♡ እናቱ ታውቅ ነበር ♡
መልዓኩ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ
ሲታጠቅ ሲፈታ ፊትሽ ተንበርክኮ
ትይዋለሽ አለሽ ልጅሽን ኢየሱስ
መድኃኒት ነውና ሁሉን የሚፈውስ
ብላ ሰየመችው መድኃኒአለም
ሰውን ወዷልና እስከዘለዓለም
ልጄ ወዳጄ ሆይ ስትለው ነበር
እርሱም ለእናቱ ታዟል በፍቅር
ጨለማን የሚያርቅ ብርሃን ወለዳለች
እርሷም የብርሃን እናቱ ተባለች
አምላክን በክንዷ ብትታቀፈው
ወላዲተ አምላክ የእርሷ ስም ነው
ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
እናቱ ታውቅ ነበረ መድኃኒት መሆኑን
ኢየሱስ አለችው ስታወጣ ስሙን
መልዓኩ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ
ሲታጠቅ ሲፈታ ፊትሽ ተንበርክኮ
ትይዋለሽ አለሽ ልጅሽን ኢየሱስ
መድኃኒት ነውና ሁሉን የሚፈውስ
ከስጋዋ ስጋ ነስቶ ከነፍሷ ነፍስ
በተዋህዶ ሚስጢር የኛን ስጋ ቢለብስ
አማኑኤል ተባለ ቢዛመድ ከሰው
ቅዱስ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው
ብላ ሰየመችው መድኃኒአለም
ሰውን ወዷልና እስከዘለዓለም
ልጄ ወዳጄ ሆይ ስትለው ነበር
እርሱም ለእናቱ ታዟል በፍቅር
የትንቢቱን መጽሐፍ እያነበበች
ሀር ወርቁን አስማምታ እየፈተለች
ዙፋኑ መሆኑን አውቃ ነበርና
ገለጸች እራሷን በፍጹም ትህትና
ጨለማን የሚያርቅ ብርሃን ወለዳለች
እርሷም የብርሃን እናቱ ተባለች
አምላክን በክንዷ ብትታቀፈው
ወላዲተ አምላክ የእርሷ ስም ነው
ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈