ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_፰
...ከጓደኞቼ መሀል ማንም እንዳላየኝና እንዳልተከተለኝ አረጋግጬ እርምጃዬን ቀጠልኩ...እንደዚ አይነት ድፍረት ከየት እንዳመጣው ባላውቅም ደፋር ሆኛለሁ...ባትሪዬ የሚያሳየኝ አቅጣጫ እንጂ ሌላው በከባድ ፅልመት ተውጧል ፀጥ ያለ የሚለው ቃል እስከማይገልፀው ድረስ ፀጥ ብለሏል የደረቀውን ቅጠል ስረገጠውና ስተነፍስ ከሚሰማው ድምፅ በቀር አንዳች የለም...አሁን እየሄድኩበት ያለውን አቅጣጫ ፈፅሞ አላውቀውም ከገባንበት ፈፅሞ ተቃራኒ ነው እናም ስመለስ እንደምቸገር ለራሴ ታውቆኛል...በቀዝቃዛው ለሊት ብቻዬን ከድቅድቁ ጨለማ ጋር ግብግብ ገብቻለሁ...ከእርምጃዎች በሗላ ከኔ ሌላ በጫካው ውስጥ የእግር ኮቴ ተሰማኝ ባትሪውን አጥፍቼ ባለሁበት ቁጭ አልኩኝ ትኩረቴን ሰብስቤ የኮቴውን አቅጣጫ ለማወቅ ትኩረት ማድረግ ጀመርኩ...አረማመዱ ከሰው ይለያል የሚሰነዝረው እርምጃ ሰፋ ያለ ነው የሚረግጣቸው የረጋገፉ ቅጠሎች ይጨነቁ ይመስል ይጮሃሉ...አሁንም ከየት በኩል እየመጣ እደሆነ አለየሁትም...ቀስ ብዬ ባትሪውን መሬት ላይ እንዳስቀመጥኩ አቅጣጫውን ያለሁት እርምጃ ቀጥ አለ በጣም ደነገጥኩኝ እቺን ትንሽ ኮሽታ ሰምቶ እንዳይሆን ብዬ ራሴን ጠየኩት...ለደቂቃዎች ፀጥ አለ ጫካው እርምጃውም ቆሟል የሱን እንቅስቃሴ እንደምጠብቅ እሱም የኔን እንቄስቃሴ እየጠበቀ ይመስለኛል...አንድ ውሳኔ ለመወሰን ከራሴ ጋር ተስማማሁ እዚ ቁጭ ብሎ ጊዜ መፈጀቱ ዋጋ ቢስ እንደሆነና እርምጃዬን መቀጠል እንዳለብኝ...ከዛም ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ባትሪው አብርቼ ዙሪያዬን ቃኘው አንዳች ነገር የለም ከዛም እርምጃዬን ፈጠን አድርጌ ወደፊት ቀጠልኩ ነገር ግን የሆነ ነገር አሁንም እርምጃዬን አስቆመኝ ከኔ ሌላ አሁንም የኮቴ ድምፅ ይሰማኛል ከቅድሙ የፈጠነ አረማመድ እየቀረበኝ መጣ አሁን አቅጣጫውን ለይቼዋለሁ ከፊት ለፊቴ ነው ወደኔ ሚገሰግሰው ባትሪው ከኔጋ ቢቆይ አቅጣጫ ጠቋሚ እንደሆነ እና የሚከታተለኝም ነገር ብርሃኑን አይቶ እንደሆነ ግልፅ ሆኖልኛል ከዛም ባትሪው ወደ ግራ አቅጣጫ ወርውሬ እኔ በሱ ተቃራኒ ከአንድ ዛፍ ስር ተደበኩኝ በሰከንዶች ልዩነት ሲከታተለኝ የነበረው ባትሪው ጋ ደረሰ ከፊት ለፊቱም ብርሃኑ ላይ ቆመ ረዘም ያለ ጥቁር ካፖርት ለብሷል ቁመቱ ለግላጋ ይመስላል ባትሪው ግማሽ አካሉ ላይ ስላረፈ ፊቱን ማየት አልቻልኩሜ ነበር...ይመስለኛል ከባትሪው ጀርባ የሆነ ሰው እንዳለ አስቧል ለዛም ነው መሰለኝ ከፊት ለፊት ለማስፈራራት በሚመስል አረማመድ ከግራ ወደ ቀኝ ይንጎራደዳል ከዛም ካፖርቱን ገለጥ አደረገና ረዘም ያለ የሚያንፀባርቅ ሰይፍ መሳይ ስለት አወጣ ይሄን ባየው ጊዜ በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ "እ" አልኩኝ ወዲያውኑ አፌን በእጆቼ ያዝኩኝ እሱም አቅጣጫውን እኔ ወዳለሁበት አደረገ ቀስ እያለም እየተራመዳ መቅረብ ጀመረ ከዛፉ በስተሗላ እኔም ቀስ ብዬ ተነሳሁ እርምጃዬን ከሱ እርምጃ እኩል አድርጌ ወደ ሗላ መሸሽ ጀመርኩ በድንገት እግሬ ውስጥ እሾክ መሰለኝ ተሰነቀረብኝ ህመሙን ዋጥ አድርጌው ዝም አልኩኝና ማፈግፈጌን ቀጠልኩ የምራመደው ወደሗላ ነበርና የወጋኝም ተረከዜን ነው በለዘበ እርምጃ እየተጠጋኝ ነው እኔም እርምጃውን ጠብቄ እያፈገፈኩኝ ነው...ነገር እሾሁ ረጅም ነበርና በተራመድኩ ቁጥር ወደ ውስጥ ይገባብኝ ጀመር ትንሽ እንደተራመድኩ ተለቅ ያለ እንጨት ጋ እንደደረስኩ በእግሬ ንክኬ ለየሁ ፊቴን ወደ እንጨቱ አዙሬ ነካካሁት የወደቀ ዛፍ ነበር ቀስ ብዬ በላዩ ላይ አለፍኩና ከስሩ ተኛሁ እርምጃዬንም ድምፄንም አጠፋሁ ነገር ግን ህመሙን አልቻልኩትም ይከተለኝ የነበረው ነገር ድንገት ወደሗላ ተመለሰ ግን ለምን እንደሆነ አልገባኝም ከተኛሁበት ጥንቃቄ በተሞላው አነሳስ ቀና ብዬ መመልከት ጀመርኩ የሰውዬውን ማንነት ባለይም እንኳን...ትንሽ ከተጓዘ በሗላ ልክ እንደቅድሙ ባትሪው ፊት ለፊት መንጎራደድ ጀመረ...ህመሜ ግን ከብርዱ ጋር ተደምሮ ስቃዬን አበዛው በጫማዬ ውስጥ የገባውን እሾህ ለመንቀል ወሰንኩ አሁንም ቢሆን ግን አይኔን ከሰውዬው ላይ አልነቀልኩም...እዛ ቦታ ላይ ሚንጎራደደው ጠቋሚ ድምፅ እስኪሰማ ይመስለኛል የለበስኩትን ሹራብ አወለኩና እጁን ጠቅልዬ አፌ ውስጥ ከተትኩት ከዛም እሾሁን ለመንቀል ተዘጋጀሁ...በጣም ማለክለክ ጀመርኩ ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ ማለት ጀመረ ጨከን አልኩና ትንሽ ጎተት አደረኩት እጅግ በጣም ያማል ቢሆንም ግን መውጣት ነበረበትና መጎተቴን ቀጠልኩ እስከ ግማሽ ድረስ አወጣሁትና ሹራቤን ከአፌ አውጥቼ ትንሽ ተነፍስኩ ልቤ ጥፍት ብላለች ወደ ሰውየው ተመለከትኩ አሁንም እዛው ይንጎራደዳል ሹራቤን መልሼ አፌ ውስጥ ከተትኩና መጎተቴን ተያያዝኩት ሙሉ ለሙሉም ነቀልኩት እንደነቀልኩትም ከተጋደመው ዛፍ ስር ራሴን ጥዬ ተኛሁ ሲውጣ የነበረው ህመም እጅግ ያማል ትንሽ ደቂቃ ተኛሁና ራሴን አረጋጋሁ ከዛ ቀና ብዬ ሳይ ....................
_Part #9 __ይቀጥላል
ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱