በደብረ ዘመዳ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ለሚገኙ 80 የአብነት ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ።
ታኅሣሥ ፳፮/ ፳፻፲፯ ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን
በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በራያ ቆቦ ወረዳ ስር ለምትገኘው ለደብረ ዘመዳ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ለሚገኙ 80 የቅዳሴ ጉባኤ ቤት ተማሪዎች የምግብ ቁሳቁስ በትናንትናው ዕለት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
በማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ማእከል የጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ መለሰ አያሌው እንደገለጹት ማእከሉ ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚገኙ በጎ ፍቃደኛ ምእመናን የሰበሰበውን ድጋፍ ማድረጉን የገለጹ ሲሆን አሁን ካለው የኑሮ ውድነት እና የሰላም እጦት አንጻር ጉባኤ ቤቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመሆናቸው በተጠናከረ ሁኔታ ተጨማሪ ድጋፎች ሊደረጉ ይገባል ብለዋል።
በተመሳሳይም መሰል ድጋፍ በጋዞ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር ለሚገኘው የዋሮ ቅዱስ ሚካኤል ለ30 የዜማ ጉባኤ ቤት የአብነት ተማሪዎችም ተበርክቷል በዚህም በአጠቃላይ ለሁለቱም ጉባኤ ቤቶች 170‚000 (ከአንድ መቶ ሰባ ሺ ብር በላይ ወጭ መደረጉን ተገልጿል፡፡