ላፈቀረ ብቻ 5683:
✍"ደኻ ወርቅ አይግዛ" 🔍
ክፍል 2 (ካለፈው የቀጠለ)
😀ሳቃችንን ሳንጨርስ ‹ቆይ ቆይ
እስኪ› አለች አዲሴ ጆሮዋን እንደ አንቴና ሰቅላ፡፡ መቼም ከአራት ኪሎ ሠፈር ጯሂና አስጯሂ አይጠፋም ብለን ጸጥ አልን፡፡ አራት ኪሎ ጠብና ዕርቅ የተለመደ ነው፡፡ ተደባዳቢና ገላጋይ በየተራ ነው፡፡ ዛሬ ትደባደባለህ፣ ነገ ደግሞ በተራህ ገላጋይ ትሆናለህ፡፡ ሁላችን ኮንዶሚኒየም ላይ እንደተሰቀለ ዲሽ ጆሮአችንን አከታትለን ብንሰቅልም የመንገደኛ ተረብ ብቻ ነው የምንሰማው፡፡ አዲሴ ተነሣችና ሳንዱቁ ላይ በልብስ ተሸፍኖ የተቀመጠውን ራዲዮ እስከ አንጀቱ ድምጹን ለቀቀችው፡፡ አበደች እንዴ ብለን በግራ ዓይናችን ገላመጥናት፡፡
‹ዛሬ በዋለው የዓለም ገበያ› ይላል ራዲዮኑ፡፡ እርሷ እዚያው እንደተለጠፈች ናት፡፡ እዚህ አራት ኪሎ ያለው የጉልት ገበያ የሚናፍቃት ሴትዮ የዓለም ገበያ ምን ሊያደርግላት ነው ብለን ሳቅን፡፡ ለወትሮው በዱቤ የሰጧት እንዳያንቋት ገበ ድርሽ አትልም ነበር ነበር፡፡ እንዲያውም እማማ ትጓደድ ‹አዲሴኮ ገበያ ብቻ ሳይሆን ገበያው የሚባል ሰውም ትፈራለች› እያሉ ይተርቧት ነበር፡፡ ራዲዮው ‹ዛሬ በዓለም ገበያ ወርቅ በካራት ይህን ያህል ተሽጧል› ሲል ‹እንዴው በደኅና ጊዜ ባልገዛ ይቆጨኝ ነበር፡፡ ለካስ ሰው ልጁን ወርቁ፣ ወርቂቱ፣ ወርቄ፣ ወርቅ አገኘሁ፣ ወርቅ አለማሁ፣ ጥሩ ወርቅ፣ አመለ ወርቅ እያለ የሚጠራው ወርቅ እየተወደደበት ነው› አለችና የግራ እጅ መዳፏን በቀኝ አራት ጣቶቿ ደበደበችው፡፡
ከዚያ በኋላ አዲሴን ማን ይቻላት፡፡ ከሱቅ በዱቤ ዕቃ ስትወስድ እንደ ድሮው መለመን፣ መለማመጥ ቀረ፡፡ ‹ማነህ ባለ ሱቅ፣ እስኪ አንድ አምስት ኪሎ ስኳር አምጣ› ትለዋለች፡፡ ‹እንዴ እማማ አዲሴ፣ በኋላ ባይከፍሉኝስ፤ ያለፈውን በመከራ አይደል እንዴ የከፈሉኝ› ሲሏት ‹ያለፈው አለፈ፣ በቃ እናንተ ሰው ይቀየራል ብላችሁ አታስቡም፤ አምጣ ባክህ፣ ቢበዛ ወርቄን ሽጬ እከፍልሃለሁ› ትላቸዋለች፡፡ ኧረ እንዲያውም አንድ ቀን አንድ ቄስ በዚያ ሲያልፉ ጠራቻቸውና ‹ዛሬ ሲያቃዠኝ አድሯል ይርጩኝ› ትላቸዋለች፡፡ ‹የክርስትና ስምሽ ማነው› ይሏታል ‹እኅተ ወርቅ› ትላቸዋለች፡፡ ቄሱ ደንግጠው ‹እኅተ ማርያም› ማለትዎ ነው› ይሏታል፡፡ ቀኝ እጇን ወደ ጎን እያውለበለበች ‹እርሱ የነዛ የነዛ ስም ነው› አለቻቸው፡፡ ‹ታድያ እኅተ ወርቅ፣ አይ፣ ያልተማረ ሰው ሰጥቶዎት እንዳይሆን› ይላሉ ያልገባቸው ቄስ፡፡ ‹ይኼው ነው አባቴ፣ካልተረዱት ይተውት› አለቻቸው፡፡
ይቀጥላል፡፡
ለአስተያየትዎ፡- @E5683
Share በማድረግ ለወዳጅዎ ያካፈሉ፡፡
@yesakal
@Yesakal