🌺ሴና🌺
#ክፍል 8⃣
#ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ✅
. . . እያወራን ወክ ማድረግ ጀመርን፡፡ ትንሽ እንደሄድን እኔና ፍሬ ሁዋላ ቀረት ብለን ለሁለት እያወራን ወክ ማድረግ ጀመርን፡፡
እኔና ፍሬ የግል ወሬያችንን ይዘናል፡፡ ከትናንቱ የተሻለ እየተቀራረብን ይመስለኛል ብዙ ግላዊ ነገሮቻችንን እያወራን ነው ወክ ምናደርገው፡፡ እነ ዴቭ ከፊት ለፊታችን እየተሳሳቁ ወክ ያደርጋሉ፡፡ ትንሽ ከሄድን ብሀላ ፍሬ "ቁጭ እንበል" አለኝ፡፡ ድንገት ቢሆንብኝም እሺ አልኩት፡፡
እነ ዴቭን ትተን በሲሚንቶ የተሰራ መቀመጫ ወዳለበት ሄደን ቁጭ አልን፡፡ መጨዋወት ጀመርን፡፡ የምሽቱ ንፋስ ይበርደኝ ጀመር፡፡ እንሂድ እንዳልል ግን ፍሬ እንዳይደብረው ብዙ ቁጭ አልኩ፡፡ ፍሬ ሲያወራ ደስ ይላል፡፡ አነጋገሩ ረጋ ያለ ነው፡፡ የሚጠቀማቸው ቃላት ብዙ እንደሚያነብ ያሳያሉ፡፡ እኔም እንዲ ቁጭ ብዬ ከወንድ ጋር ብዙ ሳወራ የየመጀመሪያዬ ሳይሆን አይቀርም፡፡
በጨዋታችን መሀል ፍሬ የለበሰውን ሸሚዝ አውልቆ ሰጠኝ፡፡ "አረ በትሸርት ብቻ ይበርድካል" ስለው አልሰማ አለኝ፡፡ ሸሚዙን ተቀብዬ እላዬ ላይ ጣል አደረኩት፡፡ "እህ ልበሺው እንጂ ሸሚዝ እኮ ነው እስከርቭ አይደለም ፡፡" አለኝ፡፡ሳላቅማማ ለበስኩት፡፡ ፍሬ በእጀ ጉርድ ትሸርት ሆኖ ሳየው የሰውነቱ ቅርፅ በተወሰነ መልኩ ይታያል ፡፡ "ፊልም ላይ የማያቸው የ አሜሪካ አክተሮችን ትመስላለክ፡፡" አልኩት፡፡ በጣም ሳቀ፡፡ ሲስቅ ዲምፕል አለው፡፡ ሳቁ ደስ ሚል ነገር ነው፡፡ ስቀን ዝም ስንል ዴቭ ደወለለት፡፡
ላውድ ላይ አድርጎ ያሰማኛል፡፡"አራዶች በጓሮ ላሽ አላቹ ማለት ነው፡፡ አንተ በ ሁለት በረራ እርግቧን ልትነድፋት ነው?" ምናምን የማይገባኝን አማርኛ አወራ ፍሬ መልስ ይሰጠዋል፡፡ እማላውቀው ቃል ይጠቀማሉ፡፡ በመሀል ይስቃሉ፡፡ ዝም በዬ ሰማው አውርተው ሲጨርሱ ሰአት አይቼ በጣም መሽቷል እንሂድ በቃ አልኩት፡፡ ፍሬም በትህትና እሺ ብሎ ተነስተን ሄድን፡፡
እስከ ዶርም መገንጠያ ድረስ ሸኝቶኝ ሊሄድ ሲል ሸሚዙን ማውለቅ ጀመርኩ፡፡ "አረ ነገ ይደርሳል ባይሆን ስልክሽን ስጪን እንዳትረሺው ደውዬ ላስታውስሽ፡፡" አለኝ፡፡ አልተቃወምኩም ስልክ ተለዋውጠን ቻው ተባብለን ወደ ዶርሜ ሄድኩ፡፡
ዶርም ስገባ ሶስቱ ጉዋደኞቼ "እ እ ጥሩ ነው "ምናምን እያሉ እየሳቁ ይቀልዱብኝ ጀመሩ፡፡ ለምን እንደዛ እንዳሉኝ በቅጡ ባይገባኝም አብሬያቸው መሳቅ ጀመርኩ፡፡
ወደበር ካለው አልጋ ላይ አንድ ልጅ መነፅር አድርጋ ላፕቶፕ እየነካካች ነው አልጋዋ ላይ ተኝታ፡፡ ደሞ ሌላኛዋ ልጅ ነች ማለት ነው ስል ለራሴ አውርቼ ዝም አልኩ፡፡ እየተሳሳቅን ልብሴን ከሎከሬ አውጥቼ ቀይሬ ልተጣጠብ ወጣው፡፡
ስመለስ ስልኬ ሶስት ግዜ ጠርቶአል፡፡ ከፍቼ ሳየው አባቴ ነው፡፡ ደነገጥኩ ልሼ ደወልኩ፡፡ ዘግቶት መልሶ ደወለ፡፡ ገና ከማንሳቴ ንግግሩን በቁጣ ጀመረ፡፡ ስልክ ባለማንሳቴ በጣም ተቆጣ ብነግረውም አይሰማኝም፡፡ ጭቅጭቅ ሚመስል ንግግር ካደረግን ብሀላ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋው፡፡
ዶርም ውስጥ መሆኔን እንኳን ረስቼው ነበር፡፡ ጉዋደኞቼ ዝም ብለው ያዩኝ ነበር፡፡ ዝም ብዬ አልጋዬ ላይ ወጣው፡፡ "ምነው በሰላም ነው?" እያሉ ጠየቁኝ፡፡ ሰላም ነው ብዬ አልጋዬ ላይ ወጥቼ ፊቴን ወደግድግዳ አዙሬ ተኛው፡፡ ቤተሰቦቼን እያሰብኩ አባቴ በስልክ የተናገረኝ በጆሮዬ እያቃጨለ እንባዬ መጣ፡፡ ይሄንን ሁሉ አመት ስኖር ምንም ተሰምቶኝ አያውቅም ነበር፡፡በጣም ተናደድኩ ውስጤ ተረበሸ፡፡ ጉዋደኞቼ ምን ሆናነው እያሉ ሲንሾካሾኩ ሰማለው፡፡
በመሀል ስልኬ ሚሴጅ ገባ፡፡ስከፍተው "አንቺ ሸሚዜ በሰላም ገባ?" ይላል፡፡ ፍሬ ነው፡፡ ሳላስበው ፈገግ አልኩኝ፡፡ ምን ብዬ እንደምፅፍለት ግን ማሰብ ጀመርኩ፡፡ text ስላላክ ለመጀመሪያ ግዜዬ ሊሆን ነው፡፡ . . .
#ክፍል_ዘጠኝን_ለማንበብ_የቸኮለ👉👍
ታሪኩ ከተመቻችሁ 👍👈 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!
.............ይቀጥላል............✍
🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚