ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_17
...የሚሆነውን ሳስበው አንቀጠቀጠኝ ለማየትም ለመስማትም ሰቀጠጠኝ...በድን የመሰለኝ የሮቤል አካል መንቀሳቀስ ጀመረ እንደ ማሳልም ሲያረገው ከአፉ ደም ይረጫል ይሄን ባየ ጊዜ ያ ሰው ይበልጥ ደስ አለው ከሚሰማው ጫጫታ ይልቅ ይሄ ለሱ ደስታ ሰጥቶታል ጠጋ ብሎ አይን አይኑን እደተመለከተ ፈገግ ይላል በሌላ በኩል ሮቤል በለዘበ እና በቀሰስተኛ ድምፅ "እርዱኝ አድኑኝ ይላል" ይሄን መመልከት ለኔ እጅግ በጣም ከባድ ነው የማደውን ነገር ማመን አልቻልኩም እጄን አፌ ላይ አድርጌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩኝ አቅም ቢኖረኝና ከዚ አረመኔ ሰው ባስጥለው ፍፁም ደስተኛ ነበርኩ ነገር ግን አልችልም...ሰውዬው አሁንም ዋይታ በሞላው የሰዎች ጫጫታ በደስታ እና እረፍት የተሰማው በሚመስል መልኩ ይንቀሳቀሳል የዘይቱን መፍላት እየተመላለሰ ይመለከታል ለምን እንደጣደው ባይገባኝም ብቻ አስፈርቶኛል...ሮቤል ሙሉ ለሙሉ ሰውነቱ በደም ተጨማልቋል ከቅንድቡ ትንሽ ከፍ ብሎ በስለት የተቆረጠ የሚመስል ቁስል አለ ይመስለኛል እኔ የተመለኩት ያ የተሰበረ መስታወት ሮቤል ለማምለጥ ሲል የሰበረው እንደሆነ ተረዳሁ ሳሩ ላይ የተመለከትኩት ደም ደሞ ከመስኮቱ ከወደቀ በሗላ ለማምለጥ በደረቱ የተሳበበት እንደሆነ ገባኝ ሁኔታዎቹን ከሮቤል መጥፋት ጋር ማመሳሰሌ ትክክል ነበርኩ ይሄን ሁኔታ ቅድስቴ አለመመልከቷ ለሌሎቻችን በህይወት መቆየት ምክንያት ነው...ብትመለከት ኖሮ ራሷን ማረጋጋት ስለማትችል ሁላችንም እንጠመድ ነበር...ሮቤል አሁንም ድምፁን እያሰማ ነው አረመኔው ሰውዬ ደግሞ እየደነሰ...እንቅስቃሴው ሁሉ ግራ ነው ጨፈረ ለማለት እንኳን አያስደፍርም...ከደቂቃዎች በሗላ የዘይቱን መፍላት አረጋገጠ ከዛም እየሳቀና እንደ ጭፈራ የሚያረገውን እንቅስቃሴ እያሳየ ወደ ሮቤል ተጠጋ ሁለት ተለቅ ያሉ ጥቋቁር ቀበቶ መሳይ ማሰሪያዎችን አንስቶ አንዱን ደረቱጋ አንዱን ደሙ ታፋው ጋር አድርጎ ከጠረጴዛው ጋር ሮቤልን የፊጥኝ አሰረው...የሮቤልን ስቃይ ለመረዳት ሮቤልን መሆን አልነበረብኝም ህመሙ አብዝቶ አመመኝ ስቃዩ አሰቃየኝ ወዲያውኑ ትሪ መሳይ በሆነው ነገር ካመጣቸው ስለቶች መሀል ሁለቱን አንስቶ ወደሰማይ እየተመለከተ ማፋጨት ጀመረ የዘይቱ መፍላት እኔ እስካለሁበት ቦታ ድረስ ሲፍለቀለቅ ይሰማል ብቻ እንደማስበው አይሁን ብዬ አምላኬን ተማፀንኩኝ..."እርዱኝ አድኑኝ እርዱኝ አድኑኝ" እያለ ሮቤል የማይደርስለትን አዳኝ ይጣራል አረመኔውም ሰውዬ አንድ ጣቱን አፉ ላይ አድርጎ ዝም እንዲል ለሮቤል በምልክት ያሳየዋል ነገር ግን ሮቤል የሚረዳውን ሰው ከማያገኝበት ስፍራ መጣራቱን ይቀጥላል በዚ ግዜ ሰውዬው አብዝቶ ይናደድና ሲያፋጭ የነበረውን ስለት ከፍ ሲያረገው አሁን ካሁን አንዳች ቦታ ላይ ወጋው ስል ከፍ ካደረገበት እጁን ሳይመልስ በንዴት የተለዋወጠው ፊቱ ወደ መጀመሪያ ገፅታው ተመልሶ በተረጋጋ ስሜት ሆኖ አሁንም አንድ ጣቱን ከንፈሩ ላይ አድርጎ ዝም እንዲል ይነግረዋል...ከዛ ከጋለ ስሜት ውስጥ መውጣቱ ለኔ በጣም ግራ ነው ሰውዬው በጣም አጠራጣሪና አወዛጋቢ በሆኑ ነገሮች ነው የተሞላው...ዶክተሮች የሚጠቀሙበትን የህክምና ጓንት ከአንዱ መሳቢያ አውጥቶ እጆቹ ላይ አጠለቀ በመሃል የከፈተው ዋይታ ፀጥ አለ እሱም እዛው የቆመበት ቦታ ለይ ሳይንቀሳቀስ ፀጥ ብሎ ቆመ ሰከንዳት አልፈው ደቂቃዎች ተቆጠሩ እንደዛው ካለበት ሳይንቀሳቀስ ፀጥ ብሉ እንደቆመ...በዚ ሰዓት ሮቤል አንዳች ድምፅ ቢያወጣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰላሰል ጀመርኩ ይሄን እያሰብኩኝ ሳለ የቅድሟ ድመት እየጮኸች ወደክፍሉ ስትገባ ከቆመበት ተስፈንጥሮ መጥረቢያውን አንስቶ ወገቧን ብሎ ለሁለት ከፈላት ከቅድሙ ይልቅ አሁን አፌን አጥብቄ ያዝኩ ሰውዬው እዛው ድመቷ የሞተችበት ቦታ ላይ በድጋሜ ፀጥ ብሎ ቆሟል አይኑ እንኳን አይርገበገብም ከደቂቃዎች በሗላ የዋይታው ድምፅ ጀመረ መጥረቢያውን ትከሻው ላይ አድርጎ እያፏጨ መንቀሳቀስ ጀመረ ትንሽ ተንፈስ አልኩኝ ምን ሲያቀብጠኝ ወደዚ ክፍል እንደመጣሁ አላውቅም እዛው ከጓደኞቼ ጋር ሆኜ የሚሆነውን ብጠብቅ ይሻለኝ ነበር...መጥረቢያውን የነበረበት ቦታ ላይ አስቀምጦ ድመቷን ከወደቀችበት አንስቶ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ከተታት ያደረገውንም ጓንት አውልቆ ከድመቷ በድን ጋር አብሮ ጣለው ከዛም አዲስ ጓንት ለማድረግ ወደ መሳቢያው ተጠጋ አውጥቶም በዋይታው እየተንቀሳቀሰ ማድረግ ጀመረ ከዛም ከተሰጡት የዶክተሮች ጋውን አንዱን አንስቶ ለበሰ ከዛም ፈገግ እያለ እየቆለፈ ራሱን በራሱ መመልከት ጀመረ በጣም ደስ ያለው ይመስላል እጁን ኪሱ ከቶ ወደዛ ወደዚ መንጎራደድ ጀመረ ጓንት ወዳወጣበት መሳቢያ በድጋሜ ሄዶ መነፅር አውጥቶ አደረገ አሁን የባሰ ፈገግ አለ የሚያረገው ነገር ትንሽም ቢሆን ከፍራቻዬ አውጥቶ በአግራሞት ዝም ብዬ እንድመለከተው አደረገኝ ደረቱን ነፍቶ አሁንም መንጎራደዱን ቀጠለ ነገር ግን ሙዚቃው በድጋሜ ፀጥ አለ እሱም ባለበት ቦታ እጁን ኪሱ እንደከተተ ቆመ እኔም እቺ ደቂቃ እስክታልፍ አፌን አፍኜ ያዝኩኝ ነገር ግን ሮቤል......
part #18 ___ ይቀጥላል
ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱