1. ገንዘብህን በብልሃት አስተዳድረው!
ብዙ ሰዎች ገንዘብ ማግኘት ይችላሉ፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው እንዴት በትክክል ማስተዳደር እንዳለበት አይማርም።
የፋይናንስ ብልህነት (Financial intelligence) የሚጀምረው በገቢና ወጭህ መካከል ያለውን ልዩነት ከመረዳት ነው። ከምታወጣው የበለጠ ገቢ እንዳለህ አረጋግጥ ፣ ይህም የበለጠ ሀብታም ያደርግሃል ።
2. መጀመሪያ ራስህ ላይ ኢንቨስት አድርግ!
ብዙ ሰዎች የሚያገኙትን ገንዘብ የሚያውሉት እዳቸውን ለመክፈል ነው።
ብልህ ሰው ግን ሁልጊዜ ከሚያገኘው ገቢ ውስጥ
- ኮርሶችን ለመውሰድ
- መጽሐፍት ለመግዛትና
- ልምድ ለመውሰድ ያውላል።
3. ቁጠባ እና ኢንቨስት ማድረግ የተለያዩ ናቸው!
መቆጠብ ግዴታ እና ጥሩ ልማድ ተደርጎ ይቆጠራል። ነገር ግን ገንዘብህን ከዋጋ ግሽበቱ በበለጠ በሚያድግበት ነገር ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያስፈልግሀል።
መቆጠብ የገንዘብን የመግዛት አቅም ሲያዳክም ኢንቬስትመንት ግን የገንዘብን ዋጋ ይጨምራል።
4. በአንድ የገቢ ምንጭ ላይ ብቻ ጥገኛ አትሁን!
ብዙ ሰዎች በአንድ የገቢ ምንጭ ላይ ብቻ ጥገኛ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ከሆንክ በፍፁም ሀብታም መሆንና የገንዘብ ነፃነት ላይ መድረስ አትችልም።
ተጨማሪ ገንዘብ የምታገኝበት ሌላ አማራጭ ሊኖርህ ይገባል።
5. ሪስክ በመውሰድ ብልህ ትሆናለህ!
በህይወትህ ሪስክ እስካልወሰድክ ድረስ ማደግ አትችልም።
በህይወት ውስጥ አንዳንድ እድሎች የህይወትህን አቅጣጫ የመቀየር አቅም ስላላቸው ሪስክ መውሰድ አለብህ።
6. ማንኛውም ሰው የገንዘብ እውቀት ሊኖረው ይገባል!
በዓለም ዙሪያ ያለው የትምህርት ሥርዓት የሚያሳዝነው ነገሩ ለገንዘብ መሥራትን የሚያስተምር መሆኑ ነው።
የትምህርት ስርዓቱ ገንዘቡን እንዴት ማግኘት፣ ማስተዳደር እና ጠብቆ ማቆየት እንደሚቻል በጭራሽ አያስተምርም።
ማንኛውም ሰው ሀብትን እንዴት መፍጠር እንደሚቻል መማርና የፋይናንስ ነፃነትን ለማግኘት እቅድ ማውጣት አለበት።
7. አስተሳሰብ ሁሉም ነገር ነው!
ደሃ አባቴ ሁልጊዜ እንዲህ ይለኝ ነበር "ይህን ለመግዛት አንችልም "ሀብታም አባቴ ግን "እንዴት መግዛት እንደምችል?" ያስተምረኛል። .
በዚህ መንገድ አፍራሽ አስተሳሰብህን ወደ አወንታዊ አስተሳሰብ ቀይረው። ይህን ስታደርግ በእርግጠኝነት ግብህን ለማሳካት መንገዶችን ታገኛለህ።
የአንተ አመለካከት እና አስተሳሰብ ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ነው።
ማንኛውንም ነገር ለማድረግ የመጀመሪያው እና ዋናው ነገር በራስህ ማመን ነው።
8. ከአንተ የበለጠ ብልህ በሆኑ ሰዎች ራስህን ከበብ!
‘በክፍሉ ውስጥ በጣም ብልህ ሰው ከሆንክ፣ የተሳሳተ ክፍል ውስጥ ነህ።’ የሚል በጣም ታዋቂ አባባል አለ።
ብልህ መሆን ከፈለግክ ከአንተ የበለጠ ብልህ በሆኑ ሰዎች እራስህን ከበብ።
9. ስሜቶችህን ተቆጣጠር!
ስሜትህን መቆጣጠር በማትችልበት ወቅት ሁኔታው በጣም የከፋ ይሆናል። ይህ መመሪያ በግል እና በሙያ ህይወትህ ልትተገብረው የሚገባ ነው።
ስኬታማ ቀን ይሁንልን 🙏🙏🙏