┈┈••◉❖◉●••┈
👨🌾 ተወዳጁ🌺
❣ :¨·....................:¨·.❣
♥️ ክፍል ሁለት
💢ልብ አንጠልጣይና አሳዛኝ ታሪክ
ሄኖክ የሀና ሁኔታ ቢረብሸውም ትላንት ደፍራ ልቡን ሰንጥቃ የገባችውን ሴት ለማየት እንደጓጓ ሰአቱ ደረሰ ይሄኔ ቀድሞ እዛ ቦታ የተገኘው እሱ ነበር ነገር ግን የመጣችው ከሩቅ የተመለከታት ሴት ነበረች... ገና ስትጠጋው ሽቶዋ የተማሪ አይመስልም የሀብታም ልጅ ለመሆኗ ወዟ ይናገራል ይሄኔ ሄኖክ ትላንት ያየውን ፈገግታ በማስታወስ የትላንቷ ልጅስ አላት ሜላት እባላለው የማፈቅርህና ደብዳቤ የላኩልህ እኔ ነኝ አለችው ሄኖክም ተናዶ ጥሏት ሄደ.... ሄኖክ በጠይሟ ልጅ የአይን ፍቅር ተለከፏል ጠይሟ ቆንጆ ኤልሳ ትባላለች የሜላት ጓደኛ ናት ሜላት ቆንጆ ዘናጭና የሀብታም ልጅ ብትሆንም "እርጋታዋና ስብእናዋ..." እያለ ሄኖክ የሚያወድሳት ግን ኤልሳን ነው ... ክፍል ገብቶ ተክዞ ሲቀመጥ ጓደኛው ዶጮ ሄኒዬ ችግር አለ ?" ሲል ጠየቀው ሄኖክም አይኑን ከተከለበት ሳይነቅል የገጠመውን ነገረው ዶጮም በዛ ጎርናና ድምፁ ከልቡ ስቆ "ሄኒዬ ቺኳኮ እዚ ግቢ ካሉ ሴቶቻችን ወደር ያልተገኘላት ናት በዛ ላይ አባቷ 6 መኪና አላቸው እና እኛ በሳምንት ልብስ ስንቀይር እሷ በ3 ቀን መኪና ትቀይራለች በዛ ላይ..." እያለ የማይቋረጥ የሚመስለውን ሀተታ ሲቀጥል... "ዶጮ እኔ ግን ለጓደኛዋ የሌለ አዲስ ስሜት ተሰምቶኛል!" አለው ዶጮም ጥቂት በዝምታ ተውጦ ሄኖክን ካስተዋለው ቡሃላ "አይ አይ ተምታቶብህ ነው ወዳጄ ኤልሳኮ ፀጉሯን ካለማበጠሯና ያቺን ቀይ ሲሊፐር ካለመቀየሯ የተነሳ ቅፅል ስሟ ድንቅ ነሽ ነው ምክንያቱም ሁሌም ተመሳሳይ ናት"...አለና ከት ብሎ ሳቀ ይሄኔ ሄኖክ በገዛ ጓደኛው በንዴት እየጋለ "ስማ ላይዋ ባይሽቀረቀርም ማንም ሊደፍረው ያልቻለውን ልቤን ደርምሳ ገብታለች እየውልህ ልታግዘኝ ባትችል እንኳ ዳግም እንደ ተራ ሰው የወረደ ንግግርህን መስማት አልፈልግም!" ብሎ ቦርሳውን አንስቶ ተነስቶ ወደ ላይብረሪ ሄደ... ዶጮ በሄኖክ ድርጊት ደነገጠ ብዙ ሴቶች ሊቀርቡት ሲመኙ እጅ ያልሰጠው ሄኖክ ዛሬ ተቀየረበት... ላይብረሪ ገብቶ የፊዚክስ መፅሃፉን ገለጠ ግን በሀሳብ ጭልጥ ብሏል ... ይሄኔ "ሄኖክ መልሱስ ላክልኝ እንጂ ብላሃለች..." የሚል ንግግር በሹክሹክታ ከጆሮው ሲፀርስ ተሰማው ከሀሳብ ሰመመኑ ብንን እንደማለት
ብሎ ቀና ሲል ያ ውብ ከለሯ ከውብ አይኖቿ ጋር ተደምሮ ልእልት ያመሰላት ቆንጆ ከጎኑ ተቀምጣለች ...ከንፈሮቿ ተገጥመው ልብ ቅርፅ ሰርተው ሲያያቸው ሰአሊ ባረከኝ ብሎ ተመኘ በድጋሚ ከነተጨባረረው ፀጉሯ ስታምር አለ በውስጡ ልጅቷ በዝምታ ሲመለከታት ግራ በመጋባት በቅንድቧ መልስልኛ አይነት ምልክት አሳየችው ሄኖክም ወደ ውጪ እንዲወጡ ምልክት ሰጣትና
ወጡ... "እእእ እየውልሽ ኤልሳ ይቅርታ አርጊልኝና ሳላነበው ጠፋብኝ ግን በቃልሽ ንገሪኝ ምንድን ነው?" አላት ኮስተር ለማለት እየሞከረ ኤልሳም እርጋታዋ ሳይለያት "እሺ እየውልህ ጓደኛዬ ሜላት በጣም ወዳሃለች እናም ተቀራርባቹ አንድ ላይ እንድትሆኑ ትፈልጋለች እባክህ ተረዳት ..." አለች አጠቃቀሟ
እንቅስቃሴዋ ሳይቀር ይማርካል ተመስጦ እያያት እያለ...."እ በላ መልስልኝ ምን ታስባለህ" አለችው......
✎ ክፍል ሶስት ይቀጥላል
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @zenafetabegna
ዘና ፈታ በኛ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄