🌺ሴና🌺
#ክፍል 1⃣0⃣
#ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ✅
እኔ ሻወር ወስጄ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩኝ፡፡ "አንቺ ሴና ተነሽ እራት አትበይም እንዴ?" ሚጣ ነበረች የቀሰቀሰችኝ ፡፡ ሰአት ሳይ ከምሽቱ አንድ ሰአት፡፡ ሻወር ወስጄ ጋደም ስል በዛው እንቅልፍ ወስዶኝ ነበር የመሸው፡፡ ልብሴን ቀያይሬ ተያይዘን ወጣን፡፡
እራት ምንበላበት ካፌ ዴቭ እና ፍሬ ከሌሎች ሶስት ወንዶች ጋር ነበሩ፡፡ሰላምታ ተለዋውጠን ሱራፌል ፣ሙባሪክ እና ዮናታን ይባላሉ፡፡ ከተዋወቅናቸው ቡሀላ እራት አዘን መብላት ጀመርን፡፡የተለመደው ጨዋታም ቀጠለ፡፡ እኔ ግን ብዙም ምቾት አልተሰማኝም፡፡እንኳን እንደዚ ብዙ ሆነን ቀርቶ ከነ ፍሬጋም እንደዛ መጫወት መቻሌ ለኔ ራሱ ገርሞኛል፡፡ ምንም የማልናገር ዝምተኛ ልጅ በሁለት ቀን እንደዛ መሆኔ እኔን ራሱ የገረመኝ፡፡
እየተሳሳቁ እያወሩ እራቱን አድምቀውታል፡፡ እኔ ግን ምንም አላወራም፡፡ አልፎ አልፎ ፈገግ ከማለቴ በስተቀር ዝም ብዬ እራቴ ላይ ነው ያለሁት፡፡ እራት እንደጨረስን ሚጣ "ቀን ያልከንን ንገረና የሴናን የሰፈር ስም"ስትል የዶርም ስም ያልወጣላትን ሴና እያየች መጠየቅ ጀመረች፡፡ ከዴቭ ጋር የመጡት ወንዶች ጨምሮ ሚጣ እና እኑካ "ይነገር! ይነገር! እያሉ ማጨብጨብ ጀመሩ፡፡እኔ ዝም ብዬ አያለው ፍሬ ስልኩን እየነካካ ነው ከጨዋታው የለበትም፡፡ ዴቭ "አንቺስ ምን ትያለሽ ይነገር ወይስ ይቅር?" ሲል እየሳቀ ጠየቀኝ፡፡ ጭብጨባውን አቁመው ይመለከቱኝ ጀመር "ይነገረን" አልኩኝ ፈገግ እንደማለት እያልኩ ጠረቤዛ ጠረቤዛውን እየተመለከትኩ፡፡
የሁሉም አይን እኔ ላይ ስለነበር የመጨናነቅ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ቀና ብዬ ወደ ፍሬ ሳይ አይን ለ አይን ተጋጨን፡፡ በአይኑ እንሂድ የሚል ምልክት ሰጠኝ፡፡ እኔም በአንገቴ እሺታዬን ገለፅኩለት፡፡ ወዲያው ብድግ አለ፡፡ "ተጫወቱ እንመለሳለን ነይ ሴና፡፡"ብሎ እጁን ዘረጋልኝ፡፡ ደንገጥ ብዬ ተነሳውኝ፡፡ "ወዴት? ወዴት? መሽቷል አይቻልም፡፡"ሲል ዴቭ እንደመቆጣት አለ፡፡ ሁሉም ማጉረምረም ጀመሩ፡፡ "አይ እንግዲ እንመጣለን አልኩ አይደል!" አለ ፍሬ ኮስተር እንደማለት፡፡ ሁሉም ዝም አሉ፡፡ እኔና ፍሬ ተያይዘን ወጣን፡፡
ወክ እያደረግን ማውራት ጀመርን፡፡ ከፍሬ ጋር በጣም እየተቀራረብን ነው፡፡ ብዙ ከከቆየን ብሀላ ዶርም ድረስ ሸኘኝ፡፡ ቻው ብዬው ልሄድ ስል "በቃ ቻው ብቻ?" አለኝ እጁን ኪሱ ውስጥ ከቶ እንደቆመ፡፡ "አና ምን?" አልኩት ፈገግ ብዬ እንደመገረም እያልኩ፡፡ "እሺ በቃ ቻው ግቢ" ብሎ ተሰናበተኝ፡፡
ዶርም ስገባ እነ ሚጣ ቀድመውኝ ገብተዋል ፡፡ ገና በሩን ከፍቼ ከመግባቴ እንደትናንቱ እየተንሾካሾኩ ይስቁብኝ ጀመር፡፡ "ምነው በግዜ ገባሽ ታዲያ?" እያሉ ያሾፉብኝ ጀመር፡፡ ከነሱጋ እየተሳሳኩኝ ልብሴን መቀየር ስጀምር ስልኬ text ገባ፡፡ ፍሬ ነው ሳይታወቀኝ ፈገግ አልኩ፡፡ "ሸሚዜን አረሳሳሽኝ አይደል?" ይላል የላከልኝ text፡፡ "አረ አውቄ አይደለም፡፡" text መለስኩለት እዛው ልብሴን ምቀይርበት ቆሜ፡፡ ዶርም ውስጥ ያሉትን ለደቂቃም ቢሆን ረሳዋቸው፡፡
ልብሴን ቀይሬ ተጣጥቤ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ፍሬን በ text ማውራት ጀመርኩ፡፡ ዶርም ውስጥ ያወራሉ ይጨዋወታሉ፡፡ ትናንት የመጣችው ልጅ አልጋዋ ላይ ተኝታ ላፕቶፕዋን እየተጠቀመች ከነ ሚጣ ጋር ታወራለች፡፡
ይስቃሉ ይጫወታሉ ፡፡ እኔ በሙሉ ልቤ እየተከታተልኳቸው አይደለም፡፡በመሀል በመሀል ብቻ መልስ ሰጣቸዋለው፡፡ ሙሉ ትኩረቴ ከፍሬ ጋር ሆኖአል፡፡ ደስ የሚል ጨዋታ ይዣለው . .
#ክፍል_አስራአንድን_ለማንበብ_የቸኮለ👍
ታሪኩ ከተመቻችሁ 👍👈 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!
.............ይቀጥላል............✍
🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚