በዓለ ጥምቀት
እንኳን አደረሳችሁ!
ጥምቀት ሥርዓቱ ከብሉይ ኪዳን ይጀምራል፡፡ አንድ አይሁድነትን ያልተቀበለ አዲስ ሰው ወደ ይሁዲነት ሲመጣ ከማኅበረ አይሁድ ከመቀላቀሉ አስቀድሞ ግዝረትን እና በውኃ መታጠብን (መጠመቅ) እንዲፈጽም ይደረጋል፡፡ ይህም ለመንጻት ሥርዓት በዘሌዋውያን ካህናት አማካኝነት ይፈፀም ነበር፡፡ ውኃ መንጽኢ ነውና ማንም ሰው በተለያየ ምክንያት ቢረክስ የሚነጻበት (የኅፅበት) ሥርዓት ለእያንዳንዱ ምክንያት ነበረው፡፡ (ዘሌ. ፲፬፥፲፭-፳፪) ይህንንም ተዘርዝሮ እናገኘዋለን፡፡ ይህም በእውነት በውኃ ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ እንዳደረበት ያስረዳል፡፡ (ዘፍ.፫፥፪) ተያይዞ እስከ ዘካርያስ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ ደርሷል፡፡
በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የተወለደው ጻድቅ፣ ቅዱስ ሐዋርያ ሰማዕት፣ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የዮሐንስ በረሃ በሚባለው እና ከሕፃናቱ ጀምሮ ባደገበትምድረ በዳ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ በብሕትውና ተወስኖ ሲኖር ቆይቶ ለክርስቶስ መንፈቅ ሲቀረው በ፴ ዘመኑ የዮርዳኖስ አውራጃ በምትሆን በይሁዳ ‹‹ነስሑ እስመቀርበት መንግሥተ ሰማያት፤ መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፣ ልጅነት በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለችና በወንጌል አምናችሁ ንስሐ እያለ ሰበከ፤ በነቢይ ‹‹የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ›› እንደ ተባለለት፡፡ (ኢሳ.፵፥፫፣ማቴ.፫፥፫)
ቃሉን የተቀበሉም ስለ ኃጢአት ስርየት ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ይጠመቁ ነበር፡፡ ይህም አማኞችን ለክርስቶስ ጥምቀት የሚያዘጋጅና በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ለመሆን የሚያበቃ ነበር፡፡ ‹‹እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸክም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል›› (ማቴ.፫፥፲፩) ክርስቶስም ናዝራዊ ከተባለበት (ማቴ. ፥፳፫) ከናዝሬት ወደ ዮርዳኖስ ጥር ፲፩ ቀን ወረደ፤ ቅዱስ ዮሐንስም ስለ እርሱ መሰከረ ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያአትት ወያሴስል ኃጢአተ ዓለም፤ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፡፡›› (ዮሐ.፩፥፳፱)
ዮሐንስም ክርስቶስ በእርሱ እንዲጠመቅ መምጣቱን ባየ ጊዜ ወትሮ ባሪያ ወደ ጌታው ይሄዳል እንጂ እንዴት ይህ ይሆናል? አለው፤ ትሕትናን ከእናቱ ተምሯልና፤ ‹‹የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?›› እንዳለች ቅድስት ኤልሳቤጥ፡፡ (ሉቃ.፩፥፵፫) ደግሞስ ሌላውን ሁሉ በስምህ አጠምቃለሁ፤ አንተን በማን ስም አጠምቃለሁ? ቢለው ‹‹ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሃለነ››፤ ‹‹አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሢመቱ ለመልከ ጼዴቅ›› ብለህ አጥምቀኝ ብሎታል፤ ብርሃንን የምትገልጥ የቡሩክ አብ የባሕርይው ልጅ ይቅር በለን፤ እንደ መልከ ጼዴቅ የዓለም ሁሉ ካህን አንተ ነህ›› እያልክ አጥምቀኝ ብሎታል፤ ከዚያም ዮሐንስ ሊያጠምቀው ወደ ዮርዳኖስ ገብቷል፡፡
ዮርዳኖስ የጥምቀቱ ቦታ እንዲሆን ጌታ የፈቀደው አስቀድሞ ትንቢት አናግሮ ምሳሌ መስሎ ‹‹ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮርዳኖስኒ ገብአ ድኅሬሁ ርእዩከ ማያት እግዚኦ ርእዩከ ማያት ወፈርሁ፤ አቤቱ ውኆች አዩህ፤ ውኆችም አይተውህ ፈሩህ፤ ጥልቆችም ተነዋወጡ፤ ውኆችም ጮሁ፡፡›› (መዝ. ፸፮፥፲፮) ‹‹ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤ ዮርዳኖስም ወደ ኋላ ተመለሰ፤›› (መዝ.፻፲፫፥፫) ዮርዳኖስ መነሻው ከላይ ነቁ፤ አንድ ነው፤ ዝቅ ብሎ በደሴት ይከፈላል፤ ከታች ወርዶ ይገናኛል፡፡ የሰውም ልጅ አባቱ አንዱ አዳም ሲሆን እስራኤልና አሕዛብ በግዝረት በቁልፈት ተለያይተዋልና፡፡ ከታች ወርዶ እንደገና በወደብ እንዲገናኝ ሕዝብ እና አሕዛብ በክርስቶስ ጥምቀት አንድ ሆነዋል፤ ከዚህም የተነሣ ጌታ የሁለቱ ወንዝ መጋጠሚያ ላይ በመጠመቅ አንድነታችንን መልሶልናል፡፡ ይህንን ውለታ በማሰብ (ይህን የነጻነት በዓል) እናከብራለን፡፡
ከዚህም በላይ የሥላሴ ምሥጢር እኛ በምንረዳው መልኩ ያየንበትን በዓል የዕዳ ደብዳቤያችን የተፋቀበትን ቀን፣ ነጻነታችንን ያወጅንበትን፣ የእግዚአብሔር ልጆች የሆንበትን ዕለት ከበዓልም የሚበልጥ ዐቢይ በዓል አድርገን አናከብረዋለን፡፡ ይህንንም ቀን ቀድሶ የሰጠን ቅዱስ አምላክ ምስጋና ይድረሰው፤ አሜን፡፡
ከበዓሉ በረከት ረድኤት ያሳትፈን!