1386 አዳዲስ አማንያን የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን አገኙ።
ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
በደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ዳሰነች ወረዳ 1386 አዳዲስ አማንያን በማኅበረ ቅዱሳን የሐዋርያዊ ተልእኮ አስተባባሪነት የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል።
ተጠማቂያኑ ባለፉት ወራት መሠረታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ሲማሩ ከነበሩ ወገኖች መካከል ሲሆኑ ሥርዓተ ጥምቀታቸው በኦሞ ብሔረ ብፁዓን አቡነ ዜና ማርቆስ ወአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንድነት ገዳም ዛሬ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈጽሟል።
በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተገኝተው ሥርዓቱን ፈጽመዋል።
ቅድመ ጥምቀት ሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፋፊያ እና ሥርዓተ ጥምቀት ማስፈጸሚያ ተግባራት ሙሉ ወጪ በማኅበረ ቅዱሳን ተሸፍኗዋል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ወራት ባከናወናቸው የሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፋፊያ ተግባራት 8547 አዳዲስ አማንያን ተምረው አምነው በመጠመቅ የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
ይህንን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመፈጸም የሚመለከተው ሁሉ በመሳተፍ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።