#ድህነትን_ተማርኩት
አንድ በጣም ሃብታም የሆነ አባት ለልጁ ከሚያቀስመው የህይወት ልምድ ትምህርት አንዱ ድህነት ምን እንደሁ እንዲያውቅ ማስቻል ነበር። እንደ ዲታው ሃሳብ ከሆነ ልጁ ስለድህነት ካወቀ፤ ድሃ እንዳይሆን በመስጋት ለገንዘቡ ጥንቃቄ ያደርጋል የሚል ግንዛቤ አለው። ሃብታም አባት ልጁን ከደሃ ገበሬዎች ጋር ቆይታ እንዲያደርግ ላከው።
ልጁ 3ቀንና ሶስት ሌሊቶችን ከገበሬዎች ጋር ቆይቶ ወደ ከተማው የሃብታምነት የቅንጦት ህይወቱ ሲመለስ....
አባቱ "ጥሩ ልምድ ቀሰምክ?" ሲል ጠየቀ።
ልጁ:- " አዎ አባ!"
አባት:- "እናም ምን ተማርክ?"
ልጁም እንዲህ ሲል መለሰ....
"በቆይታየ ያየሁት...."
1 – እኛ አንድ ውሻ አለን እነሱ አራት አላቸው።
2 –እኛ የጓሮ አትክልታችን ጋር የሚደርስ የመዋኛ ገንዳና የታከመ ውሃ አለን... እነሱ ደግሞ ኩልል ያለ ውሃ ያለው ወንዝ በውስጡ አሳዎችንንና ሌሎች ውብ ነገሮችን አቅፎ አላቸው።
3- እኛ ግቢያችን ላይ የኤሌክትሪክ ማብራት አለን እነሱ ደግሞ ደማቅና ያማሩ ከዋክብትና ጨረቃ አላቸው።
4 – የኛ የአትክልት ቦታ እስከግቢያችን አጥር ድረስ ብቸ ሲወሰን የነሱ ግን እስከ አድማስ ተንጣሏል።
5 – እኛ ምግባችንን እንሸምታለን እነሱ ያመርቱታል።
6 – እኛ ከስፒከር የሚወጣ የሙዚቃ ዜማን ስንሰማ... እነሱ ግን ተፈጥሮኣዊ የሆነ የዛፎችን ሽውሽውታ፣ የአዕዋፍትን ጥዑመ ዜማ፣ የፏፏቴዎችን ጭርጭርታና የእንስሳቱን ህብረዜማ ያጣጥማሉ። ምናልባትም ይሄ ሁሉ በስራ ላይ ባለ አንድ ጎረቤት ገበሬ እንጉርጉሮ አለያም በእረኛ የዋሽንት ስርቅርቅታ ይታጀብና ነፍስን ሰማየ ሰማያት ወስዶ በቀስተ ዳመና ያንሳፍፋል።
7 – እኛ በማይክሮ ዌቭ ስናበስል የእነሱ በእንጨት ዝግ ብሎ የሚበስል ምግብ ግን እንኳን ጣዕሙ መኣዛው አካባቢውን ያውዳል።
8 – እኛ ራሳችንን ከአደጋ ለመከላከል በአደገኛ አጥር ተከልለን ስንኖር እነሱ ግን አጥር አልባ ህይወታቸውን በወገኖቻቸውና ጎረቤቶቻቸው ፍቅር ተጠብቆ ይኖራሉ።
9 –የኛ ህይወት ከስማርት ስልኮች፣ከኮምፒውተሮችና ከቴሌቪዥኖች ጋር ሲቆራኝ የነሱ ደግሞ ከኑሮ፣ ከሰማይ፣ከፀሃይ፣ ከከዋክብት...አጠቃላይ ከተፈጥሮ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አላቸው።
አባት በልጁ ስሜት ተደነቀ። ልጁም ሃሳቡን እንዲህ ሲል ቋጨ "አባዬ ምንያህል ደሃዎች እንደሆንን እንድገነዘብ ስለረዳሃኝ አመሰግናለሁ...በየእለቱ የበለጠ እየደኸዬን እንደምንሄድም ተረድቻለሁ....ምክንያቱም የፈጣሪ ዕፁብ ድንቅ ስጦታ ከሆነው ተፈጥሮ እየራቅን ስለመጣን!"
__
አበቃሁ.....መልካም የናቶች ቀን🙏🙏🙏
ሁሌም ምንጊዜም ሠላም ሁኑልኝ🙏🙏🙏🙏
ቴሌግራም
👇👇👇
https://t.me/yinuca