አንድ ባለትዳርና የስድስት ልጆች አባት የሆነ ጎልማሳ ኦሾ ጋር ይመጣና “በዘመኔ ሌላ ሴት ተመኝቼ አላውቅም በፍፁም! አሁን ግን አንዲት ሴት ማለም ከጀመርኩኝ ውዬ አድሬያለሁ፤ የአርባ ስምንት አመት ጎልማሳና የስድስት ልጆች አባት በዚያ ላይ ባለትዳር ሆኜ ሳለ ወደ ሌላ ሴት የመሳቤ ነገር ተገቢ ነው ትላለህ ?” ይለዋል።
ኦሾም “ይልቁኑስ ተገቢ የማይሆነው ለአርባ ስምንት አመታት ራስህን ጨቁነህ መኖርህ ነው፤ ለዚህ እኮ ነው ወደ ሴት ልጅ መሳብ የጀመርከው። የሴት ቁንጅና ሲታይህ ወደ ወጣትነትህ ተመለስህ ማለት ነው። ዛፎች ለምልመው ፣ አበቦች አብበው ፣ አታክልት አፍርተው ስታይ አልኖርህምን ሴትስ በውበቷ ተገልጣ አምራ ብትታይህ ችግሩ ምንድን ነው ? ፍርሃትህ የፍጥረትን ቁንጅናን እንዳያስክድህ ተጠንቀቅ..”
፦ O S H O