🌺ሴና🌺
#ክፍል 1⃣5⃣
#ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ✅
. . . .ሁለት አለም ቤት እና ትምህርትቤት ፤ ቤት ውስጥ ያሁሉ ቁጥጥር ሰው ሁሉ ሚስጥር ሆኖ በወስጤ የተሳለበት ውጪ ነፃ አለም ከየት ወዴት ጥያቄ የሌለበት . . .
እቤት ስደርስ እናቴ እና አባቴ ቁጭ ብለው እየጠበቁኝ ነበር፡፡ ሰራተኛችን ብና እያፈላች፡፡ ከሩቅ እንደመጣ እንግዳ ሻንጣዬን ተቀብለውኝ አቅፈው ስመው ካስቀመጡኝ ብሀላ ሻማ በርቶ አባቴ በስሜ ዳቦ ቆረሰ፡፡ "ተመስገን ፈጣሪ ልጄ ለዚህ ስላበቃህልኝ፡፡" ሲል ፀሎቱን አደረሰ፡፡ አባቴ እኔን ለማግኘት ብሎ አለወትሮ ከስራ እንደቀረ ገብቶኛል፡፡ እናቴም መርቃ ምግብ በልተን ቡና ጠጥተን ስለ ግቢው እና ስላጋጠሙኝ ነገሮች ማውራት ጀመርኩ፡፡ እነርሱ ማውቅ ያለባቸውን ማወቅ በሚገባቸው አማርኛ፡፡
ከእናት እና ከአባቴ ጋር ካወራሁኝ ቡሀላ ክፍሌ ገብቼ ተኛው፡፡ ካሁኑ ግቢ ናፈቀኝ፡፡ ስልኬን አስሬ እያወጣው አያለው፡፡ቀኑ ረዘመብኝ ክፍሌ ውስጥ አንዴ መፅሀፍ ሳገላብጥ አንዴ ጋደም ስል ቀኑ አላልቅ አለኝ፡፡ ልዪነቱ አሁን ይበልጥ ታየኝ፡፡ በፊት ለመሄድ ምጓጓለት ስላልነበረኝ ቤት ስውል ምንም የተለየ ስሜት የለኝም፡፡ አሁን ግን እስርቤት ያለው ያህል ነፃነቴን የተገፈፍኩ ያህል ጨነቀኝ፡፡ ተንቆራጠጥኩ፣ ሰኞ ናፈቀኝ፡፡
አመሻሽ ላይ ወንድሞቼ መጡ፡፡ ገና ሰላምታ ከመለዋወጣችን የጥያቄ መአት ወረደብኝ፡፡ "ዶርም ያሉ ልጆች እንዴት ናቸው? ምንድናቸው? ሀይማኖታቸው? ከየት ነው የመጡት? ፀባያቸው እንዴት ነው? ክፍል ውስጥ ምን አይነት ልጆች ናቸው ያሉት? ምንምን ተማርሽ? ረፍት ግዜሽን ከማን ጋር ነው ምታሳልፊው? የት ነው ምትመገቢው? ምንድነው ምትመገቢው? . . ." አረ ለማስታወስ የሚያዳግቱ የጥያቄ እሩምታ ወረደብኝ፡፡
ለሁሉም ጥያቄ ምላሽ መስጠት ጀመርኩኝ፡፡ ማወራው አብዛኛው ውሸት እና እነሱ መስማት ሚፈልጉትን ነው፡፡ መቼስ ስሐማሳለፈው ውሉ ብነግራቸው . . .ሆሆሆ ብቻ ወንድሞቼ ተምረዋል ግን ለምን አስተሳሰባቸው እንደዚ እድደሆነ አልገባኝም፡፡ ነገሮችኝ ከአሉታዊ ጎን ነው ሚረዱት፡፡ ዛሬ አንድ ነገር ገባኝ ለካስ እማዬ እና አባዬ በወንድሞቼ አስተሳሰብ ውሰጥ ሆነው፡፡ ቅድም ሁለቱ ብቻ የነበሩ ሰአት ሁሉንም ነገር በቀላሉ ነው የጨረስነው፡፡
"አንድ እኛ መስራቤት ሚሰራ ሰው የሱ ልጅ እናንተጋ ነች፡፡ ስልኳን ሰጥሻለው ሰኞ ተገናኙ አብራቹ ሁኑ፡፡" አለኝ ወንድሜ በአውንታ ምላሽ ጭንቅላቴን ነቀነኩኝ፡፡ 'ምን ማለቱ ነው ግን እኔ ህፃን አይደለሁም ከምፈልገው ሰው ጋር ነው በምፈልገው ግዜ ምሆነው፡፡ ምናልባት የመስራቤታቸውም ሰው የወንድሜ ብጤ ይሆናል፡፡' ብዬ አሰብኩ፡፡ አመሻሽ የተጀመረ አሰልቺ ውይይት እስከ ምሽት ሁለት ሰአት ነበር የቀጠለው፡፡ "አረ ይበቃቹሀል እራት ብሉ ተነሱና፡፡"አለች እናቴ ትልቅ የነፃነት ድምፅ የሰማው ያህል ነው የተደሰትኩት፡፡ እናቴ መጥታ ባትገላግለኝ ኖሮ ጭቅጭቅ የሞላበት ነዝናዛ ውይይት ሚያልቅ አይመስለኝም፡፡
በጠረቤዛ ዙሪያ ቀርበን እራት መመብ ስንጀምር ስልኬ ጠራ አይቼ ዘጋውት፡፡ፍሬ ነበር የደወለው "ማነው እሱ!? ማነው በዚህ ሰአት!?" ወንድሜ ተቆጣ፡፡ "አይ ከዶርም ነው የተደወለው ጉዋደኛዬ ነች፡፡"አልኩት ረጋ ባለ ድምፅ፡፡ "አምጪው እስኪ ስልኩን ስነስርአት የላተም በዚህ ሰአት ምን አስደወላት?" ስልኩ ጠረቤዠ ዛው ላይ እንዳለ ወደወንድሜ አስጠጋውት፡፡ መልሶ ጠራ ወንድሜ አይቶት ዘጋው፡፡ ምንም አልተናገረም፡፡ መጀመሪያም ለምን እንደተቆጣ ታውቆኛል፡፡ ወንድ ነው የደወለው ብሎ ነው፡፡ እኔ የቤተሰቦቼን ፀባይ መች አጣሁት የሁሉንም ስልክ በሴት ስም ነው የመዘገብኩት፡፡ ስልኬ ሲጠራ ስሙ 'ሴና 3' ነው ሚለው ሴና ስለሚል የዶርም ልጅ ናት ብሎ ነው ወንድሜ ዝም ያለው እኔ ግን ፍሬን ነው ሴና 3 ብዬ የመዘገብኩት፡፡
ባለፉት ቀናት የነበረው እራት እና የዛሬው ተለየብኝ፡፡ ለካ ሁሉም ነገር በፍቅር ሲሆን ይጣፍጣል፡፡ ቤት ውስጥ ብዙ አይነት ምግብ ቀርቦ እየተመገብን ምንም ጣእም አልሰጥሽ አለኝ፡፡ አነ ፍሬ ጋር ተሻምቼ ምበላው ነው የጣፈጠኝ፡፡እራቴን ጨርሼ ክፍሌ እስክገባ ቸኩያለው . . .
#ክፍል_አስራስድስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉👍
⭕️ታሪኩ ከተመቻችሁ 👍👈 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!
.............ይቀጥላል............✍
🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን