"ወጣትነት በ ኢስላም"
ታላቁ የበድር ዘመቻ
ክፍል 2
☆የጦርነቱ ታሪክ
ኢብኑ ኢስሃቅ እንዳለው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም የተወሰኑ የረመዷን ወር ቀናት ካለፉ ነበር ለዚህ ተልእኮ የወጡት። ሰኞ ቀን ስምንት የረመዷን ወር ቀናት ካለፉ በኋላ ነበር። ዐብዱላህ ኢብኑ ኡም መክቱምን በመዲና ሰላት ላይ አቡ ሉባባን ደግሞ የመዲናን ሁኔታ እንዲቆጣጠርን እንዲያስተዳደር ሀላፊነት ሰጥተው ወጡ።
በወቅቱ የሙስሊሞች ቁጥር ሦስት መቶ አሥራ ሦስት ሰዎች ነበር። መቶ አርባ ምናምን የሚሆኑ ...