ዘመኗን በሙሉ በዝማሬዎቿ ባርካናለች። በሊሊ ዝማሬዎች ያልተፅናና ፣ ጌታን ያላመለከ ፣ ብዙ ምድረበዳዎችን የሷን ዝማሬዎች እየሰማ ያላለፈ አማኝ አለ ማለት አይቻልም። አሁን ይህች ድንቅ ዘማሪት ቁጥር 7አልበሟን በማጠናቀቅ ላይ ሳለች የተወሰኑ መዝሙሮች ተሰርቀው በonline ገበያወች ተለቀዋል። ይህ ፈፅሞ ከአንድ ክርስቲያን ነኝ ከሚል አካል የሚጠበቅ አይደለም። ተራ የሌብነት ስራ ነው። አልበሙን በህጋዊ መንገድ የገዛው ሰው ነገሩን ወደ ህግ ሊወስደው እንደሆነ ሰምተናል። እኛም ደግሞ ሊሊን የምንወዳት ከሆነ አልበሙ በትክክል እስኪወጣ ድረስ ብዙ ተለፍቶበታልና ያለፍቃድ የተለቀቀውን ባለመስማት እንተባበር ዘንድ በፍቅር እንጠይቃለን!
@Yedestaye_elilta ✅
@Yedestaye_elilta ✅