❤ሴና🌺
#ክፍል 1⃣6⃣
#ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ✅
. . . እራት ከተነሳ ቡሀላ ወደ ክፍሌ ገባው፡፡ የክፍሌን በር ከውስጥ ዘግቼ አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ለፍሬ መልእክት ላኩለት፡፡እስኪመልስልኝ ድረስ ስልኬ ላይ እንዳፈጠጥኩ በጭንቅላቴ ብዙ ጥያቄዎች ይመላለሳሉ፡፡ ለምንድነው ወንድሞቼ ግን እንደዚ ሚያስቡት ግን፡፡ ምንድነው እንደዚ ተጠራጣሪ ያደረጋቸው? ምነናልባት እነርሱ ሚያደርጉት ነገር ይሆን? የፍሬ መልእክት ገባልኝ፡፡ ከሀሳብ መንፈስ ወጣሁ ገና መልእክቱ ሲገባ ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡
አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ከፍሬ ጋር ማውራቴን ተያያዝኩት፡፡ አሰልቺ ቀን ነበር ያሳለፍኩት፡፡ በፊት ምንም የማይመስለኝ የወንድሞቼ ጭቅጭቅ ዛሬ በጣም መረረኝ፡፡ ብቻ ፍሬን ሳወራው ማምሻዬን የካሰኝ መሰለኝ፡፡
ጥዋት ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ የወንድሜ ጥሪ ነበር፡፡ በሩን እየደበደበ ሲጠራኝ ውጪ አደጋ የተፈጠረ ነው ሚመስለው፡፡ በሩን ስከፍትለት "ምን መሆንሽ ነው ሰአትሽን አይተሻል? ቆይ ምን ስትሰሪ አምሽተሽ ነው ይህን ያህል?" ወንድሜ አምባረቀብኝ፡፡ ስልኬን አንስቼ ሰአቴን አየሁ 2:30 አካባቢ ነው፡፡ ቢሆንም ግን እንደዚ ሚያስጮህ ነገር የለውም፡፡ምንም አላልኩም ተጣጥቤ ቁርሴን ከበላሁ ቡሀላ ክፍሌን ማስተካከል ጀመርኩ፡፡
ነገ ደርሶ ወደግቢ እስክመለስ ቸኩያለው፡፡ በፊት ምንም የማይመስለኝ ቤት አሁን ግን ነፃነቴን በእጅጉ እንደነፈገኝ ነው የተሰማኝ፡፡ ይዤ የምሄደውን ልብስ እና አንዳንድ መፅሀፍትን በሻንጣዬ ማስተካከል ጀመርኩ፡፡ እንደው ዛሬ ሂጂ ቢሉኝ ትልቅ ደስታ ነው ሚሰማኝ፡፡ ሻንጣዬን አስተካክዬ እንደጨረስኩ ተጣጥቤ ሳሎን ቁጭ ብዬ ቲቪ ማየት ጀመርኩ፡፡ አስር ግዜ ቀና እያልኩ የግድግዳ ሰአት እመለከታለው ሰአቱ አልሄድ አለኝ፡፡ መቼ ነግቶ ከዚህ ቤት እንደምወጣ እያሰላሰልኩ ስልኬ ጠራ፡፡ ከዶርም ነው አንስቼ ሶስቱንም የዶርም ጉዋደኞቼን ተራ በተራ አናገርኳቸው፡፡ ትንሽ ዘና አደረጉኝ ስልኩን ስዘጋው ግን ያ' ድብርት መልሶ ወረረኝ፡፡
እንደለመድኩት ከቤት ሳልወጣ መሸ፤ የተለመደው ምሽት ፣የተለመደው ወሬ ፣የተለመደው እራት ከእራት ብሀላ ክፍሌ ልገባ ስል ትልቁ ወንድሜ ወዴት ነው ምትሮጪው ነይ ቁጭ በይ እናውራ እንጂ አለ፡፡ አልተቃወምኩም ቁጭ ብዬ ሚሉትን መስማት ጀመርኩ ብዙም ሳይቆይ ስልኬ መልእክት ገባ፡፡ መክፈት ግን አልቻልኩም፡፡ ከዚህ ብሀላ ሀሳቤ ወደ ስልኬ ነው፡፡ ቤተሰቦቼ ያወራሉ ይስቃሉ አልፎ አልፎ ለሚጠይቁኝ ጥያቄ መልስ ከመስጠት ውጪ ሀሳቤ ስልኬ ላይ ነው፡፡ ምንም እየተከታተልኳቸው አይደለም፡፡ ወሬያቸው ሚያልቅበት ሰአት ናፈቀኝ፡፡ እንቅልፉ እንደመጣ ሰው መንጠራራት እና አይኔን ማሸት ስጀምር እናቴ "እንቅልፍሽ መጣ መሰለኝ በቃ ግቢና ተኚ፡፡" አለችኝ 'እናቴ ስወድሽ እኮ ነፃነቴን ሰጠሽኝ' እያልኩ በሆዴ ሀሳባቸው ሳይቀየር ፈንጠር ብዬ በመነሳት ስልኬን ይዤ ፈጥኜ ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡
የፍሬን መልእክት መለስኩለት ነገር ግን ሰአቱን ሳየው በጣም መሽቶአል እኩለ ለሊት ሊሆን ምንም አልቀረውም፡፡ 'እነዚ ሰዎች ዝም ብል ኖሮ አስቀምጠው ሊያሳድሩኝ ነበር ማለት ነው?' አልኩኝ በሆዴ፡፡ ፍሬን ትንሽ ጠብቄው እንቅልፌን መቋቋም ስላልቻልኩ ተኛሁኝ፡፡
ዛሬ ሰኞ ነው በጣም ደስብሎኛል፡፡ ወደ ግቢ ልሄድ ነው፡፡ በለሊት ነው የተነሳሁት ደሞ፡፡ ቁርስ እንድበላ ባያስገድዱኝ ኖሮ እንደተነሳው ተጣጥቤ ለባብሼ ያዘጋጀውትን ሻንጣ ሸክፌ ከዚ ቤት ሹልክ ማለት ነበር የፈለኩት፡፡ የኛ ቤት ቁርስ ጣጣው ብዙ ነው ፡፡ ይረፍድብኛል ብልም ወንድሜ ግቢ በር ድረስ አደርስሻለው ስላለ ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡
ቁርስ እንዳለቀ ከወንድሜ ጋር ወጣን የተለመደውን ጭቅጭቅ እና ንዝንዝ የቀላቀለ ምክሩን እየመከረኝ ነው፡፡ አትኩሬ ባላዳምጠውም አልፎ አልፎ ሰማዋለው፡፡ ወደ ግቢ በቀረብኩ ቁጥር የነፃነት ስሜት ይበልጥ እየተሰማኝ ነው . . .
#ክፍል_አስራሰባትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉👍
⭕️ታሪኩ ከተመቻችሁ 👍👈 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!
.............ይቀጥላል............✍
🎙ግሩፑን ለማግኘት
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን