የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ለሚያስገነባው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዲዛይን ከሚሰራለት ኩባንያ ጋር ተፈራረመ
**
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ለሚያስገነባው ግዙፍ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዲዛይን ከሚሰራለት ዳር ከተባለ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።
በቢሾፍቱ የሚገነባው ይህ ግዙፍ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያን አቪዬሽን ኢንደስትሪ ለማሳደግ የላቀ ሚና እንደሚኖረው ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው አውሮፕላን ማረፊያው በአፍሪካ ግዙፉ ይሆናል ያሉ ሲሆን፤60 ሚሊዮን መንገደኞችን በዓመት ለማጓጓዝ አቅም እንደሚኖረውም ተነግሯል።
በሁለት ምዕራፍ የሚገነባው ፕሮጀክቱ፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ከ 6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚደረግበትም ተጠቅሷል።
አውሮፕላን ማረፊያው በ35 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚያርፍ ይሆናልም ነው የተባለው።
https://t.me/zenacentral