የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የሱማሊያ አቻቸውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን ሱማሊያ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው የሱማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይል ውስጥ የኡጋንዳ ወታደሮች የኢትዮጵያን ወታደሮች ተክተው እንዲገቡ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡
በተለይም የኢትዮጵያ ወታደሮች በሚገኙበት በጌዶ፣ ቤይና ባኩል ግዛቶች የኡጋንዳ ወታደሮች እንዲሰማሩ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም የሱማሊያ ደቡብ ምእራብ ግዛት በሚገኘው ባይደዋ ከተማ የኡጋንዳ ጦር ሀይል የጦር ሰፈር እንዲያቋቁም ሀሳብ አቅርበው የነበረ ሲሆን ሙሴቪኒ ግን ውድቅ ማድረጋቸውን ዘገባው ገልጿል፡፡
ፕሬዝደንት ሙሴቪኒ በባይደዋ ከተማና በሞቃዲሾ መካከል ርቀት እንዳለ ጠቅሰው በመሀል ያለው መንገድ ደግሞ በአሸባሪ ሀይል መያዙን አስረድተዋል፡፡ የኡጋንዳ ወታደሮች ከተሰማሩ በኋላ ሀይል ለማጠናከር ተጨማሪ ወታደሮችን በአውሮፕላን ማጓጓዝ አስቸጋሪ ስለሚሆን እዚያው ያሉት የኢትዮጵያና የኬንያ ወታደሮች ባሉበት እንዲቀጥሉ ማለታቸውን ዘገባው አስረድቷል፡፡
@zena_ethiopia24