መንትዮቹ ክፍል 1
#እውነተኛ_ታሪክ
እኔ ልእልና እባላለሁ እህቴ ደግሞ ትህትና ትባላለች
መንታ ነን የተወለድነው # ዝዋይ የምትባል ከተማ
ውስጥ ነው። ወላጆቻችን በጣም የሚዋደዱ ቢሆንም
እናታችን ባንድ ቀን ሁለት ወንድሞቿንና ወላጆቿን
በድንገተኛ አደጋ በማጣቷ የትነሽ ብሎ የሚፈልጋት
ዘመድ ስለሌላት የአባታችን ቤተሰቦች በማለት አባታችን
እንዳያገባት ቢከለክሉትም እሱ ግን ከልቡ ይወዳት
ስለነበር ከቤተሰቡ ተጣልቶ ከሷጋር መኖር ጀመረ
እኛም ተወልድን አባትታችን እኔን # ልእልና እህቴን
# ትህትና አለን እናታችን እኔን ሉሌ እህቴን ትሁት
እያለች ትጠራን ነበር። ህይወት በዚህ መልኩ
አልቀጠለም። ገና 2 አመት እንኳን ሳይሞላን
የአባትነት ፍቅሩንና ጠረኑን ሳንጠግበው አባታችንን
ሞት ነጠቀን።
በፊትም ለአይናቸው ይጠሏት የነበሩት የአባታችን
ቤተሰቦች እናቴ ሀዘኗን እንኳን በቅጡ ሳትቋቋም አንቺ
ነሽ ልጃችንን የገደልሽው እያሉ መቆሚያ መቀመጫ
አሳጧት። እናቴም በዚህ ተማራ እንኖርበት የነበረውን
የቤተሰቦቿን ሰፊ መኖሪያ ቤት እንዲሁም ከከተማ
ወጣ ብሎ የሚገኘውን የቤተሰቦቿን መሬት ሁሉ ሽጣ
ጓዟን ጭና እኛን ይዛ አዲስ አበባ ገባች። ለጊዜው
ቤት ተከራይታ የሚሸጥ መኖሪያ ቤት አፈላልጋ ውጪ
ሀገር ሊሄዱ እቤት የሚሸጡ ሰዎች አግኝታ ከነሱ ላይ
ሰፊ ጊቢ ያለው አሁን የምንኖርበትን ቤት ገዝታ ኑሮ
ጀመርን።
እናቴ በጣም ጠንካራ ሴት ናት ተስፋ መቁረጥ
የሚባል ነገር አታውቅም። በቀራት ገንዘብ ደግሞ
አራት የሚሆኑ ሰርቪስ ክፍሎችን ጊቢውስጥ
አሰራች። ለኛም እኛን የምትጠብቅ ሰራተኛ ቀጥራልን
እሷ ስራ ማፈላለግ ጀመረች ብዙም ሳትቆይ
ኢትዮ_ቴሌ ውስጥ ኦፕሬተርነት ተቀጠረች።
የሰራቻቸውን ሰርቪሶችም አከራይታ ስለነበር ጥሩ ገቢ
አላት እኛም እያደግን መጣን ትምህርት ቤት ገባን።
እኔና እህቴ በጣም ከመመሳሰላችን የተነሳ እንኳን
የውጪ ሰው የገዛ እናታችን እንኳን የቷ ልእልና የቷ
ትህትና እንደሆንን እንምታታባት ነበር። ደግሞም አንድ
አይነት ልብስ አንድ አይነት ጫማ አንድ አይነት የፀጉር
እስታይ ስላለን ማንም አይለየንም ነበር። እህቴ
ጓደኛዬም ጭምር ናት እሷም እኔም የሴት ጓደኛ
የለንም ተያይዘን ትምህርት እንሄዳለን ተያይዘን
ወደቤት እንገባለን ክፍላችንም አንድ ላይ ነው
የምንቀመጠውም ጎን ለጎን ነው። በትምህርታችንም
በጣም ጎበዝ ተማሪዎች ነበርን ከክፍል ወደ ክፍል
ስንሸጋገር ክፍል ብንለያይ እንኳን ሁለታችንም
ስለምናለቅስ እናታችን አስተማሪዎቹን ለምና አንድ
ላይ ታስደርገን ነበር። እናታችን ከእናትነትም በላይ
እንደጓደኛችን ነበር የምናያት ከሷ የምንደብቀው
ሚስጥር የለንም። ቢከፋንም ብንደሰትም ቢያመንም
ሁሉ ነገራችን እናታችን ብቻ ናት። እሷም ያለኛ ማንም
የላትምና ፍቅራችን በቃላት የሚገለፅ አልነበረም።
እንዲ እንዲ እያልን ሀይስኩል ደረስን ዘጠነኛ ክፍል
ላይ ግን ከእህቴ ጋር ክፍል ተለያየን አንድ ላይ
እንዲያረጉን ብንጠይቅም አይሆንም ተባልን። እኛም
ምንም ማድረግ ስለማንችል በእረፍት ሰዓት አብረን
እየሆንን መማር ቀጠልን ሁለታችንም ኮስታሮች
ስለነበርን ማንም ደፍሮ አይቀርበንም ነበር። ወደ
አስረኛ ክፍል ከተሸጋገርን በኃላ ግን ከተማሪዎች ጋር
እየተግባባን መጣን እኔም እህቴም አንድ አንድ የሴት
ጓደኞች ከየክፍላችን ያዝን የኔ ጓደኛ ሜሮን ትባላለች
የእህቴ ጓደኛ ደግሞ አይናለም ትባላለች። በእረፍት
ሰዓት አንድ ላይ እየተሰበሰብን ደስ የሚል ጊዜ
እናሳልፋለን።
በዚህ ጊዜ ነበር ዛሬም ድረስ በፀፀት ጅራፍ ስገረፍ
እንድኖር ያደረገኝ ነገር የተፈጠረው..............
|__________ይቀጥላል............
@yefikir_menorya
@girumneg
#እውነተኛ_ታሪክ
እኔ ልእልና እባላለሁ እህቴ ደግሞ ትህትና ትባላለች
መንታ ነን የተወለድነው # ዝዋይ የምትባል ከተማ
ውስጥ ነው። ወላጆቻችን በጣም የሚዋደዱ ቢሆንም
እናታችን ባንድ ቀን ሁለት ወንድሞቿንና ወላጆቿን
በድንገተኛ አደጋ በማጣቷ የትነሽ ብሎ የሚፈልጋት
ዘመድ ስለሌላት የአባታችን ቤተሰቦች በማለት አባታችን
እንዳያገባት ቢከለክሉትም እሱ ግን ከልቡ ይወዳት
ስለነበር ከቤተሰቡ ተጣልቶ ከሷጋር መኖር ጀመረ
እኛም ተወልድን አባትታችን እኔን # ልእልና እህቴን
# ትህትና አለን እናታችን እኔን ሉሌ እህቴን ትሁት
እያለች ትጠራን ነበር። ህይወት በዚህ መልኩ
አልቀጠለም። ገና 2 አመት እንኳን ሳይሞላን
የአባትነት ፍቅሩንና ጠረኑን ሳንጠግበው አባታችንን
ሞት ነጠቀን።
በፊትም ለአይናቸው ይጠሏት የነበሩት የአባታችን
ቤተሰቦች እናቴ ሀዘኗን እንኳን በቅጡ ሳትቋቋም አንቺ
ነሽ ልጃችንን የገደልሽው እያሉ መቆሚያ መቀመጫ
አሳጧት። እናቴም በዚህ ተማራ እንኖርበት የነበረውን
የቤተሰቦቿን ሰፊ መኖሪያ ቤት እንዲሁም ከከተማ
ወጣ ብሎ የሚገኘውን የቤተሰቦቿን መሬት ሁሉ ሽጣ
ጓዟን ጭና እኛን ይዛ አዲስ አበባ ገባች። ለጊዜው
ቤት ተከራይታ የሚሸጥ መኖሪያ ቤት አፈላልጋ ውጪ
ሀገር ሊሄዱ እቤት የሚሸጡ ሰዎች አግኝታ ከነሱ ላይ
ሰፊ ጊቢ ያለው አሁን የምንኖርበትን ቤት ገዝታ ኑሮ
ጀመርን።
እናቴ በጣም ጠንካራ ሴት ናት ተስፋ መቁረጥ
የሚባል ነገር አታውቅም። በቀራት ገንዘብ ደግሞ
አራት የሚሆኑ ሰርቪስ ክፍሎችን ጊቢውስጥ
አሰራች። ለኛም እኛን የምትጠብቅ ሰራተኛ ቀጥራልን
እሷ ስራ ማፈላለግ ጀመረች ብዙም ሳትቆይ
ኢትዮ_ቴሌ ውስጥ ኦፕሬተርነት ተቀጠረች።
የሰራቻቸውን ሰርቪሶችም አከራይታ ስለነበር ጥሩ ገቢ
አላት እኛም እያደግን መጣን ትምህርት ቤት ገባን።
እኔና እህቴ በጣም ከመመሳሰላችን የተነሳ እንኳን
የውጪ ሰው የገዛ እናታችን እንኳን የቷ ልእልና የቷ
ትህትና እንደሆንን እንምታታባት ነበር። ደግሞም አንድ
አይነት ልብስ አንድ አይነት ጫማ አንድ አይነት የፀጉር
እስታይ ስላለን ማንም አይለየንም ነበር። እህቴ
ጓደኛዬም ጭምር ናት እሷም እኔም የሴት ጓደኛ
የለንም ተያይዘን ትምህርት እንሄዳለን ተያይዘን
ወደቤት እንገባለን ክፍላችንም አንድ ላይ ነው
የምንቀመጠውም ጎን ለጎን ነው። በትምህርታችንም
በጣም ጎበዝ ተማሪዎች ነበርን ከክፍል ወደ ክፍል
ስንሸጋገር ክፍል ብንለያይ እንኳን ሁለታችንም
ስለምናለቅስ እናታችን አስተማሪዎቹን ለምና አንድ
ላይ ታስደርገን ነበር። እናታችን ከእናትነትም በላይ
እንደጓደኛችን ነበር የምናያት ከሷ የምንደብቀው
ሚስጥር የለንም። ቢከፋንም ብንደሰትም ቢያመንም
ሁሉ ነገራችን እናታችን ብቻ ናት። እሷም ያለኛ ማንም
የላትምና ፍቅራችን በቃላት የሚገለፅ አልነበረም።
እንዲ እንዲ እያልን ሀይስኩል ደረስን ዘጠነኛ ክፍል
ላይ ግን ከእህቴ ጋር ክፍል ተለያየን አንድ ላይ
እንዲያረጉን ብንጠይቅም አይሆንም ተባልን። እኛም
ምንም ማድረግ ስለማንችል በእረፍት ሰዓት አብረን
እየሆንን መማር ቀጠልን ሁለታችንም ኮስታሮች
ስለነበርን ማንም ደፍሮ አይቀርበንም ነበር። ወደ
አስረኛ ክፍል ከተሸጋገርን በኃላ ግን ከተማሪዎች ጋር
እየተግባባን መጣን እኔም እህቴም አንድ አንድ የሴት
ጓደኞች ከየክፍላችን ያዝን የኔ ጓደኛ ሜሮን ትባላለች
የእህቴ ጓደኛ ደግሞ አይናለም ትባላለች። በእረፍት
ሰዓት አንድ ላይ እየተሰበሰብን ደስ የሚል ጊዜ
እናሳልፋለን።
በዚህ ጊዜ ነበር ዛሬም ድረስ በፀፀት ጅራፍ ስገረፍ
እንድኖር ያደረገኝ ነገር የተፈጠረው..............
|__________ይቀጥላል............
@yefikir_menorya
@girumneg