♡ አባ ኪሮስ ♡
በአምላክ ፍቅር ዋሻ ገባህ
እረድኡ ነህ ለአባ መርሙዳ
ተገዛችልህ ዓለም ተገዳ (፪)
ትሰግዳለህ ለፈጣሪህ
ስትራዳ ደካማውን
ተሸከምከው አምላክህን (፪)
መዝሙር
በቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
አባ ኪሮስ አባታችንገንዘብን ሥልጣንን ንቀህ
ስምህ ገድልህ ተነሳ አሁን
መገለጫህ ዘመኑ አሁን ነው
ተአምርህን እያየነው ነው
ተአምርህን እየሰማን ነው
በአምላክ ፍቅር ዋሻ ገባህ
እረድኡ ነህ ለአባ መርሙዳ
ተገዛችልህ ዓለም ተገዳ (፪)
ዲላሮስ ነበር ስምህወገብህን በአጭር ታጥቀህ
መንፈስ ቅዱስ ኪሮስ አለህ
ለብዙዎች አባት ሆነሃል
ጸሎትህ ሙት አስነስቷል (፪)
ትሰግዳለህ ለፈጣሪህ
ስትራዳ ደካማውን
ተሸከምከው አምላክህን (፪)
ይሰራል ቃልኪዳንህ
አምላክህ የገባልህ
ለመካንዋ ታሰጣለህ ልጅ
ድንቅ ስራህ በዓለም ይታወጅ (፪)
መዝሙር
በቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ