ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋውሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_፲
...ምን እንደሆነ ያለየሁት ነገር ከአንዱ ዛፍ ወደ ሌላው ሲሸጋገር ተመለከትኩ ሰውዬው በአቅራቢያዬ እንዳለ ይሰማኛል ጀርባዬን ዛፉ ላይ የሙጥኝ አስደግፌ ወደላይ ማንጋጠጤን ተያያዝኩት...ሰውነቴ በፍራቻ ይርዳል ቁስሌ ልቤ ስንጥቅ እስክትል እያስጨነቀኝ ነው ...ወደ ጆሮዬ የሹኩሹክታ ድምፅ ወደኔ መጣ "መፍራትሽ እውነት ነው" የሚል ነበር ከዛ ጫካው በሚያስፈራ የሳቅ ድምፅ ተሞላ ከየት እንደሚመጡ ማላስተውላቸው ድምፆች ያስጨንቁኝ ጀመር "ሞተች ሞተች" ይላሉ ደጋግመው ድምፅ እየቀያየሩ አንዴ በህፃን አንዴ በአዋቂ ድምፅ እያረጉ ለደቂቃዎች ካስጨነቁኝ በሗላ ጫካው ፍፁም ፀጥታ ወረሰው ከኔ ትንፋሽ ውጪ ምንም አይሰማም...አሁን ባለሁበት ሁኔታ ምንም ነገር ቢፈጠር ራሴን ለማዳን የምችልበት ምንም አቅም የለኝም ሁሉንም በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ድንገት ሳላስበው ጥቁር የሞተ ቁራ ከየት መጣ ሳልልለው እግሬ ስር ወደቀ ድምፄንም ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ ግን ወዲያውኑ አፌን ይዤ ድምፄን አጠፋሁና ግራ ቀኜን ቃኘው ምንም አልነበረም ከዛም እይታዬን ሁሉ ቁራው ላይ አደረኩ በስህተት ነጭ የሚባል ቀለም የለበትም ሙሉ ጥቁር ነው በሚያስገርም ሁኔታ ደግሞ ሁለቱም አይኖቹ የሉም...የአይኖቹ ስፍራ ጎድጎዳነት እንኳን የላቸውም በጣም ደነቀኝ አይቼው የማላውቀው ልዩ ፍጡር ሆነብኝ አንገቴን አስግጌ በመገረም እና በፍራቻ ውስጥ ሆኜ እየተመለከትኩት ሳላ እግሩ መንቀሳቀስ ጀመረ ልብ ምቱም ትርታ ጀመረ መሰለኝ ትንፋሽ ያስገባና ያስወጣ ጀመረ ሁኔታው አስገርሞኝ የማየውም ነገር አጠራጥሮኝ ከአይኔ ይሆናል ብዬ ጨፍኜ ገለጥኩት ግን አይኔን ስገልጠው ሌላ ያልጠበኩት ነገር ተከሰተ ቁራው ተነስቶ መጮህ ጀመረ በድንጋጤ እየጮህኩኝ ወደ ሗላ ስመለስ ተደግፌበት የነበረው ዛፍ አናቴን ክፉኛ መታኝ ጉጥ የሚባለው ነገር ነበረበትና በጣም ጎድቶኛል ከመቅፅበት ደሜ በጀርባዬ ላይ መውረድ ጀመረ ግን እዛው ቦታ ላይ ሆኜ ሰዓት አላጠፋሁም የቱንም ያህል መጓዝ ባልችልም ግን የነበኩበት አልነበርኩም በደረቴ እየተንፏቀኩ መሸሽ ጀመርኩ ቁራው አሁንም መጮሁን አላቆመም ይብሱኑ የሱን ድምፅ ተከትሎ ሙሉ ጫካው ተናወጣ ተንጫጫ የቅድሞቹ ሽኩሽታዎች በዋይታና በሲቃ ድምፅ ታጅበው ነፍሴን አወኳት ባለሁበት በደረቴ ተኝቼ ጆሮዬን በእጆቼ ድፍን አደረኩት ትንሽም ቢሆን ድምፁን ቀንሶልኛል ግን ከዛ አካባቢ መራቅ ስለነበረብኝ ወዲያውኑ ጆሮዬን ለቅቄ ጉዞዬን ጀመርኩ ከጭንቅላቴ የሚፈሰው ደም ወደ አገጬ እና አንገቴ መውረድ ጀመረ ልብሴ በራሴው ደም ጨቀየ ያም ሆነ ይህ ግን ነፍሴን ለማትረፍ እየተውተረተርኩ ነው በደረቴ እየተንፏቀኩ...ትንሽ እንደተንፏቀኩ ቀኝ ታፋዬ ላይ አንዳች ነገር ስምጥጥ ብሎ ሲገባ ተሰማኝ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ በጀርባዬ ተንጋልዬ እንደ ህፃን ልጅ አነባው ከዛም ቀና ብዬ ተመለከትኩት የአጥር ሽቦ ነበር ሱሪዬን ከገላዬ እኩል ሰንጥቆታል ቀስ ብዬ ቀና አልኩና ተቀመጥኝ የተሰነቀረብኝንም ለመንቀል ተያያዝኩት ግን እጄ እየተብረከረከ ነበርና ምንም ሊመቸኝ አልቻለም እንባዬ ከአይኔ ዱብ ዱብ ይላል ደሜ ከጭንቅላቴ ላይ ይወርዳል አሁን ሸቦው የቀደደው እግሬ ነጩ እስኪታይ ዘልልቆ ሰንጥቆኛል በዛ ላይ ጠማማ ነው መሰለኝ እንደ ወስፌ የውስጥ ስጋዬን ይዞታል ስቃዬ እጅግ በዛ ቀስ ብዬ በጀርባዬ ተንጋለልኩ አይኖቼም መስለምለም ጀመሩ አቃተኝ...ትንሽ እንደተኛሁኝ እጅግ ፈጣን የእግር ኮቴ ተሰማኝ እዛው በተኛሁበት ስመለከተው ጥቁር ከስክስ ጫማ ማድረጉን ተመለከትኩ ከተኛሁበት በድንጋጤ ተነስቼ ስዞር...........
_part #11 ___ ይቀጥላል
ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱