🌺ሴና🌺
#ክፍል 1⃣2⃣
#ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ✅
. . . ከዚህ በፊት ከማንም ወንድ ጋር ተደዋውዬም ተቀጣጥሬም አላውቅም፡፡ ብቻ ግን ደስ የሚል ስሜት እየተሰማኝ ወደ ፍሬ መሄዴን ቀጠልኩ፡፡
ፍሬ ከቀጠረኝ ቦታ ስደርስ ቁጭ ብሎ እየጠበቀኝ ነበር፡፡ሰላምታ ከተለዋወጥን ብሀላ ማታ ዶርም ውስጥ ስለተፈጠረው ነገር እና ለምን text እንዳልመለስኩ እያወራን እየተሳሳቅን ትንሽ ከቆየን ብሀላ "ለምን ሲኒማ አልወስድሽም?" አለኝ፡፡ ያልጠበኩት ግብዥ ነው፡፡ ትንሽ አስደንግጦኛል፡፡ እኔ ሲኒማ ሲባል ከመስማት ውጪ ምን አይነት እንደሆነ አላውቅም ምናልባት አንዳንድ ግዜ በ
በቲቪ ከማየው በስተቀር ማለት ነው ፡፡
መሄድ በጣም ፈልጌ ነበር ነገር ግን ከ ግቢ ውጪ ስለሆነ ያለኝ ለመሄድ አልተስማማውም፡፡ ከግቢ ወጥቼ ስሄድ አንድ ሚያውቀኝ ሰው ወይም የቤት ሰው ቢያየኝስ ብዬ ስለፈራው ለመሄድ ድፍረት አጣሁ፡፡
በዚህም የተነሳ "ለግብዣው በጣም አመሰግናለው ነገር ግን ከግቢ ምወጣው ወደቤት ስሄድ ብቻ ነው፡፡" ስል መለስኩለት፡፡ ምክንያቴን ቢጠይቀኝም እንዲህ ነው ለማለት አልቻልኩም፡፡
እንቢ በማለቴ ፍሬ ቅር ብሎታል ግን ሊጫነኝ አልፈለገም፡፡ ሁሌም ወደምንቀመጥበት ቦታ ሆነን እየተጨዋወትን ዴቭ ለፍሬ ደውሎ ያለንበት መጣ፡፡ ዴቭ በጣም አስቂጭ ነው በጣም ያወራል የፍሬ ተቃራኒ፡፡ ለደቂቃ እንኳ ዝም አይልም በሁሉም ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ይሰጣል አወቀውም አላወቀውም ፡፡ የኔና የፍሬ ስራ ዴቭን እየሰማን መሳቅ ሆነ፡፡ እዛው ተቀምጠን ከዶርም ተደወለልኝ፡፡ እራት እንድንበላ ነበር ያለሁበትን ነግሬያቸው መጡ፡፡ አንድ ቦታ ተሰብስበን እራታችንን ካፌ በላን፡፡ እኔ የትምህርትቤቱ ካፌ ምንም እየተመቸኝ አይደለም ነገር ግን ለእነሱ ስል ሳልወድ እበላለው፡፡
ከእራት ስንወጣ "ወክ እናድርግ ወይስ ሻይ እንጠጣ" የሚል ጥያቄ ተነሳ፡፡ እኔ ወክ ብናደርግ ስል በልቤ ተመኘው መልስ ግን አልሰጠውም፡፡ ከዴቭ ውጪ ሁሉም "ወክ እናድርግ" አሉ ፡፡ ዴቭ "አረ ደክሞኛል ዛሬ ቲቪ እንይ እኔ ጋብዛቹሀለው፡፡ ሚጢጢ ምን ትያለሽ?" ሲል አጠገብ የቆመችዋን ሴና ጠየቃት፡፡ ሳቄን ለቀኩት፡፡ "ሚጢጢ" አልኩኝ ሳቄን ሳላቋርጥ፡፡ "ዛሬ ነው እንዴ የሰማሽው?" ሲል ዴቭ አብሮኝ መሳቅ ጀመረ፡፡ መጀመሪያ ሁሉም ዝም ብለው ነበር፡፡ነገሩ ሲገባቸው እንደአዲስ መሳቅ ጀመሩ፡፡ በቀደም ማታ እራት ከበላን ብሀላ ዴቭ የሰፈር ስሟን ልንገራቹ ሲል እኔና ፍሬ ወጥተን ስለነበር አልሰማውም ነበር፡፡
ሳቄን ቶሎ ማቆም አልቻልኩም፡፡ ይበልጥ ያሳቀኝ የሰውነቱዋን ውፍረት አይቼ ሚጢጢ ሚለውን ስም ከሰውነቱዋ ጋር ሳነፃፅረው በጣም ተቃራኒ ሆነበኝ፡፡ ሳቄን እስክጨርስ እየጠበቁኝ ነበር፡፡ እነሱ ስቀው ወቶላቸዋል መሰለኝ፡፡
"እና ሻይ ይሻላል አይደል?" ሲል ዴቭ መልሶ ጠየቀ፡፡ ፍሬ ስልኩን አውጥቶ ከተመለከተ ቡሀላ "ወይኔ መሄድ አለብኝ በጣም ይቅርታ፡፡" እያለ ሁሉንም እያቀፈ መሰናበት ሲጀምር "ወዴት ነው?" ስል ጠየኩት "የሆነ ቀጠሮ አለብኝ"ሲል አቅፎ ከተሰናበተኝ ቡሀላ ዴቭን እጁን ይዞት ከኛ ጠጋ ካደረገው ቡሀላ በሹክሹክታ የሆነ ነገር ተባብለው ዴቭ ለፍሬ ከኪሱ የሆነ የተጣጠፈ ወረቀት ከሰጠው ቡሀላ ፍሬ አየር ላይ እጁን እያውለበለበ "በሉ ሰዎች የነገ ሰው ይበለን ደና ደሩ፡፡" ብሎን በቆምንበት ትቶን ሄደ፡፡ ፍሬ በመሄዱ ቅር አለኝ፡፡ ወክ ማድረግ ሚለውን ሀሳብ ተውኩት፡፡ የዴቭን ሀሳብ ደገፍኩ ሻይ እንጠጣ አልኩኝ፡፡ ሳላስበው ነው የተናገርኩት ዴቭ ይሄንን ከማለቴ "ጎሽ ነይ አንቺ ትበቂኛለሽ ሌሎሉን ተያቸው፡፡" ብሎ ትከሻዬን አቅፎኝ ይዞኝ መሄድ ጀመረ፡፡ በዚህ ሰአት የቀሩትም እሺ በቃ ደስ ይበላቹ ሲሉ ይከተሉን ጀመር፡፡
ዴቭ አቅፎኝ እየሄድኩ "ፍሬ ግን የምን ቀጠሮ ነው በዚ ሰአት? ደሞ ከማን ጋር ነው? የት ነው የተቀጣጠረው?" የሚሉ ጥያቄዎች በውስጤ ይመላለሳሉ፡፡ ዴቭ አቅፎኝ እየሄደ ያወራል ከሁዋላችን ይስቃሉ እኔ ግን ሀሳቤ ሌላ ቦታ ነው . . .
#ክፍል_አስራሶስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉👍
ታሪኩ ከተመቻችሁ 👍👈 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!
.............ይቀጥላል............✍
🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን