ግጭቶች በአፍሪካ በአስከፊ ሁኔታ ቀጥለዋል አሉ ሙሳ ፋኪ ማሃማት
“ግጭቶች በአፍሪካ ትልቅ ተግዳሮት ሆነው ቀጥለዋል” ሲሉ ተሰናባቹ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኅብረቱ 46ኛ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።
አህጉሪቱ ትርጉም ያለው እድገት ብታስመዘግብም፣ ግጭቶች በአስከፊ ሁኔታ ቀጥለዋል ሲሉ ሙሳ ፋኪ ማሃማት የአፍሪካ የውጪ ጉዳይ ምኒስትሮች በተገኙበት ጉባኤ ላይ አመልክተዋል።
ሱዳንና ምሥራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስከፊ ግጭት ከሚስተዋልባቸው ሀገራት ውስጥ እንደሆኑ በምሳሌነት ጠቅሰዋል።
የአፍሪካ ኅብረት የገንዘብ ችግር እንደገጠመው ያወሱት ፋኪ ማሃማት፣ ይህም በኅብረቱን ውጤታማነትና በውሳኔ አሰጣጥ ወቅትም ገለልተኛ መሆኑ ላይ ጫና ፈጥሯል ብለዋል።
ዓርብ ከሚከፈተው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ቀደም ብለው የተናገሩት ተሰናባቹ ኮሚሽነር፣ በዓለም በመታየት ላይ ያሉ ተግዳሮቶች በኅብረቱ ላይም ጫና እንደሚፈጥሩም ጠቁመዋል።
ኅብረቱ የኮቪድ 19፣ የኢቦላ እንዲሁም የኤምፖክስ ወርርሽኖችን የተከላከለበትን መንገድ ማሃማት አድንቀዋል።
“የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ውጤታማ ተቋም መሆኑን እያሳየ ነው” ሲሉም አክለዋል።
የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም
@zena_ethiopia24