ዛሬ ኀሙስ ነው!
ያሬድ ጌታቸው (ጃጆ)
ሰው የአቅሙ ልክ ነው፤ ሰው መሆን የሚችለው በሰውነት ልክ ነው ።
በቤተመንግስት ወይንም ክልክል በሆነ ቅጥር አጠገብ ስታልፍ ... ተመለስ!፣ ተሻገር!፣ ቁም! ብሎ እንደሚያባንን አይነት ጩኸት የቀላቀለ ድምፅ ሁሉ የሕይወት ውጣ ውረድ ፈተናዎች ሕይወት በደመነፍስ በለመደችው ተመሳሳይ መስመር እንዳትጓዝ እንደ ማንቂያ ደወልም ናቸው።
የተለመደ አይነት የሕይወት ዘዬ እንደአቀባበላችን አሰልቺ ሊሆን ድብርት በእኛነታችን ላይ የሰርክ ዳሱን ሊጥል ይችላል። ብዙ ሰው እስከአዕምሮ ሕመም የሚያደርስ ጭንቅ ድብርት ውስጥ የሚገባው በሕይወቱ አዲስ ነገር ማጣትና የነገሮች ድግግሞሽ፣ ደገጋግሞ በሕይወት መፈተን፣ ድንገቴዎችን መቋቋም አለመቻል፣ ስኬት ላይ አለመድረስ እንደ ሰው መድከም አቅም ማጣት ሊሆን ይችላል።
የፈጠረን አምላክ እኛን ሊረዳ ሊያግዘን በድካማችን ምርኩዝ ሊሆነን ግድ የሚለው አምላክ ነው። አንዳንድ ፈተናዎች ግን አቅማቸው ራስ ላይ እስከማሰጨከን ይደርሳሉ። ግን አንድ እውነት አለ ሰው የአቅሙ ልክ ነው። ሰው ፈጣሪውን መምሰል እንጂ መሆን ልኩ አይደለም። ሰው የአቅሙ ልክ ነው፤ ሰው መሆን የሚችለውም በሰውነት ልክ ነው። እኛ ብለን ብለን ያቃተንን የሕይወት ፈተና በቃ እኔ አልቻልኩም ብለን ሊረዳን ይችላል ብለን ለምናምነው ሰው ከሌለም ሰው አቅም በላይ ሲሆን፥ አልያም ምስጢር ይሁን ብለን ውስጣችን የቀበረነው እውነት ከሆነ፣ አምነን ሁሉ ገሀዱ ለሆነው ፈጣሪ አሳልፎ መስጠት ተገቢ እንደሆነ ይሰማኛል።
የራሴን ልምድ ልንገራችሁ ፍፁም በነገሮች ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሰልችቼ፣ ተደብሬ አውቃለሁ ፈተናዎች ሰዋዊ አቅሜን ሲፈታተኑኝ ግን በእኔ አቅም እንደማልመልሰው ሳውቅ ሁኔታዎችን ተቀብዬ ምፀልየው አንድ ፀሎት አለ።
"ፈጣሪዬ የምችልበትን አቅም ብቻ ስጠኝ!" የሚል ነው።
ሰው ያጣውን ይጣ፣ መንፈሱ ከፍና ዝቅ ይበል፣ ሰው ራሱን ግን ማጣት እንደሌለበት የተገባ ነው። ሰው የራሱ ብቻ አይደለም ሰው የፈጠረው፣ ሰው የሚኖርለት፣ የሚኖርበት ሁሉ ነው። በራስ ላይ ሲከፋ በሞት አርፋለሁ ብሎ የከፋው ድካም ውስጥ መገኘት ሲያልፍም ለሌሎችም የቁም ሕመም መብሰልሰልም ጥሎ ሊያልፍ ይችላል።
ሰው የመጣበትን አላማ ከዳር ማድረስ ባይችል በሙከራ ውስጥ ማለፍ ሌላው አሸናፊነት ነው። እናም ለጊዜው ድብርትም መሰላቸቱም አሸናፊ መሰሎ ቢታይ እንጂ ፈተና ሁሉ እንዲያባራ ዝናብ ነው።
ሕይወት መንታ መንገድ ላይ አቁማ ግራ ብታጋባህም ውሳኔ ትፈልጋለች። ውሳኔው ግን ራስን በማትረፍ ውስጥ ለሌሎችም መትረፍ አንተነትን ለነገ አሳልፎ በማኖር ላይ የተቃኘ ሊሆን ይገባል ።
አንድ ትልቁ ነገር፥ ሰው እንደአማኝ ፈጣሪ መኖሩን ለሚቀበል ሰው በራሱ ላይ ስልጣን እንደሌለው አምኖ መቀበል ይፈልጋል። ያኔ ፈጣሪው እንዲረዳው አምኗል ማለት ነው።
ፈተና ሲመጣ ከመጋፈጥ በላይ ቀድሞ በሕይወት ሊመጡ የሚችሉ ፈተናዎችን ቀድሞ ማሰብ ደግሞ አርቆ መፃይ ሁነቶችን የመረዳት ሌላኛው አቅም ነው። ፈተና መፈተኑ ባይቀርም ለተዘጋጀ ማንነት ግን እንግድነቱ እምብዛም ነው። ሰው በምድር ምልልሱ ብዙ ሆኗል በሌሎች የፈተናን ጥግ በሚመስል ደረጃ በመንፈሳዊ አስተምህሮት እንዲሁም በሕይወት የቀሰምነው ልምድ እኛ ለሚገጥመን ፈተና የማለፊያ ጥበብም ጭምር ነው።
በፈተና ውስጥ በትዕግስትና በጥበብ ልናልፍ የተገባ ነው። ይኽ ምክር አሁን ላይ ላለሁበት የስሜት ከፍ ዝቅ ለእኔም ጭምር ነው!
ደግሞም ...
“ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥13
ሁሉም ቀን ደስ ይላል!