በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ማኖር መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሠረት በጎንደር፣ ደሴ፣ ሰቆጣ እና ፍኖተ-ሠላምን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ሕብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ ችግኝ እየተከለ ነው፡፡
የክልሉና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በመርሐ-ግብሩ ተገኝተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው 600 ሚሊየን ችግኞችን የማኖር መርሐ-ግብር እስከ ምሽት 12 ሠዓት የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በአለባቸው አባተ፣ ከድር መሐመድ እና ጳውሎስ አየለ
#አረንጓዴዓሻራ