🌺ሴና🌺
#ክፍል አራት
#ተከታታይ ልቦለድ
ገና ከመቀመጣችን ሁለት ልጆች እኛ ወደተቀመጥንበት መጡ፡፡ አጠገባችን እንደደረሱ አንደኛው "አንቺን የመሰለች ቆንጆ ካፌ?" ሲል እንደተገረመ ሰው አፉን ያዘ፡፡ "ችግር አለው እንዴ?" ስል ድምፄን ዝቅ አድርጌ ጠየኩ፡፡ ሁሉም ሳቃቸውን ለቀቁት፡፡ ደነገጥኩኝ! ያወራውት ያስቃል እንዴ? እኔንጃ ብቻ ወንዶቹም እየሳቁ ወንበር ጠርገው ተቀመጡ፡፡ "ይሄ ዴቭ ይባላል ይሄደሞ ፍሬ ከአንድ አገር ነው የመጣነው ጉዋደኞቼ ናቸው፡፡" ስትል ቀልጠፍ ብላ ታስተዋውቀኝ ጀመር ከጎኔ የተቀመጠችው የዶርም ጉዋደኛዬ፡፡ አሁን ገባኝ ለምን እንደሳቁ እነሱ ለካ ቀድሞውኑኑ ይተዋወቁ ኖረዋል፡፡
"ምንድነው ውጦ ዝም?" አለኝ ዴቭ የተባለው 2ክንዱን ጠረቤዛው ላይ አስደግፎ በእጁ ጉንጩን ደግፎ በትኩረት እየተመለከተኝ፡፡ "እንዴ መች በላው ምንድነው የዋጥኩት?" ስል ጠየኩት፡፡ አሁን ከቅድሙ የበለጠ ሳቁ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ "የኛን ሰምተሽ ዝም አልሽ አንቺም ራስሽን አስተዋውቂን ለማለት ነው፡፡"ሲል ፍሬ የተባለው ቀስ ብሎ ነገረኝ፡፡ አንተ ምን አገባህ እያሉ ወረዱበት፡፡ስሜን እና የሀዋሳ ልጅ መሆኔን ነገርኳቸው፡፡ "ሙሉ ዶርሙ ሴና ሆነ በቃ" ሲል ዴቭ ሳቀ፡፡ ለካ ዶርም ውስጥ ሁላችንም ሴና ነው ስማችን፡፡ አሁን ነው ያወኩት፡፡ ግን ዝም አልኩ፡፡ ምግብን የሁላችንንም አንድ ትሪ ላይ ገለበጡት፡፡ ዴቭ እና ፍሬ ብሉ ሲባሉ "እኛ ሰቅለን ነው የመጣነው፡፡" አለ ዴቭ፡፡ ሚጠቀመው ቃል ግራ እየገባኝ ነው፡፡ ግራ መጋባቴን አይቶ "በልተን ነው የመጣነው ለማለት ነው፡፡" ሲል ፍሬ በኔ አማርኛ ተረጎመልኝ፡፡ መብላት ጀመርን፡፡ ምግቡ ገና ስቀምሰው ጠአሙ ብዙም አይመችም፡፡ ግን እነሱን ላለማስቀየም ስል ዝም ብዬ መመገብ ጀመርኩ፡፡ እኛ እየበላን ዴቭ ይለፈልፋል፡፡ በመሀል ይስቃሉ፡፡ ፍሬ ምንም አይናገርም፡፡ አልፎ አልፎ ፈገግ ይላል፡፡ አይኔን ቀና ባደረኩ ቁጥር አይን ለ አይን እንጋጫለን ከፍሬ ጋር፡፡ ዴቭ ወሬውን እንደቀጠለበት ነው ፡፡ ምግቡን ወደመጨረስ ስንቃረብ "በቃ ይሄ ተመላሽ ነው በቃቹ!" ሲል ትሪውን አነሳው፡፡ አንተ አረ እንብላበት ቢሉትም አልሰማም አለ ትሪውን ይዞት ሄደ፡፡ እኔ ምንም አላልኩም፡፡ "አይ ሊጋብዘን ነው ማለት ነው" ስትል አንደኛዋ ተናገረች እየተሳሳቅን ከመቀመጫችን ተነስተን ወደ ውጪ ወጣን፡፡ ስንወጣ የካፌው መግቢያ በር ዝግ ነበር፡፡ ከወጣን በሗላ ዴቭ "የወሰድኩትን ምሳቹን ልካሳቹ" ሲል ሁሉም እሺ ብለው ተስማሙ፡፡ አኔን ሲጠይቁኝ ብቻዬንም ብሆን መሄጃ ስለሌለኝ ተስማምቻቸው ግቢ ውስጥ ወደሚገኝ ተከፍሎበት ወደሚመገቡበት ካፌ ሄድን፡፡ እንደደረስን ዴቭ "እነሱን ተያቸው ቢሆንላቸው እኔን ይበላሉ ስለዚ አልጠይቃቸውም አንቺ ምንትበያለሽ?" ሲል ጠየቀኝ፡፡ "አረ ዴቭ ይደብራል..."እያሉ ያጉረመርሙ ጀመር "እኔ ምንም አልፈልግም ጠግቤያለው፡፡" አልኩት ደግሞ ቢጠይቀኝም አለመፈለጌን ገለፅኩለት፡፡ በቃ ግብዣው ለ እራት ይሁን በሚለው ተስማምተን ከመጣን አይቀር ለምን ፑል አንጫወትም አሉ፡፡ ሁሉም ተስማሙ፡፡ እኔ ተጫውቼ እንደማላውቅ ነገርኳቸው፡፡ እንደለመዱት መሳቅ ጀመሩ፡፡ ፍሬ "አሁን ይሄ ምኑ ያስቃል ምድረ ዱርዬ ደና ነገር አውቃቹ ሞታችሗል! ነይ አንቺ እነሱ ይጫወቱ" ተያቸው ብሎ እጄን ይዞኝ ከ ካፌው ወጣ፡፡
ከካፌው እንደወጣን እጄን ለቆኝ ቆመ፡፡ እኔንጃ ከ አባቴ እና ወንድሞቼ ውጪ ወንድ እንደዚ እጄን የያዘበት ቀን ትዝ አይለኝም፡፡ ፍሬ እንደዛ ለምን እንደተናደደባቸው እባይገባኝም በኔ ላይ መሳቃቸው እንዳበሳጨው ያስታውቅበታል፡፡ ካፌው በር ላይ እንደቆምን እነ ዴቭ አጥርቼ ባልሰማቸውም ከውስጥ የሆነ ነገር ብለው ይስቃሉ፡፡
"ቡና ትጠጫለሽ?" አለኝ ትህትና በተሞላበት ድምፅ እኔ ብና እንደማልጠጣ ነግሬው እንግዲያውስ አሪፍ ቦታ ላሳይሽ ብሎ ይዞኝ መሄድ ጀመረ፡፡
ዛሬ ቀኑ ተለወጠብኝ፡፡ እንደዚ አይነት ቀን ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ ከጥዋት ግቢ ከገባውበት ሰአት አንስቶ ብዙ አዲስ ነገሮችን አደረኩ፡፡ በአንድ ቀን እንደዚ ሰው መቅረቤን እያሰብኩ ገረመኝ፡፡ በዙ ሀሳብ በውስጤ እየተመላለሰ ከፍሬ ጋር መሄዴን ቀጠልኩ . . .
#ክፍል_አምስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉👍
⭕️ታሪኩ ከተመቻችሁ 👍👈 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!
.............ይቀጥላል............✍
🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚