🌺ሴና🌺
#ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ✅
#ክፍል 1⃣4⃣
. . . . በጣም ደነገጥን፡፡ እኔ ልቤ ልትወጣ ደረሰች፡፡ ሊጣሉ ነው፤ማንም በሌለበት በጣም ፈራን ፡፡ ዴቭ ዝም ብሎ ቆሞአል እኛ እንርበተበታለን፡፡ እግሬ ተንቀጠቀጠ "አረ ዴቭ ምንድነው?"! ሚጣ እየተርበተበተች ጠየቀችው፡፡ "አረ አትፍሩ ከኔ ጋር ነው ጉዳያቸው፡፡ ዝም ብለው ነው እናንተ ሂዱ እኔ መጣለው፡፡" አለ ዴቭ ቆጣ እንደማለት እየሆነ፡፡ እኔ ሰው ሲጣላ ማየትም መስማተም ፈራለው፡፡ ቤት ውስጥ ራሱ ትንሽ ጭቅጭቅ ካለ ጆሮዬን ይዤ አንድ ጥግ ላይ ነው ምቀመጠው፡፡
ዴቭ ሂዱ እያለን ትተነው በመሄድ እና ባለወሄድ መሀከል ስንወዛገብ ቅድም የተጣላው ልጅ ወደ ዴቭ ጠጋ ብሎ "አሁንም ደግሜ ላስጠንቅቅህ ብትተዋት ይሻልካል! ይህ ለመጨረሻ ግዜ ምነግርክ ነው እንቢ ካልክ አሳይካለው!" ሲል ቁጣና ንቀት በተቀላቀለበት ሁኔታ ዴቭ ላይ አንባርቆበት ጉዋደኞቹን ይዞ ሄደ፡፡
ልጆቹ ከኛ ራቅ እስከሚሉ ድረስ ማናችንም ምንም አልተነቃነቅንም፡፡ ከኛ ከራቁ ቡሀላ ድንጋጤው ባይለቀንም ራሳችንን ለማረጋጋት እየሞከርን ዴቭ ላይ የጥያቄ ናዳ እናወርድበት ጀመር፡፡ "ማነው? ምንድነው? ምን ፈልጎ ነው? ምንድነው አድርግ ሚልህ? ምንድነው ተው ያለክ? በምን ተገናኝታቹ ነው? " ጥያቄ ላይ ጥያቄ እያከታተልን መፈናፈኛ አሳጣነው፡፡ "አረ ይሄ ውሻ ዝም ብሎ ነው ተውት፡፡"አለ ዴቭ ወገብን በእጁ ይዞ እየተንቆራጠጠ በእልህ ስሜት ከንፈሩን ነክሶ፡፡"የዴቭ የሆንከውን ለምን አትናገርም!? " የተመካከርን ይመስል በእኩል ድምፅ ጠየቅነው፡፡ "ምንም አልሆንኩም አልኳቹ እኮ!"እንባ በተናነቀው ድምፅ ዴቭ ተቆጣ፡፡
"እሺ በቃ ተረጋጋ"ብላ ሚጣ እጁን ከወገቡ አስለቅቃው ይዛው መሄድ ጀመረች፡፡ እኛም ተከተልናቸው፡፡ በኛ ዶርም በኩል አልፎ ስለነበር ሚሄደው ዴቭ ወደዶርማችን መግቢያ ድረስ አብሮን መጥቶ በቅጡ እንኳን ደና ደር ሳነንለው ትሎን ሄደ፡፡ እኛም ምንም ሳንነጋገር ወደ ዶርም ገባን፡፡
ፍሬ አለመኖሩ እንደገና ደሞ ዴቭ እንዲ መሆኑ ተደምረው ውስጤ የሆነ ነገር ተሰማኝ ዶርም ገብቼ ማን እንዳለ ምን እንደተደረገ እንኳን ሳላይ ልብሴን ብቻ ቀይሬ አልጋዬ ላይ ወጥቼ ፊቴን ወደግድግዳ አዙሬ በሆዴ ተኛው፡፡
ትንሽ ቆይቶ ስልኬ ጠራ ወንድሜ ነው፡፡ ገና ስልኩን ሳነሳ በቁጣ እና በጭቅጭቅ ጀመረ፡፡ ምንም ያደረኩት ነገር የለም፡፡ ምን እንዳስቆጣው አላውቅም፡፡ ደና ደሪ ብሎ ስልኩን እስኪዘጋው ቸኮልኩ፡፡ እስኪበቃው ካወራ ቡሀላ ደና እደሪ ብሎ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋው፡፡ ስልኬን አጠገቤ አስቀምጬ ተኛው፡፡
ትንሽ ቆይቶ ስልኬ መልእክት ገባ፡፡ ፍሬ ነው የላከው አልኩ ፈጥኜ ከፈትከት ወንድሜ ነው ካርድ ልኮልኝ፡፡ የሆነ የመብሸቅ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ጥቅልል ብዬ ተኛው፡፡
ጠዋት ከ ክፍል መልስ ፍሬን አገኘውት፡፡ ደስ ሚል ቀን አሳለፍን ማታም በ ስልክ እያወራን አመሸን፡፡ ፍሬን በጣም እየቀረብኩ መጣሁ፡፡ ቅዳሜ ደርሶ ጥዋት ላይ ወደቤት ለመሄድ የቆሸሹ ልብሶቼን በሻንጣዬ አስተካክዬ ወጣው፡፡ ገና ወደቤት መሄዴን ሳስበው ደሞ የሆነ ቅር ሚል ነገር ይሰማኛል፡፡ ሁለት ቀን እስር እንደምገባ ነው የሚሰማኝ፡፡ ይሄንን ያህል ቀን ከቤት ርቄ ብቻዬን የቆየውበት ግዜ የለም፡፡ ፍሬ እና ዴቭን በስልክ ነው ቻው ያልኳቸው፡፡
የዶርም ጉዋደኞቼ ታክሲ አሳፍረውኝ ተመለሱ፡፡ 'ቤት እና ዶርም ዶርም ነፃ የሆነ አለም ቤት እስር ቤት ፤ እነ ፍሬ እነ ዴቭ እነ ሚጣ የግቢ ልጆች ቤት ደሞ እናቴ አባቴ ወንድሞቼ በአንድ ሳምንት ያየሁት ቤት ውስጥ ይሄንን ሁሉ ቆይቼ ምንም ያላየዋቸው በብዙ ሀሳብ ውስጥ ሆኜ ወደቤት መሄዴን ቀጠልኩ . . .
#ክፍል_አስራአምስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉👍
ታሪኩ ከተመቻችሁ 👍👈 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!
.............ይቀጥላል............✍
🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን