፨
ዳገቱን ወጥተን ገደል ጫፍ ላይ ቆመናል... የ አየሩ ቅዝቃዜ ጉንጮቻችንን እየገረፈ ፤ በምቾት ከሞቀ ወፍራም ጃኬቶቻችን ውስጥ ፊታችንን ወሽቀን ለመቅበር እየተጨናነቅን ነው
አየሩ ደስ ይላል ፣ ቅዝቃዜው አልመጠን አለን እንጂ... ይሄ ሁሉ ፍጹም እንዲሆን የሚጠብቀው ጭንቅላታችን ይቺን ጊዜ አላጣፍጥ አለን እንጂ... ቦታው ያምር ነበር... ያምራልንጂ ፣ ከከተማ ርቆ በቀን የወፍ ዝማሬ የሚሰማበት... ቦታ። የደኑ ቀለማት አረንጓዴ ቢባል የሚቀልበት አረንጓዴዎች ቢባል የሚቀልበት ታይቶ ቢቆጠር የማያልቅ አይነት ልዩነት ያለበት ቀለም... ተፈጥሮ በለው ፈጣሪ ተጠበው ብሩሽ እያማረጡ የሳሉት የሚመስል ደመና... የተለቀመ መልክዓምድር... ገደል
እኔ ማስበው እንዴት ነው የሚበርደው ደሞ መቼ ነው የምንሄደው መምሸቱም አይቀርም ፣ አንድ ቦታ መቆም የማያውቅ ጭንቅላት አስቸጋሪ ነው...ይሮጠዋል አንተ እሱን ስትከተል ሳትውል ይመሽብሃል.....
ከመምሸቱ በፊት ግን ቅዝቃዜው ሲበረታ የ ስራ መውጫ ሰዓታቸው የደረሰ የቀን ሰራተኞች ከ ላይኛው ዳገት መውረድ ጀመሩ ፣ በትከሻቸው የያዙት ባህላዊ የመቆፈሪያ መሳሪያ የተሸከመው ጭቃ ከላይ የደረቡትን ሹራብና ጃኬት እያቀለመ ፣ ሲሰሩ የዋሉበት ወዝና አቡዋራ የጠገበ ቁምጣቸው የጎማ ጫማቸው ላይ የተጣበቁ የጭቃ ቅንጥብጣቢዎች በተራመዱ ቁጥር ረገፍ ረገፍ እያለ እኛ ጋር ደረሱ... እኛ ይሄን ውበት ልናይ ሰገነት ላይ የቆምነው በድን አካላችን የተገተረው ሰዎች ጋር ደርሰው ከነተሸከሙት ከባድ መሳሪያ ጋር ያዩትን ነገር በመገረም ይመለከታሉ... ሁሉም በ አግራሞት...
ያነቃኝ ነገር የአለምን ሁሉ ሸክም እንደተሸከመ ሰው ከፊቴ ያለውን ውበት እንዳላየ መሆኔ ነበር
ደስታ እያለ ፣ ማረፍ እያለ መሄድን መምረጥ...
ካልለቀቅነው የማይለቅ በሽታ ፣ ወይ መድሃኒት?
ውሃ
https://t.me/wuhachilema