ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_፱
....ሰውዬውም ባትሪውም የለም በጣም ደነገጥኩኝ የሆነ ነገር እያሰበ እንዳለ በውስጤ ይታወቀኛል ከተደበኩበት ቦታ በእርጋታ ተነስቼ በፊት ወደነበርኩበት ስፍራ ተመለስኩ ተረከዜ አላስረግጥ ብሎ ያስነክሰኛል በዛ ላይ ደሜ መቆም አልቻለም... ወዲያውኑ በሰከንድ ልዩነት ተደብቄ የነበርኩበት የወደቀ ዛፍ ጋ ባትሪው በራ በዛው ቅፅበት መጥረቢያውም ተሰነዘረ በዛ ቦታ ብሆን ምን እንደምሆን አሰብኩት...በቦታው አለመኖሬን ሲመለከት እና ሲያጣኝ በጣም ተበሳጭቶ ባትሪውን መሬት ወርውሮ "ዛሬ ማንም አያመልጠኝም" እያለ እየተውተረተረ ማውራት ጀመረ እንዳጋጣሚ የወደቀው ባትሪ ሙሉ ከወገብ በላይ እሱ ላይ ያበራበት ጀመር ረዘም ያለ ኮፊያ ያለው ካፖርት ለብሷል ነገር ግን ፊቱን ለመለየት ያዳግታል ኮፊያው ግማሽ ፊቱ ድረስ ሸፍኖታል ወዲያው የተደበኩበት ስፍራ ጋር ዝቅ ብሎ እጁን ወደ መሬት ሰንዘሮ ወደ አፍንጫው መለሰው ይመስለኛል ደሜን እያሸተተ ነው ከዛም ከመቅፅበት ተነስቶ ቀጥ ብሎ ቆመ አፍንጫውንም እያንቀሳቀሰ ማነፍነፍ ጀመረ በዚ ሰዓት የሆነ መንገድ መጠቀም እንዳለብኝ ተረዳሁ ከውስጥ የለበስኩትን ቦዲ ቀስ ብዬ አውልቄ መልሼ ጃኬቱን ለበስኩት ተረከዜንም በቦዲው አሰርኩት ሽቶ ስለነበረው የደሜን ሽታ ይሸፍንልኛል ብዬ በማሰብ ሰውዬው አሁንም እያነፈነፈ ነው ከዛም እርምጃ ጀመረ እኔም ካለሁበት ተነስቼ ወደ ሌላ መደበቂያ መሄድ ጀመርኩ ባትሪው እዛው አሁን በሙሉ ጨለማው ውስጥ እኔና ሰውዬው እየተሳደድን ነው...ድንገት እርምጃው ቆመ እኔም እርምጃዬን አቆምኩ ይመስለኛል ከሱ ሌላ የእግር ኮቴ እንዳለ ተረድቷል እኔ ገብቶኛል ነገር ግን መቆም እየተሳነኝ ነው ምክንያቱ ደግሞ እሾህ በወጋው እግሬ ነው የቆምኩት በጤነኛው እንዳልቀይር ሰውዬው ኮሽታ እየጠበቀ ነው እርምጃውን ካቆመ በጣም ቆየ እግሬ መንቀጥቀጥ ጀመረ እንዳጋጣሚ አጠገቤ ዛፍ ነበርና እንዳልወድቅ በመዳፌ ተደገፍኩ እርምጃው ጀመረ ግን ቅድም ከነበረው ፍጥነት ጨምሯል ቦዲዬ በደም ተጨማልቋል የሽቶው ሽታ እንደጠፋ ይታወቀኛል ሰውዬውም ደሜ ሸቶት መሰለኝ በፍጥነት እየመጣ ነው እኔም እያነከስኩ ፍጥነቴን ጨምሬ መሸሽ ጀመርኩ በጣም እየቀረበኝ ከኔና ከሱ ሌላ ጫካ ውስጥ ኮቴ ተሰማ ይሄንን ኮቴ እንደሰማ ይመስለኛል እሱ ባለበት ቆሟል እኔ ግን ሽሽቴን ቀጥያለሁ ወዲያውኑ የሚጮህ የእንስሳ ድምፅ ሰማሁ ይመስለኛል ጥቃት ሲያደርስበት ነው የጮኸው በዚ ክፍተት መሀል እግሬ ላይ ያሰርኩትን ቦዲ ፈትቼ ከምጓዝበት በተቃራኒ መንገድ ወረወርኩት ከዛም ጉዞዬን ወደፊት አደረኩ ያለ ማቋረጥ ብዙ ተጓዝኩኝ ነገር ግን ኮቴው አልተከተለኝም ነበር የዛሬው ለሊት የሶስት ቀን ያህል ረዝሞብኛል የእግሬን ህመም መቋቋም አልቻልኩም ግን ቢሆንም ግን አልቆምኩኝም ነበር በዛው እሾህ በወጋኝ በኩል አንዳች ነገር እግሬ ውስጥ ተሰነቀረብኝ ድምፄንም አውጥቼ ጮውኩኝ ህመሙ ከቅድም እጅግ እጥፍ ነበር አልቻልኩም እግሬን ይዤ እየተንከባለልኩ ደጋግሜ ጮውኩኝ ጮውኩኝ አልቻልኩም ከእሾኩ የባሰ ስለት አለው ውስጥ ድረስ እየቆራረጠኝ ነው የገባው የቱም የህመም ስሜት አይገልፀውም ነፍሴ እግሬ ላይ ያለች ይመስል ትንፋሽ አጠረኝ መላ አካላቴ መብረክረክ ጀመረ የእግሬ እንቅጥቃጤ ቃል አይገልፀውም እየተንፏቀኩኝ ለመሄድ ግን አልቻልኩም ካንዱ ዛፍ ስር ተደገፍኩኝ ነፍሴ ዛለች የተወጋው እግሬን ወደራሴ ይዤ አንዱ እግሬ ጉልበት ላይ አኖርኩት የተሰነቀረብኝን ነገር ስነካው እጅግ በጣም ያማል ቀስ አድርጌ ወደነበረበት መለስኩ ጎህ እየቀደደ ነው እዚ ጫካ ውስጥ ፀሀይ ካልወጣች ወገግታ ብቻ ብርሃን አይሰጠውም ግን ፀሀይ ወጣች መሰለኝ ውስጡ መታየት ጀምሯል ሌላ አለም ያለው እስኪመስለኝ ድረስ ጨነቀኝ ዙሪያ ገባዬን ከግራ ከቀኝ ቃኘው ምንም አልነበረም ፀሀይ አብዝታ ባታፈካው እስከ ሆነ ርቀት ድረስ ያለውን ነገር የምለይበት ብርሃን አለ...ማንም እንደሌለ ባስተዋልኩ ጊዜ ራሴን ለማረጋጋት ወሰንኩ ከደቂቃዎች በሗላ ከተደገፍኩት ዛፍ ላይ ቅጠሎች መርገፍ ጀመሩ ቀና ስል ...........
_part #10 _ ይቀጥላል
ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱