የምላት ግር ብሎኝ፡፡
‹‹ይሄኛውስ ስለምንድነው?…›› (የቡና ቁርስን አንስታ)
‹‹አጫጭር ታሪኮች ናቸው››
‹‹ሁለቱም ያንድ ሰው ናቸው?››
‹‹ አዎ…እኔ ነኝ የጻፍኳቸው››
‹‹እንዴ…አንቺ ነሽ ደራሲዋ?›› (ፊቷ እያበራ)
‹‹አዎ…››
ማሻላህ! (ሁለቱ ባንድነት)
‹‹ሴትንማ ማበረታታት አለብን እንግዛ››
‹‹ግዴለም ይሄ ራሱ ለእኔ በቂዬ ነው›› (አፍሬ)
‹‹እንዴ…እንገዛለን…የቡና ቁርሱ ስንት ነው?››
ሶስት የቡና ቁርስ ገዝተውኝ ከነመልካም ጠረናቸው ሄዱ፡፡
ደግሞ አንድ ተለቅ ያለ ሰውዬ መጣ፡፡
‹‹እንዴት ዋልሽ?› (ሁለቱንም መፅሐፍት አንስቶ እያየ)
‹‹ይመስገን ደህና››
‹‹ ምን ሆኛለሁ አለሽ?››
‹‹እ››
‹‹ምን ሆኛለሁ የሚለው መፅሐፍ…የትእግስት ዋልተንጉስ››
‹‹እ…አይ የራሴን ብቻ ነው የያዝኩት…››
‹‹እሺ…የዮሃንስ ሞላ አዲስ የግጥም መጽሐፍስ…?››
‹‹እሱንም አልያዝኩም…ሁሉም ደራሲ የራሱን ብቻ ነው የያዘው..ዮሃንስ ግን ያውልህ›› (ፊት ለፊቴ እየጠቆምኩ)
ግራ እንደተጋባ መፅሐፎቹን ቦታቸው መልሶ ወደ ዮሃንስ ሳይሆን ወደ አንሶላ መሸጫው ሄደ፡፡
ሰውየው ምን ሆኗል?
ደግሞ ሌላ ደልደል ያለ ሰውዬ ሰላም ብሎኝ ከተጠጋኝ በኋላ ፣
‹‹ስለምንድነው…ለምን መጻፍ ፈለግሽ…ማሳተም አይከብድም ወይ…ከዚህ በምታገኚው ገቢ ነው ኑሮሽን የምትገፊው….ለምን ስነልቦና ላይ አትፅፊም›› ብሎ በጥያቄ ጎረፍ ከመታኝ በኋላ የቱን ሊገዛ ይሆን ብዬ ስጠብቅ፣
‹‹በይ እሺ…እኔ እንኳን ፊልም እንጂ ንባብ ላይ እስከዚህም ነኝ›› ብሎኝ እብስ አለ፡፡
የሆነው ሆኖ የያዝኩትን መጽሐፍ ሁሉ ገዝታችሁ ለደገፋችሁኝ፣ ላበረታችሁኝ እና ላዝናናችሁኝ አንባቢዎቼ ሁሉ ቁና ሙሉ ምስጋና!
አልቋል ብዬ ለመለስኳችሁ ይቅርታ፤ ሁለቱም መፅሐፍ አሁንም ጃፋር ጋር ስለሚገኝ እዚያ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ቸር ይግጠመን !